2022-08-25 17:44:33
የእስራኤል እና የአሜሪካ F-35 የጦር ጄቶች በተደጋጋሚ ወደ ኢራን የአየር ክልል ሲዘልቁ መቆየታቸው ተሰማ፡፡
የእስራኤል እና የአሜሪካ የጦር ጄቶች በተደጋጋሚ በኢራን የራዳር ሥርዓት ሳይታዩ ወደ አገሪቱ የአየር ክልል በተደጋጋሚ እንደዘለቁ ዋይ ኔት በድረ ገጹ ፅፏል፡፡
አውሮፕላኖቹ በተደጋጋሚ ወደ ኢራን የአየር ክልል የዘለቁት በልምምድ በረራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
እስራኤል በተደጋጋሚ የኢራንን የኒኩሊየር ተቋማት የማደባየት እቅድ እንዳላት በግላጭ ስትናገር መቆየቷን ዘገባው አስታውሷል፡፡
የእስራኤል እና የአሜሪካ ሚስጥራዊ የጦር አውሮፕላኖች የበረራ ልምምድ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ እየተነሳ ነው ተብሏል፡፡
ኢራን እና እስራኤል በቀጠናው በከፍተኛ የጠላትነት ስሜት የሚተያዩ አገሮች ናቸው፡፡
የኔነህ ከበደ
#ArifNeger
#Ethiopia #Ethiopiannews #ዜና #News
ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/c/Addisnegertop10
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Arifneger
ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
1.4K views14:44