Get Mystery Box with random crypto!

እህቴ የጎዳኝ ሰው በይቅርታው ያድነኛል ብለሽ አትጠብቂ! ይልቅስ አንቺ ይቅር በማለትሽ ለሌላ | አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

እህቴ የጎዳኝ ሰው በይቅርታው ያድነኛል ብለሽ አትጠብቂ!

ይልቅስ አንቺ ይቅር በማለትሽ ለሌላ ሰው ሳይሆን ለአንቺ ለራስሽ ከበቀል ደዌ ፈውስ ታገኛለሽ ።

የይቅርታው ንጉስ ኔልሰን ማንዴላ (Madiba) እንዲህ ይላሉ...."በቀል ማለት መርዙን እራስ ጠጥቶ ሌሎች እንዲሞቱ የመጠበቅ ሞኝነት ነው።"

ስለሆነም ይቅርታሽ በውስጥሽ ካለው የበቀል መርዝ ያሽርሻል።

ለዚህም ነው #ይቅርታ 'የአለም ውዱ ስጦታ ነው' የሚባለው!

ልብ አድርጊ ይህን ውድ ስጦታ የምትሰጪው ለጎዳሽ፣ ላሳመመሽ፣ ላስለቀሰሽ፣ ላወረደሽ...በጥቅሉ ለማይገባው ሰው ነው።

ለምን ቢባል ደግሞ በይቅርታው ስጦታ አንቺ ከህመምሽ ስለምትፈወሺ ነው !

እህቴ እዚህ ጋር አንድ ነገር እንዳትረሺ.....

በይቅርታሽ ከባለፈው ትምህርት ትወስጃለሽ እንጂ የጎዳሽን ሰው ወደ ህይወትሽ እንደገና እንዲመልስ ትፈቅጅለታለሽ ማለት ግን አይደለም።

እርምጃሽ በማስተዋል ይሁን!

#ጥበብ እና #ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!
-ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
========================
ሙዳዬ ንዋይ - የቢዝነስ ልህቀት