Get Mystery Box with random crypto!

አፄዎቹ ድል ቀንቷቸዋል ! የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ | Alpha Sport

አፄዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል ። ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከነማ በ ሙጂብ ቃሲም ግብ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

በዘንድሮ የውድድር አመት ሙጂብ ቃሲም በ ቤት ኪንግ የ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ሶስተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ። ፋሲል ከነማ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችለዋል ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ ሀምሳ ስምንት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ። ሀዋሳ ከተማ በ አርባ ሁለት ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

በቀጣይ ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ መከላከያ የሚገናኙ ይሆናል ።

@Alphasportet