Get Mystery Box with random crypto!

> ( ( አርጋዉ ሙሃመድ ) ) #Ethiopia አባቱ ወሎ ነዉ መካነ ሠላም እናቱ ከጎጃም መርጦ ለ | ETHIO ABOL

<< ምንድን ነዉ ብሄሩ ? >>
( ( አርጋዉ ሙሃመድ ) ) #Ethiopia
አባቱ ወሎ ነዉ መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸዉ ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካሠላዋ ቆንጆ ተጋብተዉ ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫዉ ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፍር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተዉ ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ ! ሲሉ
አፖስቶ ነዉ አቦ ! ሀረር ባህሉ
ወሎ ከቤንሻጉል ልጅ ወልደዉ ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነዉ ብሄሩ ??

@ahaduna1