Get Mystery Box with random crypto!

ስብሀት ወዶ አይደለም! ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ስብሀት ወዶ አይደለም፣ | ETHIO ABOL

ስብሀት ወዶ አይደለም!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ስብሀት የማይለው፣
ወይ ትርጉም አቶ ነው፣ ወይ አግኝቶለት ነው።

"ጋሽ ስብሀት ወደህ አይደለም አይደል.....?"

"አዎ ልጄ።..... ወድጄ አይደለም።"

"አስቲ ተረት አውራልኝ..?"

"ተረት..?"

"አዎ ተረት"

"እኔ ተረት አልችልም።"

"ያው ትፅፍ የለ..?"

"ተረት...?"

"አዎ ተረት"

"ተረት እኮ አይደለም"

"እና ምንድነው ..?"

"ህይወት ነው"

"ህይወት ይፃፋል እንዴ...?"

"ሁሉም አይደለም እንጂ...."

"ለምን ሁሉም አይፃፍም..?"

"ሁሉም አይገኝማ ልጄ።"

"ታድያ ጎዶሎ ህይወት አለ...?"

"ለዚህ እኮነው ተረት ያላኳት።"

"ማንን...?"

"ህይወትዋን...."

"አይ ጋሼ..."

"አይ ልጄ..."

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እንዲህ የሚፅፈው፣
ሰውን አንዳይመረው ነው፣ እሱን የመረረው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ድሀ ድሀ ያለው፣
አሄን ድህነት፣ ገልጦ ስላየው ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ጋሽ ስብሀት ባለጌ ነህ አይደል...?"

"ሰው ብቻውን አይባልግም"

ማለቴ የምትፅፈው እርቃንን ነው..?"

"ታድያኮ እሱ እውነት ነው።"

"ፅሁፍህ ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው..?"

"አይደለም ውሸትም አለበት አንዳንዴ እኮ ሰዎችን ልብስ አለብሳቸዋለሁ።"

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ እርቃንን የፃፈው፣
አዳምና ሄዋን፣ ትዝ ብለውት ነው።

ስብሀት ወዶ አይደለም፣ ወሲብ ወሲብ ያለው፣
የጉድ መፈልፈያ መሆኑ፣ ገብቶት ነው።

https://t.me/ahaduna1