2022-12-13 14:43:17
#ማብሪያ_ማጥፊያዎች/ #Switches:-
በጣም ብዙ አይነት ማብሪያ/ማጥፊያዎች አሉ። ነገር ግን በዚህ ክፍል የምናየው በብዛት የህንፃ መስመር ዝርጋታ ላይ የምንጠቀምባቸውን ሲሆን ማብሪያ/ማጥፊያዎችን በትትክክል የሚያውቅ ሰው ለጥገናም ሆነ አዲስ ስራ ለመስራት አብዛኛውን ዋናውን ነገር አውቋል ማለት ነው።
ማብሪያ ማጥፊያ የኤሌክትሪክ ፍሰትን ለማቋረጥ ይማብሪያጠቅማል። በሌላ አባባል አንድን የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ለማቋረጥ ወይም ለማገናኘት ይረዳናል።
ማንኛውም በኤሌክትሪክ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ትግብራ የሚሰራ እቃ ቢያንስ አንድ ማብሪያ ማጥፊያ ይኖረዋል።
ማብሪያ ማጥፊያዎች የመቆጣጠሪያ ሲስተም አካል ናቸው።
ማብሪያ ማጥፊያዎችን የተለያዩ ቦታዎች እንጠቀምባቸዋልን። ለምሳሌ:- ለመኖሪያ ቤት፣ ለንግድ ቤት፣ ለኢንዱስትሪዎች፣ለጦር መሳሪያዎች፣ ለኤሮስፔስ ወ.ዘ.ተ.
ማብሪያ ማጥፊያዎች ሜካኒካል ወይም ኤሌክትሮኒክ ሊሆኑ ይችላሉ።
ኤሌክትሮኒክ ማብሪያ ማጥፊያዎች /Electronic Switches~ለማብራት ወይም ለማጥፋት አካላዊ ንክኪ አይፈልጉም። ለምሳሌ:- ትራንዚስተር፣ሞስፌት፣ትሪያክ፣ አይጂቢቲ ወ.ዘ.ተ.
ሜካኒካል ማብሪያ ማጥፊያዎች/Mechanical Switches~በመንካት፣ በመጫንና በመልቀቅ ፣በማንቀሳቀስ የሚሰሩ ናቸው።
~በዚህ ክፍል በስፋት የምናየው ሲሆን የተለያዩ ሁኔታዎችን መነሻ በማድረግ በብዙ ምድብ ይከፈላሉ። ነገር ግን አሁን የምናየው የpole እና የ throw ቁጠርን መሰረት አድርገን በከፈልናቸው ምድብ ስር ያሉትን ነው።
~በየቤታችን ያሉት ማብሪያ ማጥፊያዎችም በዚህ ስር ይመደባሉ።
1. #ነጠላ_ማብሪያ_ማጥፊያ/Single Switch:-
one way Switch /Single pole single throw Switch(SPSTS)/ one gang one way Switch ብለን ልንጠራው እንችላለን።
መሰረታዊ ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን አንድ ገቢና አንድ ወጭ አለው።
በዚህ ማብሪያ ማጥፊያ ከአንድ በላይ የሆኑ መብራቶችን መቆጣጠር እንችላለን። ነገር ግን ሁሉንም ማጥፋት ወይም ማብራት ነው የሚቻለው እንጅ በከፊል መቆጣጠር አይቻልም።
የምንጠቀምበት ቦታም:-
ለመፀዳጃ መብራት
ለስቶር መብራት
ለኤሌክትሪክ እቃዎች ወ.ዘ.ተ.
√ባጭሩ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ለምንቆጣጠረው አገልግሎት ሁሉ እንጠቀምበታለን።
2. #ባለሁለት_አቅጣጫ_ማብሪያ_ማጥፊያ/Two way Switch:-
Two way Switch /Single pole double throw (SPDT) Switch/ one gang two way Switch ብለን ልንጠራው እንችላለን።
ሶስት ተርሚናል(ፒን) ያለው ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን አንድ ገቢና ሁለት ወጭ አለው።
ሁለት 'ON' ፖዚሽንና አንድ 'OFF' ፖዚሽን አለው።
ይህ ማብሪያ ማጥፊያ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ መብራቶችን ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ሆነን ለመቆጣጠር ያስችለናል። ማለትም ቦታ 'ሀ' ጋ ሆነን ከበራነው ቦታ 'ለ' ጋ ሆነን ደግሞ ማጥፋት እችላለን ማለት ነው ።
የምንጠቀምበት ቦታም:-
ለመኝታ ክፍል መብራት
ለሳሎን መብራት
ለደረጃ መብራት ወ.ዘ.ተ. ልንጠቀምበት እንችላለን።
3. #ባለ_አራት_አቅጣጫ_ማብሪያ_ማጥፊያ/4 way Switch:-
4 way Switch/intermediate Switch// one gang intermediate Switch/crossover Switch ብለን ልንጠራው እንችላለን።
4 ተርሚናል(ፒን) ያለው ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን ሁለት ገቢና ሁለት ወጭ አለው። አሰራሩም እነዚሀን ተልሚነሎች L1ናL2 ገቢ ቢሆኑና L3 ና L4 ደግሞ ወጭ ቢሆኑ ለመብራት ከ4 አማራጮች አንዱ መገናኘት አለበት። አማራጭችም L1ናL3፣ L2ናL4 ወይም L1ና L4፣ L2ና L3 ሊሆኑ ይችላሉ።
ዋናውና ትክክለኛው አገልግሎቱ አንድና ከአንድ በላይ የሆኑ አምፖሎችን 3ና ከዛ በላይ የሆኑ ቦታዎች ላይ መቆጣጠር ስንፈልግ የምንጠቀመው ነው። ይህን አገልግሎት የምናገኘዉም ባለ 4 አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያን ከባለ 2 አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያዎች ጋር እንደ አስፈላጊነቱ በማቀናጀት ነው።
የምንጠቀምበት ቦታም:-
ለአዳራሽ መብራቶች
ለመኪና ማቆሚያ ቦታ መብራቶች
ለደረጃ መብራቶች ወ.ዘ.ተ. ልንጠቀምበት እንችላለን።
4. #ሁለት_ነጠላ_ወይም_ሁለት_ባለአንድ_አቅጣጫ_ማብሪያ_ማጥፊያ/Double pole one way Switch:-
Double pole Switch/Double pole single throw (DPST) Switch/ Two gang one way ብለን ልንጠራው እንችላለን።
4 ተርሚናል(ፒን) ያለው ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን ሁለት ገቢና ሁለት ወጭ አለው።
ሁለት ነጠላ ማብሪያ ማጥፊያዎችን አንድ ቦታ ላይ መጠቀም ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ቦት ላይ ስለሁነ ሁለት ፌዝ(እሳት) ያለው ገመድ መሳብ ኣይጠበቅብንም አንድ ስበን ለሁለተኛው ሻንት አርገን መስጠት እንችላለን።
በአሁኑ ሰዓሰት በዙ አምራች ድርጅቶች በዚህ ፋንታ ሁለት ባለ ሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ ነው የሚያመርቱት። ምክንያቱም ሁለት ባለ ሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ ለተለያዩ አገልግሎቶችም መጠቀም ስለሚችሉ ነው።
የምንጠቀምበት ቦታም:-
ለሳሎን ወይም ለትምህርት ቤት መብራቶች ቀንሰን ማብራት አስፈላጊ ሲሆን።
ለስቶር መብራትና ለመፀዳጃ ቤት መብራት ሁለቱ ተከታታይ ከሆኑ ወ.ዘ.ተ. ልንጠቀምበት እንችላለን።
5. #ሁለት_ባለሁለት_አቅጣጫ_ማብሪያ_ማጥፊያ/Double pole two way Switch:-
Double pole Switch/Double pole Double throw (DPDT) Switch/ Two gang Two way ብለን ልንጠራው እንችላለን።
6 ተርሚናል(ፒን) ያለው ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን 2 ገቢና 4 ወጭ አለው።
ሁለት ባለሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያዎችን አንድ ቦታ ላይ መጠቀም ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ቦት ላይ ስለሁነ ሁለት ፌዝ(እሳት) ያለው ገመድ መሳብ ኣይጠበቅብንም አንድ ስበን ለሁለተኛው ሻንት አርገን መስጠት እንችላለን።
በአሁኑ ሰዓሰት በዙ አምራች ድርጅቶች በሰፊው እያመረቱት ይገኛል።
የምንጠቀምበት ቦታም ልክ እንደ ሁለት ባለአንድ አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ ሲሁን ልዩነቱ የዚህን ማብሪያ ማጥፊ አንደኛውን ፖል እንደ ባለሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ መጠቀም መቻላችን ነው።
6. #ሶስት_ባለአንድ_ወይም_ባለሁለት_አቅጣጫ_ማብሪያ_ማጥፊያ
Triple pole Single Through (TPST) or Triple pole double through (TPDT)
Three gang Two way Switch or Three gang one way Switch ብለን ልንጠራው እንችላለን።
6/9 ተርሚናል(ፒን) ያለው ማብሪያ ማጥፊያ ሲሆን 3 ገቢና 3/6 ወጭ አለው።
ሦስት ባለአንድ/ ባለሁለት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያዎችን አንድ ቦታ ላይ መጠቀም ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ቦት ላይ ስለሁነ ሶስት ፌዝ(እሳት) ያለው ገመድ መሳብ ኣይጠበቅብንም አንድ ስበን ለቀሪዎቹ ሻንት አርገን መስጠት እንችላለን።
የምንጠቀምበት ቦታም ሶስት የተለያዩ አምፖሎችን በተናጠል መቆጣጠር ስንፈልግ ይሆናል።
#ለሌሎችም_ያጋሩ
#በግል_ወይም_በቡድን_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል።
0911585854
0118644716
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!
#እናመሰግናለን!
1.7K views11:43