2023-04-04 10:30:24
የታይዋን ፕሬዝደንት ማስጠንቀቂያውን ወደ ጎን በመተው ከአሜሪካ አፈጉባኤ ጋር ተገናኙ
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲ በዚህ ሳምንት በካሊፎርኒያ የታይዋን ፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌንን እንደሚገናኙ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቻይና ይህ ወደ “ከባድ ግጭት” እንደሚያስገባ አስጠንቅቃለች።
የአሜሪካ-ቻይና ግንኙነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው።
በስለላ ፊኛ ላይ በተነሳው ውዝግብ እና አሜሪካ የቻይናን የላቀ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ለመቁረጥ የምታደርገውን ጥረት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረቱ ተባብሷል።
ሰኞ እለት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ቤጂንግ በአሜሪካ እና በታይዋን መንግስታት መካከል የሚደረግን ማንኛውንም አይነት ይፋዊ ግንኙነት እና ግንኙነት በጥብቅ ትቃወማለች።
ጻይ በፈረንጆቹ 2016 ከተመረጡ ወዲህ ቤጂንግ ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በደሴቲቱ ላይ ከፍ አድርጋለች።
ቻይና ከ13ቱ የታይዋን ዲፕሎማሲያዊ አጋሮች በሚገኙበት ላቲን አሜሪካ የምታደርገውን ኢንቨስትመንት ጨምራለች።
256 views07:30