Get Mystery Box with random crypto!

Alpha Sport

የቴሌግራም ቻናል አርማ alphasportet — Alpha Sport A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alphasportet — Alpha Sport
የሰርጥ አድራሻ: @alphasportet
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.60K
የሰርጥ መግለጫ

የሚዲያ ሽፋን የተነፈገውን የኢትዮጵያ ስፖርት ለማሳደግ ከሰፈር እስከ ጠፈር በትኩረት እንዘግባለን !!

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-29 21:32:50
ፋሲል ከነማ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሎግ አ.ማ ደብዳቤ ፅፏል።
5.8K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:31:51
ፋሲል ከነማ ከሜዳ ምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታዉን አቅርቧል !!

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014 የዉድድር ዘመን ሊገባደድ የቀናት እድሜ ብቻ እንደቀሩት ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በተለይ የዋንጫ ባለቤቱን እና ቀሪ ወራጅ የሆነዉ ቡድን ለመለየት ሳኝነት ያላቸውን ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት በሶስት ስታዲየሞች ለማካሄድ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ፕሮግራም ማዉጣቱ ይታወሳል። በዚህም ክለቦች ጨዋታዎቻቸውን እንዲያካሂዱ የተመደበላቸው ስታዲየም አግባብነት የጎደለዉ ስለመሆኑ እና አክሲዮን ማህበሩ በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲሉ ጠይቀዋል። ሙሉ ደብዳቤው ከታች በምስሉ ተያይዟል።
5.5K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 15:03:57
የዛሬዉ ጨዋታ የጎሎቹ ባለቤቶች !

* ሁለገቡ ተጫዋች ሙጅብ ቃሲም በፊት መስመር አጥቂነት በተሰለፈባቸዉ ሶስት ጨዋታዎች 5ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

* አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸዉ ደግሞ ከሁለት አመታት በኋላ በዛሬዉ ዕለት ኳስ እና መረብን ማገናኘት ችሏል።

@Alphasportet
6.0K viewsedited  12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 14:57:42
ተጠናቀቀ | ፋሲል ከነማ 3 - 0 ኢትዮጵያ ቡና

ሙጂብ ቃሲም
ሱራፌል ዳኛቸው

√ አፄዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ የሊጉን መሪነት ተረክበዋል ።

@Alphasportet
5.6K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 13:16:17
12' ሙጂብ ቃሲም ፋሲልን መሪ ያደረገ ጎል አስቆጥሯል

15'

ፋሲል ከነማ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና

@Alphasportet
4.8K views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 18:04:31
ባህርዳር ከተማ በሜዳዉ እና በደጋፊዉ ፊት አስቀድሞ መዉረዱን ካረጋገጠዉ ሰበታ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ዉጤት አጠናቋል።

ተጠናቀቀ| ባህር ዳር ከተማ 1-1 ሰበታ ከተማ

ኦሴ ማዊሊ ሳሙኤል ሳሊሶ

@Alphasportet
5.1K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 07:15:11
የ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀግብር ዛሬ በሚደረጉ ሶስት ወሳኝ ጨዋታዎች ጅማሮዉን ያደርጋል።

@Alphasportet
5.0K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 19:38:08
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 በ28ኛ ሳምንት በየተደረጉ 8 ጨዋታዎች ላይ 17 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ሲቆጠሩ 39 ቢጫ ካርድ በተጫዋቾች ላይ ተመዘዋል ፥ በሳምንቱ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ሰኔ 18 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ፍሪምፖንግ ሜንሱ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሪችሞንድ ኦዶንጐ(አዲስ አበባ ከተማ)፣ ፍሬው ጌታሁን(ድሬደዋ ከተማ) ፣ ክሌመንት ቦዬ(መከላከያ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቾቹም ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ ሲወሰን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ(ድሬዳዋ ከተማ) ክለቡ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኃላ የድህረ ጨዋታ ቃለመጠይቅ አለመስጠታቸው ሪፓርት የተደረገባቸው ለፈፀሙት ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል::

@Alphasportet
4.8K viewsedited  16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 10:49:58
ይሄን ያውቁ ኖሯል !!

የወቅቱ ኮከብ ተጫዋቾች አቡበከር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደረገዉ በ2009 ከአርባምንጭ ከተሚ ጋር ሲሆን በትላንትናው ዕለት ደግሞ ከአምስት አመታት ቆይታ በኋላ ከክለቡ ጋር ሲለያይ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገዉ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር መሆኑ የተለየ ግጥምጥሞሽ ሆኗል።

ተጫዋቹ ከቀጣዩ የዉድድር አመት አንስቶ ለደቡብ አፍሪካው ማሚሎ ዲሰንዳወስ ለመጫወት ፊርማዉን ማኖሩ ይታወሳል።

@Alphasportet
4.4K viewsedited  07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:29:13
የደረጃ ሰንጠረዡ

@Alphasportet
4.4K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ