Get Mystery Box with random crypto!

Alpha Sport

የቴሌግራም ቻናል አርማ alphasportet — Alpha Sport A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alphasportet — Alpha Sport
የሰርጥ አድራሻ: @alphasportet
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.60K
የሰርጥ መግለጫ

የሚዲያ ሽፋን የተነፈገውን የኢትዮጵያ ስፖርት ለማሳደግ ከሰፈር እስከ ጠፈር በትኩረት እንዘግባለን !!

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-24 14:58:46
አፄዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል ። ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከነማ በ ሙጂብ ቃሲም ግብ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

በዘንድሮ የውድድር አመት ሙጂብ ቃሲም በ ቤት ኪንግ የ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ሶስተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ። ፋሲል ከነማ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችለዋል ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ ሀምሳ ስምንት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ። ሀዋሳ ከተማ በ አርባ ሁለት ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

በቀጣይ ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ መከላከያ የሚገናኙ ይሆናል ።

@Alphasportet
4.5K viewsedited  11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 12:34:46
አቡበከር ናስር በ70 ጎሎች ፣ በሪከርዶች ፣ በኮከብነት ማዕረጎች እና አይረሴ ክስተቶች ከታጀበው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስደናቂ ቆይታው በኋላ ዛሬ በክብር ወደ ደቡብ አፍሪካ ተሸኝቷል።(Soccer Ethiopia)

@Alphasportet
4.2K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 12:20:59
አዞዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል አርባምንጭ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል ።

ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመው አርባምንጭ ከተማ በ አህመድ ሁሴን ግብ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

አቡበከር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና የመጨረሻ ጨዋታውን ያከናወነ ሲሆን በዘንድሮ የውድድር በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ አስራ አራት ግቦችን አስቆጥሮ አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ አርባ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ። ኢትዮጵያ ቡና በ አርባ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።በቀጣይ ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገናኙ ይሆናል ።

@Alphasportet
4.1K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 10:03:25
" መልካሙን ሁሉ ይግጠምህ "

የኢትዮጵያ ቡና ቡድን አባላት በክለቡ ደማቅ ስኬትን ላገኖፀፋቸው ኮከባቸው አቡበከር ናስር ሽኝት የሚያደርጉ ይሆናል ።

በዚህም መሰረት የቡድን አባላቱ ለተጫዋቹ በቀጣይ " መልካሙን ሁሉ ይግጠምህ " ሲሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈውለታል ።

አቡበከር ናስር በቀጣይ ወደ ደቡብ አፍሪካው ሀያል ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚያቀና ይሆናል ።

@Alphasport
3.8K viewsedited  07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 18:11:37
ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር መዉረዳቸዉን አረጋግጠዋል።

በ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሚወርዱ ሦስት ክለቦች መካከል ሁለቱ ቀሪ ሁለት የጨዋታ ሳምንታት እየቀሩ ተለይተዋል። አዲስ አበባ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር በ2015 ወደ ሁለተኛው የሀገሪቱ የሊግ እርከን መውረዳቸው ተረጋግጧል።

@Alphasportet
4.2K viewsedited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 15:07:55
ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቷቸዋል !

የሀያ ሰምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቷቸዋል ።

• ድሬዳዋ ከተማን የገጠመው ባህር ዳር ከተማ በ መናፍ ዐወል ግብ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

• በዘንድሮ የውድድር አመት መናፍ ዐወል በ ቤት ኪንግ የ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

• የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ ሰላሳ ሶስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

• ድሬዳዋ ከተማ በ ሀያ ዘጠኝ ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

• በቀጣይ ባህር ዳር ከተማ ከ ሰበታ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከ አዳማ ከተማ የሚገናኙ ይሆናል።

@Alphasportet
4.6K views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ