2023-04-12 10:39:45
ደቡብ ኮሪያ ልጆች ለሚወልዱ ጥንዶች 10,500 ዶላር ጉርሻ አዘጋጅቻለሁ አለች
ምን ይሄ ብቻ ፍቅር ለመጀመር ያሰባችሁ ጥንዶች የፍቅር ቀጠሮ እለት የምታወጡትን ወጪ እኔው እራሴ እሸፍናለሁ ብሏል የደቡብ ኮሪያ መንግስት።
በዓለም ዝቅተኛው የወሊድ መጠን ባለባት ደቡብ ኮሪያ እያሽቆለቆለ ያለው የስነ-ሕዝብ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ መንግስትን እንቅልፍ ነስቷል።
ሁኔታውን ለመቀልበስ የደቡብ ኮሪያ ማዕከላዊ መንግስት ልጅ ለወለደ ማንኛውም ሰው ክፍያን እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለመስጠት እየሞከሩ ይገኛል። እናቶች ልጅ ሲወለዱ 2 ሚሊዮን ዎን ወይን 1,510 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብ ክፍያ ያገኛሉ።
ከዛም ልጆች ለማሳደግ ይረዳቸው ዘንድ ቤተሰቡ በወር 700,000 ዎን ወይም 528 ዶላር በጥሬ ገንዘብ እስከ አንድ አመት ያሉ ህፃናት ወላጆች ይሰጣል። 264 ዶላር ከሁለት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ወላጆች በየወሩ ይቀበላሉ።
#ArifNeger
#Ethiopia #Ethiopiannews #ዜና #news
ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/@arifnegari
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24
ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/profile.php?id=100089842895627
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
339 views07:39