Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO ABOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduna1 — ETHIO ABOL E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduna1 — ETHIO ABOL
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduna1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 193
የሰርጥ መግለጫ

📰 ጥቅሳች
📖 አባባሎች
📰ቁሞነገር
🍂አስገራሚ እውነታዎች
🌫ቀልዶች

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-10 21:09:54 ምኞት የህይወት ግማሽ ነው ።
ስሜት አልባነት ደግሞ
የሞት ግማሽ ነው ።
/ ካህሊል ጂብራን /
202 viewsI'm .........Nothing, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 18:46:27 TikTok
Movie
Series Movie
Music
All in one
What Fuck are you luking join nowwwwwwwwwww
https://t.me/Applefrezer
195 viewsĶŰŔŰ, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:03:21 ዋልያዬ

የሀገሬ ክብሯ ለአለም ሲራባ
የደስታን እንባ አይኔ እያነባ
ከቶ እንዴት ልቻለው ደስታና ለቅሶዬን
የሀገሩን ሰንደቅ የጠላት ጠላት ሲቆስል በሀዘን

በልጆቿ ላብ ከፍ ከፍ ስትል
መጻይ ተስፋዋን ከእንብርቷ ላይ ስታጎነቁል
የተሸመቀው ጦርና ሾተል
ሸማቂውን አዙሮ ሲገድል
ከተራራው ላይ ቆሞ እንደ ዝግባ
ከአላማው ሳይደርስ ቤቱ ማይገባ
ዋልያ ማለት ካፀናው እግሩን ማያንቀሳቅስ
ለሀገር ክብር ደሙን ጨርሶ መቅኔውን 'ሚያፈስ።

ኳስ ብቻ አይደለም፣ ጎልም አይደለም። ከጀርባው ያየሁት መቼም! የትም! አይበገሬ እምቢ ለሀገሬ መሆናችንን ነው!!!

ተጨዋቾቹን እንዳትረሽን አል-ሲሲ

@ahaduna1
171 viewsI'm .........Nothing, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 16:57:36 የብልፅግና እንባ
(በላይ በቀለ ወያ)

.
.
ከላይ ከሰማያት...
ህዝቦች በድለውት ፤ ይህ መንግስት ያለቅሳል
ከታች ያለ ፍጥረት...
"ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል።
ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ
የሀገሬ ገበሬ...
በመንግስት እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ።
፣።።።።።።።።
እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው
ትእግስት አጠራቅሞት...
ለወራት የቆየ ፤ የመንግስት እንባ ነው።
።።።
ከማንባቱ በፊት...
ማዘኑን ሊያረዳን ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ
መንግስት ሲቆጣ...
ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ።
።።።።
የሀገሬ ገበሬ.....
ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል
የገበሬው በሬ...
ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል
በዚህ መንግስት እንባ
በዚህ ህዝብ ደባ
የታረሰ መሬት...
ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል
ከላይ መንግስታችን...
ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል
ከታች ያለ ፍጥረት
ርሀቡን ሊያስታግስ
ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል።
።።።
ለእንደገና ዝናብ
ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ
የሀገሬ ገበሬ……
ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ።

(በላይ በቀለ ወያ)
@ahaduna1
140 viewsI'm .........Nothing, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 15:04:59 ስብሀት ወዶ አይደለም!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ስብሀት የማይለው፣
ወይ ትርጉም አቶ ነው፣ ወይ አግኝቶለት ነው።

"ጋሽ ስብሀት ወደህ አይደለም አይደል.....?"

"አዎ ልጄ።..... ወድጄ አይደለም።"

"አስቲ ተረት አውራልኝ..?"

"ተረት..?"

"አዎ ተረት"

"እኔ ተረት አልችልም።"

"ያው ትፅፍ የለ..?"

"ተረት...?"

"አዎ ተረት"

"ተረት እኮ አይደለም"

"እና ምንድነው ..?"

"ህይወት ነው"

"ህይወት ይፃፋል እንዴ...?"

"ሁሉም አይደለም እንጂ...."

"ለምን ሁሉም አይፃፍም..?"

"ሁሉም አይገኝማ ልጄ።"

"ታድያ ጎዶሎ ህይወት አለ...?"

"ለዚህ እኮነው ተረት ያላኳት።"

"ማንን...?"

"ህይወትዋን...."

"አይ ጋሼ..."

"አይ ልጄ..."

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እንዲህ የሚፅፈው፣
ሰውን አንዳይመረው ነው፣ እሱን የመረረው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ድሀ ድሀ ያለው፣
አሄን ድህነት፣ ገልጦ ስላየው ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ጋሽ ስብሀት ባለጌ ነህ አይደል...?"

"ሰው ብቻውን አይባልግም"

ማለቴ የምትፅፈው እርቃንን ነው..?"

"ታድያኮ እሱ እውነት ነው።"

"ፅሁፍህ ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው..?"

"አይደለም ውሸትም አለበት አንዳንዴ እኮ ሰዎችን ልብስ አለብሳቸዋለሁ።"

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እርቃንን የፃፈው፣
አዳምና ሄዋን፣ ትዝ ብለውት ነው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ወሲብ ወሲብ ያለው፣
የጉድ መፈልፈያ መሆኑ፣ ገብቶት ነው።

https://t.me/ahaduna1
124 viewsI'm , 12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 14:31:16 << ምንድን ነዉ ብሄሩ ? >>
( ( አርጋዉ ሙሃመድ ) ) #Ethiopia
አባቱ ወሎ ነዉ መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸዉ ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካሠላዋ ቆንጆ ተጋብተዉ ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫዉ ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፍር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተዉ ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ ! ሲሉ
አፖስቶ ነዉ አቦ ! ሀረር ባህሉ
ወሎ ከቤንሻጉል ልጅ ወልደዉ ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነዉ ብሄሩ ??

@ahaduna1
128 viewsI'm, 11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 14:09:20 አንችን_ላለማጣት_ወዳጅሽን_ላግባት ===========////============
አንችን ማጣት ማለት …
በስሜት የሆነ ደስታን እንደመናድ
በአዕምሮ የሆነ ጥበብ እንደመካድ
በመንፈስ የሆነ ፍቅርን እንደማቅለል
ከመውደድ የመጣ ሸክም እንደመቆለል ነው
እኔ ምቆጠረው - ብየ ብነግርሽም
ከቶ በጄ አላልሽም
ወይም አላመንሽም
ወይም አልፈለግሽም
ወይም አልገባሽም …መብትሽ ነው ፡፡
መለየት ብርቅ ነው ?.
ለእኔም ግን መብት አለኝ
ማንም የማይሰጠኝ
ማንም የማይነጥቀኝ
ባታስጠልይኝም በሕይወትሽ አክናፍ ባታስደርሽኝም
ከመኖሪያሽ በራፍ
ለመዳን በማሰብ ካንች ፍቅር ቅጣት
ሌላ ዘዴ ዘይድሁ - "አንችን ላለማጣት"
.
ያኔ እንደነገርሽኝ
እህቴ ናት ያልሺኝ ? ነው ወይስ ጓደኛሽ ?
ብቻ ምስጢረኛሽ
አንቺ እርሷን መለየት? - ከቶ አይደረግም
እሷም አንቺን ማጣት? - ፈጽሞ አትፈልግም
ስለዚህ ተመቸኝ …ከዛሬ ጀምሮ እቀበላታለሁ !
እርሷ አፍቅራኛለች - አረጋግጫለሁ፡፡
.
ያልነገርሁሽ ምሥጢር…
ያኔ አንችን ፍለጋ ደጅሽ ስመላለስ - ሲበዛ መንገዴ
ሰላም እላት ነበር - እርሷን በማናገር ልቀርብሽ በዘዴ
እርሷም በደስታ ታናግረኝ ነበር - ስላልገባት ጉዴ
.ከዕለታት አንድ ቀን…
"ለምን ትፈራለህ ? ችግርህ ገብቶኛል
በቃል ባታወጣው ዓይንህ ይነግረኛል
ፍቅሬ ብትሆን እኮ… ለእኔም ደስ ይለኛል
"ብላ ስትነግረኝ ሴቷ ቃል አውጥታ
አልደፈርኩም ነበር - "አልሆንሽም" ብዬ መውደዷን ልገታ.
ምክንያቱም …
ዓመታት ሲነጉዱ - እየተመላለስኩ አንችኑ ፍለጋ
ተመልሼ አላውቅም ሳልደርስ ከእሷ ጋ
መጽናኛ እንዲሆነኝ - ሀሳብ እየፈጠርሁ ጥበብ ስናወጋ
ጥበብ አፍቃሪ ናት - በጥበብ ወሬ ነው ልቧ የተወጋ፡፡
በውል ላስተዋለው - የፍቅሯ መጠኑ - ሊርቁትይከብዳል ፤
በጊዜ ቢለካ አንችን ካፈቀርሁሽ - ከእኔው ጋር እኩል ነው ቢቀር ያሳብዳል ፡፡.
ስለዚህ ወሰንኩኝ…እኔ አንችን አጥቼ - አብጄ ከምዞር
እርሷም እኔን አጥታ - ተጎድታ ከምትኖር
እናንተ ሁለቱ - ተለያይቶ መኖር ስለማትችሉ
የፍቅራችን መፍትሄ ይሄውልሽ ውሉ
፡-.
እርሷን ላግባትና አንቺ ሚዜ ሁኛት
ቤቷ ቤትሽ ይሁን እየመጣሽ ጎብኛት
አየሽ መፍትሄ ማለት…?.
በፍቅሬ እንዳልጎዳት እርሷን አገባለሁ
ፍቅርሽ እንዳይጎዳኝ ስትመጭ አይሻለሁ.
ያው ነግሬሻለሁ…
አንችን ምፈልገው ልተኛሽ አይደለም
በመተኛት ሚታይ የሰው ፍቅር የለም
ለሩካቤ መኖር - እንስሳዊ ግብር - ከውስጣችን ይውጣ
በመንፈስ እንሁን - በአዕምሮ እንዋደድ - ይሄው ነው የእኛ ዕጣ፡፡

#share
@ahaduna1
@ahaduna1
130 viewsI'm, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 07:31:19 ​[ - - - "#የህይወት_ህጎች" - - - ]


ከመናገርህ በፊት | ☞ አስብ ★
ከመፈረምህ በፊት | ☞ አንብብ ★
ከማስተማርህ በፊት | ☞ ተማር ★
ከመምከርህ በፊት | ☞ ተግብር ★
ከመቁረጥህ በፊት| ☞ ለካ ★
ከማጉደልህ በፊት | ☞ ተካ ★
ከመዋጥህ በፊት | ☞ አላምጥ ★
ከመገንዘብህ በፊት | ☞ አድምጥ ★
ከማመንህ በፊት | ☞ አረጋግጥ ★
ከመረከብህ በፊት | ☞ ቁጠር ★
ከመወሰንህ በፊት | ☞ መርምር ★
ከመስራትህ በፊት | ☞ አቅድ ★
ከመተኮስህ በፊት | ☞ አልም ★
ከመተቸትህ በፊት | ☞ አጣራ ★
ከመብላትህ በፊት | ☞ ስራ ★
ከመሞትህ በፊት | ☞ ነሰሃ ግባ ★
ከመሄድህ በፊት | ☞ተስፋ ሰንቅ ★
ስትወያይ-----☞ ሁን አስተዋይ ★
ስትናደድ---- ☞ ቶሎ ብረድ ★
ስትናገር---- ☞ በቁምነገር ★
ስትቸገር---- ☞ መላ ፍጠር ★
ስትቀመጥ---- ☞ ቦታ ምረጥ ★
ስትወስን---- ☞ ቆራጥ ሁን !!
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
152 viewsĶŰŔŰ , 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 07:30:18 ለፈገግታ
ድንገት ብመንገድ ላይ ቆንጆ ልጅ አይቼ
እሷን እያየሁኝ እይኔን ኣንከራትቼ
በአታላዩ አፌ እትት እያልኳት
ፋዘር vitzማዘርሆቴል አላት
ቤታችን ቪላ ቲቪያችን ፍላት
ብዬ አስደምሚያት
ልስም ስስናዳ....








ፋዘር ከች አለልኝ
አህያ እየነዳ
136 viewsĶŰŔŰ , 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 00:03:03
429 viewsĶŰŔŰ , 21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ