Get Mystery Box with random crypto!

የብልፅግና እንባ (በላይ በቀለ ወያ) . . ከላይ ከሰማያት... ህዝቦች በድለውት ፤ ይህ መንግ | ETHIO ABOL

የብልፅግና እንባ
(በላይ በቀለ ወያ)

.
.
ከላይ ከሰማያት...
ህዝቦች በድለውት ፤ ይህ መንግስት ያለቅሳል
ከታች ያለ ፍጥረት...
"ዝናብ ጣለ" ብሎ ፤ ምድሪቱን ያርሳል።
ወራትን ጠብቆ፤ ርሀቡን አስታግሶ
የሀገሬ ገበሬ...
በመንግስት እንባ ነው ፤ የሚበላው አርሶ።
፣።።።።።።።።
እንዲያው በተለምዶ፤ ዝናብ የምንለው
ትእግስት አጠራቅሞት...
ለወራት የቆየ ፤ የመንግስት እንባ ነው።
።።።
ከማንባቱ በፊት...
ማዘኑን ሊያረዳን ፤ ሰማይ ጠቁሮ ሳለ
መንግስት ሲቆጣ...
ትውልድ ያማትባል፤ "መብረቅ" ነው እያለ።
።።።።
የሀገሬ ገበሬ.....
ሰማዩን እያየ፤ ምድሪቱን ያርሳል
የገበሬው በሬ...
ሳር ሳሩን እያየ፤ ከገደል ይደርሳል
በዚህ መንግስት እንባ
በዚህ ህዝብ ደባ
የታረሰ መሬት...
ስንዴና እንክርዳዱን፤ባንድ ላይ ያበቅላል
ከላይ መንግስታችን...
ስንዴን ከእንክርዳዱ ፤ሊለይ ይታገላል
ከታች ያለ ፍጥረት
ርሀቡን ሊያስታግስ
ስንዴና እንክርዳድን፤ ደባልቆ ይበላል።
።።።
ለእንደገና ዝናብ
ለእንደገና በደል ፣ ለእንደገና ለቅሶ
የሀገሬ ገበሬ……
ሰማይ ሰማይ ያያል፤ ደረቅ መሬት አርሶ።

(በላይ በቀለ ወያ)
@ahaduna1