2023-04-04 16:39:00
#የኤሌክትሪክ_አክሰሰሪዎች_ከመሬ_ወይም_ከወለል_ያላቸው_ከፍታ (Electrical Accessories Height from the floor):-
========================
የተከበራችሁ የአሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች የዕለቱን ትምሀርት ከመጀመራችን በፊት ሰሞኑን ስለጠፋን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። በጣም ይቅርታ ብዙዎቻችሁ ጠፋችሁ አቆማችሁት ወይ? እያላችሁ ስጠይቁን ነበር ። በጭራሽ እናንተ እሰከወደዳችሁት ድረስ አናቆምም። ባለችን ትርፍ ሰዓት ተጠቅመን የምናውቀውን ለማካፈል በጣም ደስተኞች ነን። ነገር ግን በስራ መደራረብና በተለያዩ የግል ምክንያቶች ቶሎ ቶሎ ላንገባ እንችላለን። ይህን ደግሞ እንደምትታገሱን እርግጠኞች ነን። ስለምትታገሱንም ምስጋናችን ከፍያለ ነው።
አሁን በቀጥታ ወደ ትምህርቱ ስንገባ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ማለትም ማብሪያና ማጥፊያ፣ ሶኬት፣ ቆጣሪ፣ ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ ወ.ዘ.ተ. ከወለል ያላቸውን ከፍታ ነው የምናየው።
ብዙዎቻችሁ ስለነዚህ አክሰሰሪዎች ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ብዙ መፅሐፍ አንብባችሁ ይሆናል፤ ምናልባት ትክክለኛ መረጃ አላገኝ ብላችሁ ግራ ተጋብታችሁ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ አንፃራዊ ትክክለኛ ቦታውን አውቃችሁ የምትሰሩም ትኖራላችሁ። ጭራሹንም ደግሞ ስለ አቀማመጡ ግድ የማይሰጣችሁ አስባችሁትም የማታውቁ መስራቱ ላይ ብቻ ትኩረት የምታደርጉ ትኖራላችሁ። ሁላችሁም ተከታተሉን መልሱን ታገኛላችሁ።
አሜሪካን ሀገር የሚገኘው "ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ደንብ" ወይም "National Electrical Code" የተባለው የግል ድርጅት ስለሁሉም ጥቃቅን የሚባሉት እንኳን ሳይቀሩ በስፋት ህጎችንና መመሪያዎችን አስቀማጧል። አሁንም የአለማችን ሀገሮች እየተጠቀሙበት የገኛሉ። ነገር ግን የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ምንም ያለው ነገር የለም።
"አለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ደንብ" "International Electrical Code" ቢሆንም ግለፅ የሆነ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ያስቀመጠው ነገር የለም።
"የኢትዮጵያ ህንፃ ደንብ መመሪያ" ወይም "Ethiopian Building Code standard" የሚለው መፅሃፍም ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ህጎች በዚህ መፅሐፍ የሚዳኙ ቢሆንም አብዛኞቻችሁ እንዳያችሁትና ከስሙም እንደምንረዳው ለግንባታ/ለሲቪል ስራው ብቻ የተዘጋጀ ነው የሚመስለው ፤ ለማንበብ ስትሞክሩም እንቅልፍ ጠሪ ነው ። ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ህግ የለም በዛ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ስራውም ተጠቅልሎ ለሲቪል ምህንድስናው ተሰቷል። እንኳን ስለኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ሌሎች ህጎችም መፅሐፉ ላይ የተጠቀሱት በግልፅ አልተቀመጡም።
ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ያላቸው ከፍታ እነዚህ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ካልተጠቀሰ ለምን ከፍታቸውን ማወቅ አስፈለገ? ለምን እንደፈለግን አንዘረጋቸውም/አናስራቸውም?
መለሱም አዎ በግልፅ የተቀመጠው ህግ ያላቸው ሀገሮች ሊኖሩ ቢችሉም። እንደምሳሌ በተጠቀሱት ላይ ግልጽፅ የሆነ ህግ የለም። ነገር ግን ለእይታ እንዳይደብር በማሰብ፣ ለመጠቀም ለሁሉም አምች እንዲሆን፣ አደጋን ለመቀነስ በማሰብ እንዲሁም አቅመደካምችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተለመደ የከፍታ መጠን አለ።
ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ያላቸው ከፍታ የስምምነት ወይም የምርጫ ጉዳይ ነው። ነገር ግን በጣምም ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት የለባቸውም የተለየ ፍላጎት ከሌለ በስተቀር። በተቻለ መጠን ፊት ለፊት የሚታይና ለአጠቃቀም ምቹ ማድረግ ነው። በብዛት የምንጠቀምበት የተለመደ ከፍታ አለ እሱን ከማየታችን በፊት የበለጠ ትኩረት ስለሚገባን ነጥቦች እንይ:-
አንዴ በጀመርነው ከፍታ መጨረስ። ይህ የአብዛኛው ሙያተኛ ችግር ነው። ነገር ግን መሆን ያለበት ቦታ ላይ በተለያየ ምክንያት ማድረግ ካልቻልን ትንሺ ከፍ ወይም ዝቅ ልናደርግ እንችላለን።
በተቻለ መጠን አክሰሰሪዎች ተመሳሳይ ቀለም፣ መጠንና ቅርፅ እንዲኖራቸው ማድረግ
ስንገጥም ውሃ ላክችን መጠበቅ መንጋደድ የለበትም። ትንሽም ቢሆን።
point ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ተብሎ ለይታ ደስየማይልና ከተለመደው አስራር ውጭ በፍፁም አለመስራት።
ለአቅመ ደካሞች(ለሽማግሌዎችና ለአዛውንቶች)ና ለአካል ጉዳተኞች ሲባል ሶኬቶችን በጣም ዝቅ ማለት የለባቸውም፤ ማብሪያ ማጥፊያዎች ደግሞ በጣም ከፍ ማለት የለባቸውም።
በተቻለ መጠን በጣም ህፃን ልጆች ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም የቤተሰብ አባል እራሳቸውን ችለው አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ።
አዲስ ዝርጋታ ካለሆነ በስተቀር የሚቀየር ወይም የሚጠገን ከሆነ ከፍታውን ከሌሎች ጋር እኩል ማድረግ ነው ያለብን።
የሻወር ቤት ወይም የመፀዳጃ ሶኬትና ማብሪያ ማጥፊያ በተቻለ መጠን ከፍ ማለት አለባቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ከውሃ መራቅ አለባቸው።
በተቻለ መጠን ከማንኛውም ኮርነር፣ በር፣ መስኮት ወ.ዘ.ተ. 35cm መራቅ አለባቸው።
እነዚህን ግንዛቤዎች ከያዝን በብዛት የተለመደውንና ከላይ የጠቀስናቸውን መሰረት ያደረገ የከፍታ መጠን በቀጣይ እናያለን።
የቀጠለ...3
በበዛት የተለመደውና አብዛኛቻችን የምንስማማበት የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ያላቸው ከፍታ:-
የክሰሰሪ ከወለል ያላቸው
አይነቶች ከፍታ በ cm
1. ማብሪያ/ማጥፊያ..............130-140
2.ሶኬት....................................45-50
3.ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ...........170-175
4.ኪችን ሶኬት.........................90-100
5.አኑንሴተር............................170-175
6.ቤል ስዊች..........................130-140
7. ቆጣሪ................................175-180
8.ሻወር/መፀዳጃ ቤት ሶኬት..180-200
9. ሻወር/መፀዳጃ ቤት ማብሪያ ማጥፊያ...............................150
ማሳሰቢያ:- ከዚህ በፊትም እንዳልነው ዋናው ነገር ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ ማድረግ ነው። ስለዚህ ቦታው ላይ ያሉትን ነገሮች ታሳቢ በማድረግ እንደሁኔታው ከፍም ዝቅም ማለት ይችላል።
#አዲሱን_የYouTube_Channel ሊንኩን በመጫን #Subscribe እያደረጉ የበለጠ እንድንሰራ ያበርቱን
https://www.youtube.com/channel/UCAdqgLHZGPPay3oBXmfC6Vw
#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ማሰራትና_መሰልጠን_የምትፈልጉ_ድርጅቶችና_ግለሰቦች_በነዚህ_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል
0911585854
0991156969
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን "
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ
#እናመሰግናለን
906 views13:39