Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ሰው •═••• •••═• በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ | አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

ይህ ሰው

•═••• •••═•

በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ

በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ

በ17 ዓመቱ 4 የተለያዩ ስራዎቹን አጥቶ ነበር

ከ18 እስከ 22 ዓመቱ የባቡር ትኬት ቆራጭ ሆኖ ሰራ ነገር ግን አልተሳካለትም

የሀገሩን መከላከያ ቢቀላቀልም ተባረረ

ህግ ለመማር አመለከተ አልተሣካለትም

ለአንድ ኢንሹራንስ ድርጂት ግብይት ሰራተኛ ሆነ ይህም አልተሣካለትም

በ19 ዓመቱ ደግሞ ልጅ ወልዶ ነበር 2ዐ ዓመቱ ላይ ሚስቱ ልጃቸዉን ይዛ ጥላዉ ሄደች

በአንዲት ትንሽየ ካፌ ምግብ አብሳይና ሰሃን አጣቢነት መስራት ጀመረ

የራሱን ልጅ አግቶ ሚስቱን ወደ ቤት እንድትመለስ ለማግባባት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀረ
.
.
.
65 ዓመት ሲሞላዉ ጡረታ ወጣ

ጡረታ በወጣ በመጀመሪያዉ ቀን የ$105 ቼክ ከመንግስት ደረሠው። እሱ ግን የተረዳዉ መንግስት "ራስህን መመገብ አትችልም" እንዳለዉ ነበርና ከዚህ በኋላ መኖሩ ጥቅም እንደሌለዉ ራሱን አሣምኖ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረግ፤ ይህም ሳይሆን ቀረ

አንድ እለት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ምኞቶቹን ወረቀት ላይ ማስፈር ፈለገ የፃፈዉ ግን በህይወቱ ሊያደርጋቸዉ እየቻለ ሳያደርጋቸዉ ስለቀሩ ነገሮች ነበር። ከዝያም በእርግጠኝነት ማድረግ እንደሚችለዉ የሚያዉቀዉን አንድ ነገር አሰበ፤ ምግብ ማብሰል፡፡

ወዲያዉም የመንግስትን የዉለታ ቸክ መልሶ $87 ተበደረ

በዚያች ብድርም ቅመሞቹን ሸምቶ ፍራይድ ችክን አዘጋጀ። እናም በኬንታኬይ ለሚኖሩ ጎረቤቶቹ በራቸዉ ድረስ እየሄደ መሸጥ ጀመረ

አስታዉሱ ይህ ሰዉ በ65 ዓመቱ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አድርጎ ነበር

ግን በ68 ዓመቱ ኮሎኔል ሳንደርስ የኬንታኬይ ፍራይድ ችክን KFC ኢምፓየር መስራች ቢሊየነር ሆነ!

«ስለዚህ ወገን ከዚህ ሰው ብዙ መማር ይቻላል ተስፋ መቁረጥ የሰነፎች መፈክር መሆኑን ተገንዝበህ ሁሉንም ሞክር አንድ ቀን መክሊትህ የት እንዳለች ታውቃለህ፣ እሷም ስትቀርባት ትጠራሃለች።

68 አመት እስኪሆንህ መጠበቅ የለብህም


ሰው ሁን ከሰውም ሰው
መልካም አዳር ይሁንላችሁ