2023-03-26 14:02:01
ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነውሩሲያ ስልታዊ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በአጋሯ እና በጎረቤቷ ቤላሩስ ውስጥ በማንኛው ጊዜ እንዲተኮሱ ለማድረግ እንደምታጠምድ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ፑቲን አሜሪካ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን በአውሮፓ አገራት ውስጥ ማሰማራቷን በመጥቀስ፣ ይህ የሩሲያ ውሳኔ የኑክሌር ጦር መሳሪያን ለሌላ አገር ላለማስተላለፍ የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ አይደለም ማለታቸውን የሩሲያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የአሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ “ያሉንን ስልታዊ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን አቀማመጥ ለማስተካከል የሚያስገድደን ምንም ምክንያት አይታየንም” ብሏል።
የጦር መሳሪያዎቹ የሚጠመዱባት የቤላሩስ መንግሥት ጠንካራ የሩሲያ ወዳጅ ሲሆን፣ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውንም ወረራ ይደግፈዋል።
ይህ የሩሲያ ውሳኔ የተለየ እንዳልሆነ የጠቀሱት ፑቲን “አሜሪካኖች ተመሳሳይ ነገር ለአስርት ዓመታት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ስልታዊ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን ከረጅም ጊዜ በፊት ነው በወዳጆቻቸው አገራት ግዛት ውስጥ ያሰማሩት” ብለዋል።
በዚህ የሩሲያ እርምጃ ከ30 ዓመታት ወዲህ ሩሲያ ከግዛቷ ውጪ የኑክሌር የጦር መሳሪያ ማስወንጨፊያ ማዕከል ሲኖራት የመጀመሪያው ይሆናል ተብሏል።
#ArifNeger
#Ethiopia #Ethiopiannews #ዜና #News
ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/@Arifneger24
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24
ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
441 views11:02