Get Mystery Box with random crypto!

አዞዎቹ ድል ቀንቷቸዋል ! የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ | Alpha Sport

አዞዎቹ ድል ቀንቷቸዋል !

የሀያ ስምንተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል አርባምንጭ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል ።

ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመው አርባምንጭ ከተማ በ አህመድ ሁሴን ግብ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል ።

አቡበከር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና የመጨረሻ ጨዋታውን ያከናወነ ሲሆን በዘንድሮ የውድድር በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ አስራ አራት ግቦችን አስቆጥሮ አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ አርባ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ። ኢትዮጵያ ቡና በ አርባ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።በቀጣይ ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገናኙ ይሆናል ።

@Alphasportet