Get Mystery Box with random crypto!

አንችን_ላለማጣት_ወዳጅሽን_ላግባት ===========////============ አንችን ማጣት ማለት | ETHIO ABOL

አንችን_ላለማጣት_ወዳጅሽን_ላግባት ===========////============
አንችን ማጣት ማለት …
በስሜት የሆነ ደስታን እንደመናድ
በአዕምሮ የሆነ ጥበብ እንደመካድ
በመንፈስ የሆነ ፍቅርን እንደማቅለል
ከመውደድ የመጣ ሸክም እንደመቆለል ነው
እኔ ምቆጠረው - ብየ ብነግርሽም
ከቶ በጄ አላልሽም
ወይም አላመንሽም
ወይም አልፈለግሽም
ወይም አልገባሽም …መብትሽ ነው ፡፡
መለየት ብርቅ ነው ?.
ለእኔም ግን መብት አለኝ
ማንም የማይሰጠኝ
ማንም የማይነጥቀኝ
ባታስጠልይኝም በሕይወትሽ አክናፍ ባታስደርሽኝም
ከመኖሪያሽ በራፍ
ለመዳን በማሰብ ካንች ፍቅር ቅጣት
ሌላ ዘዴ ዘይድሁ - "አንችን ላለማጣት"
.
ያኔ እንደነገርሽኝ
እህቴ ናት ያልሺኝ ? ነው ወይስ ጓደኛሽ ?
ብቻ ምስጢረኛሽ
አንቺ እርሷን መለየት? - ከቶ አይደረግም
እሷም አንቺን ማጣት? - ፈጽሞ አትፈልግም
ስለዚህ ተመቸኝ …ከዛሬ ጀምሮ እቀበላታለሁ !
እርሷ አፍቅራኛለች - አረጋግጫለሁ፡፡
.
ያልነገርሁሽ ምሥጢር…
ያኔ አንችን ፍለጋ ደጅሽ ስመላለስ - ሲበዛ መንገዴ
ሰላም እላት ነበር - እርሷን በማናገር ልቀርብሽ በዘዴ
እርሷም በደስታ ታናግረኝ ነበር - ስላልገባት ጉዴ
.ከዕለታት አንድ ቀን…
"ለምን ትፈራለህ ? ችግርህ ገብቶኛል
በቃል ባታወጣው ዓይንህ ይነግረኛል
ፍቅሬ ብትሆን እኮ… ለእኔም ደስ ይለኛል
"ብላ ስትነግረኝ ሴቷ ቃል አውጥታ
አልደፈርኩም ነበር - "አልሆንሽም" ብዬ መውደዷን ልገታ.
ምክንያቱም …
ዓመታት ሲነጉዱ - እየተመላለስኩ አንችኑ ፍለጋ
ተመልሼ አላውቅም ሳልደርስ ከእሷ ጋ
መጽናኛ እንዲሆነኝ - ሀሳብ እየፈጠርሁ ጥበብ ስናወጋ
ጥበብ አፍቃሪ ናት - በጥበብ ወሬ ነው ልቧ የተወጋ፡፡
በውል ላስተዋለው - የፍቅሯ መጠኑ - ሊርቁትይከብዳል ፤
በጊዜ ቢለካ አንችን ካፈቀርሁሽ - ከእኔው ጋር እኩል ነው ቢቀር ያሳብዳል ፡፡.
ስለዚህ ወሰንኩኝ…እኔ አንችን አጥቼ - አብጄ ከምዞር
እርሷም እኔን አጥታ - ተጎድታ ከምትኖር
እናንተ ሁለቱ - ተለያይቶ መኖር ስለማትችሉ
የፍቅራችን መፍትሄ ይሄውልሽ ውሉ
፡-.
እርሷን ላግባትና አንቺ ሚዜ ሁኛት
ቤቷ ቤትሽ ይሁን እየመጣሽ ጎብኛት
አየሽ መፍትሄ ማለት…?.
በፍቅሬ እንዳልጎዳት እርሷን አገባለሁ
ፍቅርሽ እንዳይጎዳኝ ስትመጭ አይሻለሁ.
ያው ነግሬሻለሁ…
አንችን ምፈልገው ልተኛሽ አይደለም
በመተኛት ሚታይ የሰው ፍቅር የለም
ለሩካቤ መኖር - እንስሳዊ ግብር - ከውስጣችን ይውጣ
በመንፈስ እንሁን - በአዕምሮ እንዋደድ - ይሄው ነው የእኛ ዕጣ፡፡

#share
@ahaduna1
@ahaduna1