Get Mystery Box with random crypto!

Amen Electrical Technology Official®

የቴሌግራም ቻናል አርማ amenelectricaltechnology — Amen Electrical Technology Official® A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amenelectricaltechnology — Amen Electrical Technology Official®
የሰርጥ አድራሻ: @amenelectricaltechnology
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.90K
የሰርጥ መግለጫ

✅We provide professional #training supported by workshop and on-site training which is unique in its kind.
Let's be a reason for the change of others'lives!
Buy ads: https://telega.io/c/amenelectricaltechnology
👉 @electricexpert
📱0911585854
📱0118644716

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-15 14:30:58 #የመብራት_አምፖሎች_ቶሎ_ቶሎ_እየተቃጠሉ_ተቸግረዋል?
== ==
በየጥቂት ሳምንቶች ወይም ወራቶች አምፖሎች ለምን እንደሚቃጠሉ እና ምን  ማድረግ እንዳለብዎት ተቸግርዋል?
በአጠቃቀምዎ መሰረት አምፖሎች ከ4-6 ወር ያለምንም ችግር ይሠራሉ ፡፡ ነገር ግን አገልግሎት መስጠት ያለባቸዉን ያህል ሳይቆዩ ሊቃጠሉ ይቸላሉ ፡፡
አምፖሎች በፍጥነት  የሚቀጥሉባቸው  ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ እንደሚከተለዉ እናያለን ፡፡
1. #ከፍተኛ_ቮልቴጅ
ኢትዮጵያ ውስጥ 220 ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል መደበኛ ነዉ ፡፡ ነገር ግን አንድ አምፖል ከመደበኛዉ በላይ የሆነ ከፍተኛ ሀይል ካገኘ ይሞቃል፤ ቶሎ ቶሎም ይቃጠላል  ፡፡
#መፍትሔው፡-
ፈቃድ ያለው የኤሌክትሪክ ባለሙያ የቤትዎን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በመመርመር የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ ከታወቀ መፍትሔ ማምጣት ይችላል ፡፡
ከፍ ያለ ቮልት የሚያነብ ከሆነ ታዲያ መጪውን ቮልት እንዲመረምር እና በዚህ መሠረት እንዲያስተካክለው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያመልክቱ ይህ ካልሆነ ውድ የኤሌክትሪክ መገልገያዎቾን ሊያጡ ይችላሉ ፡፡
2.#ጥራታቸዉን_ያልጠበቁ_አምፖሎች
አምፖሎችን በፍጥነት ለማቃጠል በጣም ከተለመዱ ምክንያቶች አንዱ ርካሽ ወይም ዝቅተኛ አምፖሎችን መጠቀም ነው ።
አምፖሎች በፍጥነት እየተቃጠሉ ከተቸገሩ  ጥራት ያላቸዉን ለመቀየር ይሞክሩ እና ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ ይመልከቱ ፡፡
#መፍትሄው ፡-
ጥሩ ጥራት ባላቸው አምፖሎች ላይ ትንሽ ተጨማሪ ኢንቬስት ለማድረግ ይሞክሩ ይህም አምፖሎችን ለመተካትና ለኤሌክትሪክ ሙያተኛ የሚያወጧቸዉን ወጭዎች ያስቀራል፡፡
3.#ከመጠን_በላይ_መሞቅ
የአምፖሉ ዋት ከማቀፊያዉ ወይም ከሚመከረው ከፍ ያለ ከሆነ ከመጠን በላይ ሙቀት ሊፈጥር ይችላል ፡፡
ይህ የአምፖሉን ቆይታ የሚቀንስ እና ያለጊዜው እንዲቃጠል የሚያደርግ ነዉ ፡፡
#መፍትሄው፡-
አዲስ አምፖሎችን በሚገጥሙበት ጊዜ ሁል ጊዜም ከማቀፊያዉ ዋቶች ያነሱ ዋቶች መሆናቸዉን ያረጋግጡ ፡፡
4.#ከመጠን_በላይ_የሆነ_ንዝረት
ከጣሪያ አየር ማቀዝቀዣዎች እና ከመግቢያ በሮች አቅራቢያ ያሉ ኢንካንዲሰንት አምፖሎች በንዝረቶች(vibration) ምክንያት  ክር መሳዩ የአምፖሎችን ከፍል እንዲበጠስ በማድረግ በፍጥነት እንዲቃጠሉ ያደርጋሉ ፡፡
ለጥምዝ( CFL) አምፖሎችም  እንዲሁ የተለመደ ጉዳይ ነው ፡፡
#መፍትሔው፡-
ፌከሰቸሩ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን በማረጋገጥ ንዝረትን ይቀንሱ እንዲሁም  የLED አምፖሎች ይጠቀሙ።
5.#ቶሎ_ቶሎ_ማብራትና_ማጥፋት
ይህ ለጥምዝ(CFL) አምፖሎች ትልቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል ፣ ምክንያቱም ኤሌክትሮዶች መብራቱ በሚበራበት ጊዜ ሁሉ ውጥረት ስለሚሰማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ዝቅ እንዲሉ ያደርጋቸዋል ፡፡
ስለዚህ ለ10,000 ሰዓታት አገልግሎት የሚሰጠው የ ጥምዝ(CFL)  አምፖል በአንድ ጊዜ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ከበራ ለ 3,000 ሰዓታት ብቻ ሊቆይ ይችላል ፡፡
#መፍትሄው :-
እንደ መጸዳጃ ቤት ፣ እንቅስቃሴን የሚቆጣጠሩ ሴንሰሮች እና ቁምሳጥን በመሳሰሉ ለአጭር ጊዜ ብቻ በሚበሩ መብራቶች ውስጥ ጥምዝ(CFL) አምፖሎች በ LED አምፖሎች ይተኩ ፡፡
6.#የማይጣጣም_የዲመር_ማብሪያ_ማጥፊያ
የቆዩ የዲመር መቀየሪያዎች ከኢንካድሰንት አምፖሎች ጋር እንዲጠቀሙ ተደርገዋል ፡፡
እነዚህ  መቀየሪያዎች  ለCFL ወይም ለLED አምፖሎች መጠቀም አምፖሉን ወይም ሰርኪዩቱን ሊጎዳ ይችላል ፡፡
በተጨማሪም ፣ ሁሉም አዲስ አምፖሎች ከዲመር ማዞሪያዎች ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም ፡፡
የእርስዎ ደብዛዛ ማብሪያ/ማጥፊያ እና አምፖል እርስ በርሳቸው የሚስማሙ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
#መፍትሔው:-
ከLED አምፖሎች ጋር ለመስራት የተነደፉ የደብዛዛ ማብሪያዎችን መግዛት ይኖርብዎታል ፡፡
የድሮ ደብዛዛ ማብሪያ / ማጥፊያውን ከ LED አምፖሎች ጋር በሚስማማው ብቻ ይተኩ እና ችግሩ ይፈታል!
7.#በአግባቡ_ያልታሰረ_የኤሌክትሪክ_ሽቦ
የባለሙያን ልዕቀት ሊጠይቅ የሚችል አንድ ችግር ይህ ነው ፡፡
ማቀፊያዉ መገናኛው ሳጥን ውስጥ ከሽቦዉ ጋር በትክክል ካልታሰረ ወደ አምፖሉ የሚሄደውን ቮልቴጅ በፍጥነት እንዲለዋወጥ ሊያደርግ ይችላል ፡፡
#መፍትሄው:-
በመገናኛው ሳጥኑ ውስጥ ያሉትን ሽቦዎች ከማቀፊያዉ ተርሚናል ጋር በጥብቅ መገናኘት አለባቸው ፡፡
8.#የተሳሳቱ_ዓይነት_አምፖሎች
ከማቀፊያዉ ጋር ንክኪ በሚያደርግበት አምፖል የታችኛው ክፍል ላይ አንድ አነስተኛ ብይድ ነጥብ አለ ::
ይህ ነጥብ ሁልጊዜ ተመሳሳይ መጠን ያለው መሆን አለበት ፣ነገር ግን አንዳንድ ርካሽ ብራንዶች በቂ ብየዳ የላቸውም ፣ ይህም የአምፖሉን ሕይወት ያሳጥረዋል።
#መፍትሄው፡-
አምፖሉን በተለየ ማቀፊያ ውስጥ ይሞክሩ እና ተመሳሳይ ችግር ካለ ትክክለኛዉን ምርት ይቀይሩ ፡፡

#ለሌሎችም_ያጋሩ

#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት_ወይም_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል።

0911585854
0991156969
0118644716

#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
"#ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#እናመሰግናለን!
296 viewsedited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 14:30:41
313 views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 18:14:26 #የኤሌክትሪክ_ኃይል_መቆራረጥ_መንስዔዎች_እና_መፍትሄዎች!
=======================
በሀገራችን በተደጋጋሚ ለሚከሰተው የኃይል መቆራረጥ እንደ ምክንያት ከሚነሱት መካከል የማስተላለፊያ መስመሮች አቅም ማነስና እርጅና፣ ኃይል አባካኝ የመገልገያ መሳሪያዎች መጠቀም ፣ በየወቅቱ ያለው የኃይል አጠቃቀም ወጥ ያለመሆን እና ረዥም ጊዜ ያገለገሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በመኖሪያ ቤት የሚከሰቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነት መንስኤዎች፡-
የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (ኢንስታሌሽን) ዕውቀት እና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች በተገቢ ሁኔታ ካልተሰራ ወይም ዋየሮች፣ ኬብሎች፣ ሶኬቶች እና ብሬከሮች በተገቢው መልኩ ተመርጠው በአግባቡ ካልታሰሩ ብክነቱ ይጨምራል፣ 
ቤቱ በቂ የፀሃይ ብርሃን እንዲያስገባ ተደርጎ ካልተሰራ የግድ በቀንም የኤሌክትሪክ ብርሀን ያስፈልገዋል ይህም ለብክነት መንስኤ ይሆናል፣
ኃይል አባካኝ የሆኑ አምፖሎችን (የኢነርጂ ፍጆታው ዝቅተኛ ሆኖ ከፍተኛ ብርሃን የሚሰጡ ባለ 7 ዋት ኤል ኢ ዲ አምፑሎች ይልቅ ባለ 60 ዋት የቀድሞ ቢጫ አምፖልን ስንጠቀም)፣ ምድጃዎችን ፣ ምጣዶችን እና ማሽነሪዎችን መጠቀም ወይም አገልግሎት በማይሰጡበት ጊዜ አለማጥፋት እና ሶኬቱን አለመንቀል፣
ትናንሽ የብረት ድስቶችን እና ማንቆርቆርያዎችን ሰፊ በሆነ ምድጃ ላይ መጣድ፤ ይህም መሃሉ ያለው የምድጃው ክፍል የሚያመነጨው ሙቀት በተገቢው አገልግሎት ላይ ሲውል ከድስቱ የተረፈው የምድጃው ክፍል የሚያመነጨው ሙቀት ለብክነት ይዳረጋል፣ 
ረዥም ጊዜ ያገለገሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችም እንዲሁም ለኢነርጂ ብክነት ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በአንፃሩ የኃይል ቁጠባ ማለት ከላይ የተዘረዘሩትን የኢነርጂ ብክነት መንስኤዎች በማስወገድ የኤሌክትሪክ ኢነርጂን በሚፈለገዉ ልክ ብቻ መጠቀም ማለት ሲሆን፣ የማስተላለፊያ መስመሮችን አቅም በማሻሻል እና በቴክኖሎጂ የተሻሻሉ እቃዎችን በመጠቀም ኃይልን መቆጠብ ይቻላል፡፡ ይህም ለማህበረሰቡና ለተቋማት ብሎም ለአገር ኢኮኖሚ አያሌ ጥቅሞች አሉት፡፡ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፡-
የኢነርጂ ብቃታቸው የተሻለ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ስንጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ስለሚቀንስ የምንከፍለው የፍጆታ ሂሳብ ይቀንሳል፣
በኢንዱስትሪ ደረጃ የኃይል ፍጆታ ሲቀንስ ምርቶችን ለማምረት የሚወጣዉ ወጪ ስለሚቀንስ የምርቶች ዋጋ ይቀንሳል ይህም ተፈላጊነታቸውና ትርፋማነታቸው ይጨምራል፡፡
በዋናነት የኤሌክትሪክ ኃይል ቁጠባ ሲኖር ተቋሙ ያለ አስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረትና  ያልተቆራረጠ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያስችለዋል፡፡ 

ያስተውሉ፡-
ጠዋት ከ3፡30-6፡00 እና ማታ ከ12፡00-3፡30 ያለው ጊዜ የኃይል ጫና የሚበዛበት በመሆኑ  ኤሌክትሪክ ባይጠቀሙ ይመረጣል፣
ማንኛውንም የቤት ዉስጥ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ሲገዙ የኃይል ቆጣቢ መሆናቸዉን ያረጋግጡ፣ 
ረዥም ጊዜ ያገለገሉ የቤት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን  ቢቀይሩ ይመከራል፣ 
ሁሉንም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አገልግሎት በማይሰጡበት ጊዜ ያጥፉ፤ ሶኬቶችንም መንቀል አይርሱ

#የራስዎን_ስራ_የሚጀምሩበት_የአጭር_ጊዜ_ስልጠና በመሰልጠን ገቢዎን ያሳድጉ
#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

"#ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!
#እናመሰግናለን!
960 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 21:14:02 ስራ አለ ወይ ? አዎ
ቁጭ ብለው ሳይንከራተቱ
ሳይጋፋ ፣የ አየር ንብረት ሳይቀያየርቦት
ያለምንም ወጪ ከ 0 አመት ጀምሮ
የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች
የትምህርት ዕድሎች፣ወርክ ሾፖች እና የጀማሪ የቢዝነስ ማስታወቂዎችን ለመግኘት እና ጨረታዎች ሁሉንም በአንድ ላይ ለማግኘት
በተኑን በመጫን ይቀላቀሉን
679 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 13:16:46
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_አገልግሎት  እየሰጠው ያለው አዲሱ #ስማር_ኤሌክትሪክ_ሜትር ወይም #ስማርት_ቆጣሪ
====
ስማርት ቆጣሪ የመኖሪያ፣ የንግድ ወይም የኢንደስትሪ ኤሌክትሪክ አጠቃቀምን አውቶማቲክ ንባቦችን ወስዶ መረጃውን በገመድ አልባ ለኃይል አቅራቢዎ ያስተላልፋል። በተጨማሪም መብራት ሲጠፋ ፣ መብራት ላይ የሚደረግን ስርቆት ወዘተ ሌሎች መረጃዎችንም ያስተላልፋል።
#ጥቅሞቹ
1. ደንበኛው የተጠቀመውን ፍጆታ እራሱ ቆጣሪው ስለሚልክ ቆጣሪ የሚያነብ ባለሙያ አያስፈልግም። ይህም ለአገልግሎት አቅራቢው ድርጅትና ለተጠቃሚዎች እንደ ጥቅም ይገለፃል።
2. ለበለጠ ትክክለኛ የሂሳብ አከፋፈል ትክክለኛ ንባቦች በመደበኛነት ስለሚልክ ከቀድሞው ቆጣሪ ይህ ቆጣሪ በጣም ትክክለኛ ፍጆታ ያነባል።
3. ንባቦች በርቀት እንዲሰጡ በማድረግ ወጪዎችን ይቀንሳል። ምንም አይነት ቆጣሪ አንባቢ አያስፈልግም ማለት ነው።
4.የሀይል አጠቃቀምን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።
5. የአጠቃቀም ልማዶችን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ለተጠቃሚዎች ቀላል የሜትር ንባብ ይሰጣል።
6. ሀይል በሚቋረጥ ጊዜ  ኩባንያዎችን ቅድሚያ ለመስጠትና ሚዛናዊ ለማድረግ ይጠቅማል።
#ጉዳቶቹ
1. ስማረት ሜትሩን ገዝቶ በመግጠም ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል።
2. ዘመናዊ የሆነውን የመረጃ ቋት ለመተርጎምና ለማስተዳደር ተጨማሪ መሣሪያዎችን፣ ስልጠናዎችን እና ግብዓቶችን ይፈልጋል።
3. በላቁ ኤሌክትሮኒክስ ምክንያት የሃርድዌር ወጪዎች ይጨምራል።
4. በቆጣሪ ማንበብ ስራ የተሰማሩትን ከስራ ውጪ ያደርጋል።

#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

#ለወዳጅዎም_ያጋሩ
2.0K viewsedited  10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 15:43:39
ማስታወቂያ
#በአይነቱ_ልዩ_የሆነ_ስልጠና

ሰላም  ውድ የአሜ ኤሌክትሪል ቴክኖሎጂ  ቤተሰቦች
#ቅዳሜ_ከሰዐት እና #እሁድ_ጥዋት (3 ወራት)  
እንዲሁም #ከሰኞ እስከ #አርብ(ለ2 ወራት )  በሳምንት 3 ቀን በወርክሾፕና 1ቀን የሳይት ላይ ልምምድ  የሚሰጡትን 12ኛው እና 13ኛው ዙሮች  #የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታ_ስልጠና #ቅዳሜ በቀን 19/06/15 ምዝገባ ይጀመራል።ስለዚህ ለመሰልጠን ፍላጎት ያላችሁ #ቦሌሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን እንደምናሰለጥን እንገልፃለን።
የስልጠናው ሙሉ ክፍያ 5000 ብር ሲሆን በሁለት ጊዜ ክፍያ የሚከፈል ይሆናል። የመጀመሪያ ግማሽ ክፍያ  2500 ብር እና የመመዝገቢያ ክፍያ 150 ብር በድምሩ 2650 ብር ይሆናል።
ክፍያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የድርጅቱ አካውንቶች ገቢ በማድረግ የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝ ፎቶ  በዚህ ሊንክ  @electricexpert  በመላክ ወይም በአካል ይዘው መምጣት መመዝገብ ይችላሉ።
በአካል በመምጣት ካሺ መክፈልና መመዝገብም ይችላሉ።
በነዚህ ፕሮግራሞች የማይመቻችሁ 6650 ብር በመክፈል በሚመቻችሁ ቀንና ሰዐት #በግል መሰልጠን ትችላላችሁ።
ስልጠናው #በወርክሾፕና_በሳይት_ላይ_ልምምድ በልዩ ሁኔታ ይሰጣል።
ድርጅቱ የባንክ አካውንቶች
#የኢትዮጵያንግድ_ባንክ: 1000454398932
#አቢሲንያ_ባንክ: 88939409
Amen institute of technology
#በአካል_መሰልጠን_የማትችሉ _የYouTube ስልጠና ለመከታተል ሊንኩን በመጫን #Subscribe ያርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw/
#ለተጨማሪ_መረጃ
0911585854
0991156969
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!
#እናመሰግናለን!
515 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:47:07 #የኤሌክትሪክ_መብራቶች_ለምን_ብልጭ_ድርግም_ይላሉ? #ወይም_ይርገበገባሉ?
=========================
ብዙ ሰዎች ይህ የመብራት ብልጭ ድርግም ማለት ያጋጥማቸውል፤ ብዙዎችም ልክ እንደ አስፈሪ ፊልሞች ያስቡታል።
የኤሌክትሪክ ሀይል የቤትዎን ቤት ከሚያረጉት አንዱ ነው ነገር ግን ችግሮች በሚፈጠሩበት ጊዜ የቤትዎን፣ የቤተሰብዎን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል።
ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ምቾት ከመንሳቱም በላይ በጊዜ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ንብረት ይጎዳሉ እንዲሁም በመቶወች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤሌክትሪክ ምክንያት በሚፈጠር እሳት ሂወታቸውን ያጣሉ።
ጠቅለል ስናረገው ብልጭ ድርግም የሚሉ መብራቶች ለአፍታ የቤታችን የቮልቴጅ መቀነስ ወይም መለዋወጥ  ወጤቶች ናቸው።
ዋና ዋና ምክንያቶችን ማወቁ ችግሩን ለመፍታት ስለሚጠቅም እንደሚከተለው ቀርቧል:-

፩. #በደንብ_ያልታሰረ_አምፖል/#Loose_Bulbs
አምፖል ሲታሰር ባለመጥበቁ ምክንያት የሚፈጠር የመብራት ብልጭ ድርግም ማለት በብዛት የተለመደ ሲሆን መፍትሄውም አጥብቆ መሰር ነው።
ላልቶ የታሰረ አምፖል ተለዋዋጭ  ሀይል ስለሆነ  የሚያገኘው የምናገኘውም የብርሀን  ፍሰት ወጥነት የሌለው ነው።
ነገር ግን ፍሎረሰንት መብራቶች መጀመሪያ ሲበሩ የሚያሳዩት ብልጭ ድርግም ማለት ተፈጠሯዊ ነው።
፪. #ከፍተኛ_የሆነ_ከረንት_ወይም_ቮልቴጅ_ሺመነጭ/#Large_Current_or_Voltage_Draws
የቤታችን ቮልቴጅ በጣም ከፍ ካለ መብራቶች ብልጭ ድርግም እንዲሉ ያደርጋል። አለፍ ሲልም መብራቶች ብርሃን እንዳይሰጡና እንዲቃጠሉ ያደርጋል።
ይህ አይነት ችግር ካጋጠመ ከፍተኛ ችግር ከመፍጠሩ በፊት በኤሌክትሪክ ሙያተኞች መስተካከል አለበት።
፫.#የተሳሳቱ_አስተሳሰሮች/#Faulty_Connections
ትክክል ያልሆነ አስተሳሰር በማቀፊያዎች፣ በማብሪያማጥፊያዎች ወ.ዘ.ተ ላይ ካለ ይህ ችግር ያጋጥማል።
መፍትሄውም መቀፊያውን ወይም ማብሪያ ማጥፊያውን ይዘን በማወዛወዝ መለየት ይቻላል። ይህ ችግር መሆኑን ካወቅን አስተካክለን ማሰር ተገቢ ነው።
፬. #ተገቢ_ያልሆነ_ዲመር_ማብሪያ_ማጥፊያ_መጠቀም/#Using_Incompatible_Dimmer_switch
ለ LED አምፖሎች ዲመር ማብሪያ ማጥፊያ ከተጠቀምን ብልጭ ድርግም የሚለው ነገር ይከሰታል።
ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ በብዛት ዲመር ማብሪያ ማጥፊያ የምንጠቀም ከፍተኛ ኤሌክትሪካል ሀይልን ለመቆጣጠር ነው። ነገር ግን LED አምፖሎች በጣም በትንሺ ሀይል ነው ሚጠቀሙት። በዚህም የተነሳ ዝቅተኛ ሀይል የሚፈልግን አምፖል በከፍተኛ ዲመር ማብሪያ/ማጥፊያ ለመቆጣጠር ስንሞክር አምፖሉ መደብዘዝ ወይም መርገበገብ ይጀምራል።
መፍትሄውም ለዝቅተኛ ሀይል የሚሆኑ ዲመር ማብሪያ/ማጥፊያዎችን መጠቀም ነው።
፭. #የአምፖል_አይነት/#Bulb_type
ፍሎረሰንት አምፖሎች ከLED ወይም ከሌሎች አምፖሎች በላይ ይርገበገባሉ። ምክንያቱ ደግሞ መብራት ሲመጀመር ለማሞቅ፣ ርጅም ጊዜ ያገለገል ከሆነ፣ የሙቀቱ ሁኔታ ሲሆን በመጠኑ መርገብገቡ የተለመደ ሲሆን በተከታታይ ለረጅም ጊዜ ከሆነ ግን ፍሎረሰንቱ መቀየር ይኖርበታል።
ተቀይሮም ብልጭ ድርግም ማለቱ ከቀጠለ ከላይ የተጠቀሱትን ሌሎች ምክንያቶችን ማየቱ አስፈላጊ ነው ።
፮. #ጉድለት_ያለው_አምፖል/#Defective_Lamp
አምፖሉ የተበላሸ ወይም ጤነኛ ካልሆነ ሊከሰት ሰለሚችል መፍትሄው አምፖል መቀየር ነው።
፯.#የጉረቤት_ኤሌክትሪክ_አጠቃቀም/#Electrical_Usage_from_Neighbors
ቤታችን በሰፈራችን የሚገኝ ትራንስፎርመርን በጋራ በሚጠቀም ጊዜ የጉረቤቶቻችን የሀይል አጠቃቀም የኛን የሀይል መጠን ላይ ተፅዕኖ አለው።
የጉረቤቶቻችን ከፍተኛ ሀይል መጠቀም የኛን መብራት እንዲርገበገብ ሊያደርገው ይችለል።
ይህን ችግር በኤሌክትሪክ ሙያተኛ ችግሩን ከለዩ በኋላ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 905 ላይ ደውሎ በማመልከት መፍትሄ ምግኘት ይችላሉ።

#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ማሰራት_ለምትፈልጉ_ድርጅቶችና_ግለሰቦች_ደግሞ_በነዚህ_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል።
    
  0911585854
  0991156969

"#ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!
እናመሰግናለን!
995 viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:39:25
#የኤሌክትሪክ_መብራቶች_ለምን_ብልጭ_ድርግም_ይላሉ
#ወይም_ይርገበገባሉ
702 viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:37:12 #መጥፎ_የህንፃ_የኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታ_ምልክቶች/#Signs_of_bad_Wiring
=========================
በሀገራች ልክ ያልሆነ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ለሰው ሂወት መጥፋትም ሆነ ለንብረት ውድመት እንደዋና ምክንያት የሚጠቀስ ይጠቀሳል። ለዚህ ደግሞ እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰው በተለይ  ለህንፃ የኤሌክትሪክ ስራዎች ትኩረት አለመስጠት እና የሚሰራውን ሙያተኛ የሙያ ሁኔታ ግምት ውስት አለማስገባታችን ነው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በትክክል ያልተሰራ የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ምልክቶች ሲሆኑ መስተካከል ያለባቸው ናቸው።
1. #ከመጠን_በላይ_የኤሌክትሪክ_ገመድ_የበዛበት_ፓኔል/ #Overloaded_Electrical_panel
ከምናስበው በላይ የተዝረከረኩ የኤሌክትሪክ ገመዶች  ፓኔላችን ወይም ዲስትሪቢውሽን ቦርድ ላይ ካሉ ልክ አይደልም።
ግልፅ የሆነ አስተሳሰር እና  እርዝመታቸውም በልክ መሆን አለበት።
2. #መብራቶች_የሚርገበገቡ_ወይም_ፈዛዛ_ከሆኑ / #Blinking_or_dim_lights
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚርገበገቡ መብራቶችን ችላ ይላሉ።  መብራቶች ሙሉ ለሙሉ ካልጠፉ የሚርገበገቡ ወይም የደበዘዙ ሌላው ቀርቶ እዝዝ.. የሚል ድምፅ ድምፅ የሚያሰሙ መብራቶች እንዲታዩ አይደረግም።
ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ያረጁ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ ኤሌክትሪክ ገመዶች እርስበርስ የታሰሩበት ቦታ የላላ ወይም ከመጠን በላይ የሆነ ጭነት ስለሚሆን በብቁ ሙያተኛ ታይተው መፍትሄ መስጠት አለበት።
3. #ብሬከር_ቶሎ_ቶሎ_የሚመልስ_ከሆነ/#Tripping_Circuit_Breaker
ብሬከሮች የተሰሩት የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ችግር ሲኖር እንዲመልሱ ተደርጎ ነው።
የሚሰጡት ምላሽም በጣም ፈጣን ሲሆን በኤሌክትሪክ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን እሻት ለማስቀረት ሀይሉን ያቋርጡታል።
እነዚህ ሰርኪዩቶች በተደጋጋሚ የሚመልሱ ከሆነ መስመሩ መታየት ይኖርበታል።
4. #እዝ_የሚል_ድምፅ__ወይም_የሚነዘር_ከሆነ/ #Buzzing_Sound_or_Electric_Shock
እዝ የሚል ድምፅ ካለ ኤሌክትሪክ ከረንት በዙሪያው ባሉ ሌሎች የኤሌክትሪክ ሽቦች መካከል ወይም አጠገቡ በሚገኙ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ በሆኑ እቃዎች ይፈሳል ማለት ነው።
ይህ ምልክት የሚያሳየው የኤሌክትሪክ ዝርጋታው መታየት እንዳለበት ነው። 
ይህ ምልክት ከጊዜ በኋላም ሊከሰት ይችላል።
5. #የቃጠሎ_ሽታ/ #Burning_Odor
ይህ ምልክት ብዙ ጊዜ የሚታይ ችግር ሲሆን የኤሌክትሪክ ገመዶች በጣም ሲሙቁ ይከሰታል።
በዚህ ጊዜም ቶሎ መፍትሄ ካልተሰጠው የኤሌክትሪክ ሽቦው የውጨኛው ክፍል ይቀልጥ እና ፌዝና ኒውትራል ይገናኙ እና ሾርት ሰርኪዩት፣ የመብራት መቋረጥ ወይም እሳት ሊከሰት ይችላል።
6. #ማብሪያ_ማጥፊያዎች_እና_ሶኬቶች_ከሞቁ / #Hot_outlets_or_Switches
ሶኬቶች ወይም ማብሪያ ማጥፊያዎች አይሞቁም። ነገር ግን የሚሞቁ ከሆነ ልክ ስላልሆነ ብሬከር አጥፍቶ የኤሌክትሪክ ባለሙያ በመጥራት መሰራት አስፈላጊ ነው።

#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe ያርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw

#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ማሰራት_ለምትፈልጉ_ድርጅቶችና_ግለሰቦች_ደግሞ_በነዚህ_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል።
    
  0911585854
  0991156969

"#ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ!
እናመሰግናለን!
599 viewsedited  11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:28:38 #የኤሌክትሪክ_ጥገና / #Electric_Maintenance
=====================
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃወች ወይም የቤታችን መሰመር ብልሽት ሲያስተናግድ የምናስተካክልበት መንገድ ጥገና ይባላል።
ብልሽት ሊይስከትሉ የሚችሉ ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው።
1. #ክፍት_የኤሌክትሪክ_መስመር ( #open_circuit)
የክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም
የጭነት መብዛት
የፊዉዝ መቃጠል
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መበጠስ
በደንብ አለመገናኘት ወይም አለመርገጥ
መዛግ
መላላት
2. #የተገናኘ_የኤሌክትሪክ_መስመር (#short_circuit)

የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም፦
የመቃጠል
የሙቀት መብዛት
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ
እርጥበት
3. #የኤሌክትሪክ_መስመር_ከአካሉ_ጋር_መገናኘት ( #grounding)
የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር እዲገናኙ የሚያደርጉ መንስኤዎች
የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ
እርጥበት
የመቃጠል
የመላላት
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ብልሽቶች ይሁኑ እንጂ እያንዳንዱ ብልሽት አንዱ ሌላዉን እንደሚያመጣ ይታወቃል።ለምሳል የኤሌክትሪክ ሥርጭት በአቐራጭ መገናኘት ከአካሉ ጋር መገናኘትን መበጠስን ያመጣል።
ብልሽቶች በመብራት ፣ በሞተር፣ በትራንስፎርመር ላይ ተመሣሣይ ቢሆም ምልክታቸዉና የጥገና ሥራቸዉ ይለያያል።ለምሳል መብራትን የወሰድ እንደሆነ አምፖሉ ከተቃጠለ ያለዉ አማራጭ መጣል ነዉ።ሞተርን ወይም ትራንስፎርመር ሽቦ(winding) ከተቃጠለ ተጠግኖ በሥራ ላይ ይዉላል።
#ብልሽትን_የመለየት ዘዴ
ብልሽቶች በተለያዩ መንገዶች ይታወቃል።
መረጃን የማወቅ የመለየት ዘዴ አጠቃቀም አንደሰዉ ልምድ ቢለያይም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ።
በማየት
በመስማት      
በመመርመሪያ መሣሪያ በመጠቀም
#በማየት
የኤልክትሪክ ዕቃዎች ብልሽት ( ለምሳል ምጣድ,ምድጃ ) የተበጠሰ ወይም የተቃጠለ ከሆነ በመፍታተ ውስጡን በመመልከት ብልሽቱ ማወቅ ይቻላል።
#በመስማት
በመስማት ዕቃዎቹ ብልሽቱ ሲያጋጥማቸዉ ሙሉ በሙሉ ሥራቸዉን በማቐማቸዉ ብቻ ሳይሆን እየሰሩ በሚፈጥሩት ድምፅ ሊደርስ የሚችለውን ብልሽት አስቀድሞ ማስተካከል ይቻላል።
#በመመርመሪያ_መሣሪያ_በመጠቀም
ማንኛዉም የኤሌክትሪክ ዕቃ ብልሽት ሲገጥመዉ በቀላሉ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን በመጠቀም የብልሽቱ ዓይነት ለይቶ ለማወቅና ለጥገና አመቺ መሆኑንና አለመሆኑን መለየት ይቻላል።
የመፈተሻ መሣሪያዎች:-
መልቲ ሜትር
ሜገር
መብራት
ቴሰተር
#መልቲ_ሜትር
ይህ የመመርመሪያ የመፈተሻ መሳሪያ ቮልቴጅን ፣ከረንትንና የሬዚስታንስ መጠን የሚለካልን መሣሪያ ነዉ።
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ዕቃዎች ሁሉ በዉስጡ ሬዚስታንስ (ከረንት ተቃዋሚ) አለዉ።
ከፍተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ አነስተኛ ነዉ።
አነስተኛ ጉልበት ያለዉ የኤሌክትሪክ ዕቃ ሬዚስታንሱ ሲለካ መጠኑ ከፍተኛ ነዉ።
የተበጠሰ ገመድ ወይም ያልተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ በጣም ከፍተኛ ነዉ።
ያልተበጠሰ ገመድ ወይም በአቐራጭ የተገናኘ መስመር ሬዚስታንሱ ወደ ዜሮ ይጠጋል።
#በኤሌክትሪክ_የሚሰሩ_መሳሪያዎች_ጥገና
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን ለመጠገን በመጀመሪያ እቃዎችን ጠንቅቆ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ።
በዚህ መሰረት አንድ ኤሌክትሪሺያን ማወቅ የሚገባዉ:-
እቃዉ እንዴት እንደሚሰራ መረዳት
በኤሌክትሪክ እቃ ላይ የተፃፉትን መረጃዎች ማወቅ
ለእቃዉ መጠገኛ የሚዉሉትን መለኪያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ
የሚጠገኑ እቃዎች ሲፈቱ በጥንቃቄ መረጃዎችን መሰብሰብ        
የጥገና ቅደም ተከተል መሰረት በማድረግ መታየት የሚገባቸዉ የመሳሪያዉ አካል በኃይልና በኤሌክትሪ መፈተሻ መሳሪያ መመርመር
ከኤሌክትሪክ መሳሪያው ወይም ከሚጠገኑ እቃዎች ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ሰራተኞ ወይም ግለሰቦች ስለ እቃዉ ሁኔታ ማነጋገርና መረጃ መሰብሰብ
#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe ያርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
#ለሌሎችም ያጋሩ
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት_ወይም_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል።

0911585854
0118644716
0991156969


#አሜን_ኤሌክትሪካል_እና_ኤሌክትሮሜካኒካል_ስራዎች_ስራ_ተቋራጭ
730 viewsedited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ