Get Mystery Box with random crypto!

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhemewiya — 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuhemewiya — 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍
የሰርጥ አድራሻ: @abuhemewiya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.50K
የሰርጥ መግለጫ

የጠራ እውቀት ከተቃና አቐም ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 18:32:27
ከላይኛው ፅሁፍ የተወሰደ ትልቅ ነጥብ
506 viewsأبو حموية, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:38:09 ተለቀቀ

አዲስ መፅሐፍ

"ሙስሊሞችን "ሰለፍያ" ፣ "ሱፍያ" ፣ "አሻዒራ" ፣ በሚሉ ስያሜዎች አትከፋፍሏቸው። ሁላችንም ሙስሊሞች ነን?"

በሸይኽ ሑሴን ብን ሙሐመድ አስስልጤ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዱልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ወደ አማረኛ የተመለሰ

በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል

በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq
323 viewsأبو حموية, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:31:46 የሀገራችን ሙመይዓዎች
ልብ ብሎ ላስተዋለ ሁሉ ከሚታዩ የሙመይዓዎች ጥመቶች ውስጥ:
5 ጥንድ ጥፋቶች ለምሳሌ

ያፈረሱት እና የገነቡት
ለዚህ ዘመን አይበጅም በሚል አዳዲስ በፈበረኳቸው መርሆዎች መንሃጅ አሰለፍን ንደው ህንፃ ገንብተዋል።ከሙብተዲዖች ጋር ለመኗኗር ሲሉ ሀቅን ደብቀው ቀብረዋል።

ያንቋሸሹት እና ያወደሱት
ለተውሂድና ሱነህ የሚተጉ ሰለፊዎችን አንቋሸው ሙብተዲዖችን አወድሰዋል። ዑለማዎችን ጭምር "ወሰን አላፊ ፣ አቡጀህል ፣ የረድ ጉረኛ ፣ የእንጨት ሽበት ፣ እብድ ወዘተ " እያሉ በተቃራኒው ደግሞ ግልፅ የወጡ አጥማሚዎችን አወድሰዋል ፤ ጥብቅና ቆመውላቸዋል ።
ሰለፊዮችን ንቀው አንቋሸው ሙብተዲዖችን ክበው አወድሰዋል።

የበተኑት እና የሰበሰቡት
እንደ አንድ ልብ የሚዋደዱ የነበሩ የሀቅ ጀመዓዎችን አነታርከው በትነዋል።በዚህም ከጠማሞች ድጋፍና ውዳሴን አግኝተዋል። የሱነህ መድረሳዎችን በትነው የሂዝቢየህ ስብስቦችን አፍርተዋል።

የተጣሉት እና የተወዳጁት
ከሙሽሪኮች ጋር ሳይቀር ተደራድረው ፣ ከሙብተዲዖችም ጋር ተቀራርበው ልዩነታቸውን አጥብበው ሊተባበሩ ተስማምተዋል። ሰለፊዮችን ግን ለማናገር በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ምክንያት እየደረደሩ ሰንበተው፣ በንቀት አልፈው ጠላትነታቸውን አሳውቀዋል።

የከሰሩት እና ያተረፉት
ብዙ ከልባቸው ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ሰለፊዮችን ፣ አስተማሪ የነበሩ ኡስታዞችና ትልልቅ ዑለማወችን በየቦታው ከስረዋል ያተረፉትን ግን አላውቅም። የሂዝቢይ ቲፎዞ ማብዛት ፣ ጭፍን ሙሪዶችን መኮትኮት እና በጥቅማጥቅም የተለጎሙ ሙለቢሶችን መያዝ እንደሆነ በራሱ ኪሳራ ነው።

እንደዚህ ነገሩ ተገላባብጦባቸዋል።

{ رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا }.
ጌታችን ሆይ: ቅንኑን ከመራሀን በኋላ ልቦቻችንን አታጣምብን።

 " اللَّهُمَّ مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ "
ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ: ልቤን በዲንህ ላይ አፅናት።

ሸምሱ ጉልታ
https://t.me/Abuhemewiya
6.0K viewsأبو حموية, 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:17:22 ሸርህ አሱነህ አልበርበሃሪይ ክፍል 116።

የኸዋሪጅ (ተክፊሮች) ፣ የሀዳዲይ እና የሙርጂዓህ ጥመት

ከዚህ በፊት የተለቀቁ ክፍሎች እስከ 115 ብቻ እንዳገኛችሁ ለነገራችሁኝ ሁሉ ቀጣዮችን ክፍሎች በተከታታይ እለቃለሁ።
إن شآء الله
https://t.me/Abuhemewiya
1.2K viewsأبو حموية, edited  17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:26:33 Hey! Join our live stream: https://t.me/+kmYBQDWa0qY0ZTU0
1.2K viewsأبو حموية, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:20:18 የሱንና ዓሊሞቻችንን ምክር አጥብቀን እንያዝ!!
———
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ብለዋል:-
«ነፍሲያችን እና ወንድሞቻችንን የምንመክርበት ነገር፣ አላህን በመፍራት ላይና በደጋግ ቀደምቶች መንገድ በመጣበቅ!፣ እንዲሁም ከቢድዓና ከሙብተዲዓዎች መጠንቀቅን፣ ትክክለኛውን ዓቂዳንና የሚቃረነውን በማስተማር ላይ ትኩረት መስጠትን፣ እንዲሁም በዓቂዳቸውና በእውቀታቸው ታማኝ ከሆኑ ዓሊሞች (እውቀት) መያዝን ነው።

ከነዚያ እውነትን በባጢል ከሚያደባልቁና እውነትን የሚያውቁት ከመሆናቸውም ጋር የሚደብቁ ከሆኑ መጥፎ ሰባኪ (ዳዒዎች) መጠንቀቅን!፣ አልያም ከነዚያ እውነትን እነሱ የማያውቁት ሆነው ሳለ ከሚሞግቱ መሀይማን መጠንቀቅን ነው የምንመክረው!!። ምክንያቱም እነሱ ከሚያሳምሩት የበለጠ አበላሾች ናቸው!።» [አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ ዐን አስኢለት አልመናሂጅ አልጀዲዳ 257-258]
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join በማድርግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
1.0K viewsأبو حموية, 08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 14:24:33 ትልቁ ዓሊም አህመድ አነጅሚይ አሉ :

" እወቅ:ላ ኢላሀ ኢላ አላህ (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ያለ አካል እርሱ ከአላህ ውጭ ሌላን እየተማፀነ ከአላህ ውጭ ማንም ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ ማይችለውን ነገር ከእርሱ ጥቅም ያስገኛል ጉዳትም ይከላከላል ብሎ እየከጀለ ፤ ወይም ለእርሱ እየተሰለ ፤ ወይም በስሙ እያረደ ፤ ወይም ለጭንቁ እየጠራው ፤ ጥገኝነት እየጠየቀው ከሆነ ይህ አካል ትልቁን ሺርክ (ማጋራት) አሻርኳልበአላህ አንድነት ከሃዲ ነው። ምንም ያክል ቢሰግድ ፣ ቢፆም ፣ ሙስሊም እንደሆነ ቢሞግትም ፣ (ላ ኢላሀ ኢላ አላህ) እያለ በቀን ሰባ ሺ ጊዜ ቢደጋግምም። ከአላህ ውጭ በሚመለኩ ሁሉ እስከሚክድ ድረስ ይህ ንግግሩ ብቻውን በፍፁም አይጠቅመውምና።"

https://t.me/Menhaj_Alwadih
1.3K viewsأبو حموية, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:28:54 የሙብተዲዖች ተውበት ሲበጠር

በማረሳሳትና በማዘናጋት ሳይሆን
# ከጥመታቸው በተሟላ ተውበት ይመለሱ
# ያበላሹትን ያስተካክሉ
# የደበቁትና ያለባበሱትን ያብራሩ

ልብ ያለው ልብ ይበል

https://t.me/Abuhemewiya
803 viewsأبو حموية, edited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:28:34ከውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው

ድንቅ ምክር ከታላቁ ኢትዮጵያዊ
ዓሊም አንደበት

ከሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ

《ሰዎች የአህሉሱና ወልጀመዐን መንገድ ከመከተልና የዚህ ኡማህ ምርጥ ቀደምቶችን (ሰለፎች) አርኣያ ከማድረግ አንፃር ብዙ አይነት ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ በውስጡ አርኣያ አድርጎ የሚከተላቸው አለ። ማለት ከአቂዳህ (ከውስጣዊ እምነት) አንፃር ጤናማ ኢዕቲቃድ (እምነት) ይይዛሉ።ነገር ግን ውጫዊ ገፅታዎችን አስተካክሎ ማቆም ያቅታቸዋል።

ሱናን (የመልዕክተኛውን ፈለግ) በግልፅ አጥብቆ መያዝ ያቅታቸዋል የአህሉሱናንም ተግባር አይተገብሩም።
እንዲያውም በውጫዊ ተግባራቸው አህሉሱናን ከሚፃረሩ አካለት ጋር ይስማማሉ።ለምሳሌ እነርሱ በአቂዳቸው (በአቋማቸው) ሰለፊይ ነን ብለው የሚያምኑ ሆነው ነገር ግን በአደረጃጀት ፣ በተግባርና በእንቅስቃሴ ሌሎች ጀማዓዎችን (አንጃዎችን) ይስማማሉ


ለዚህ እንደምክንያት የሚጠቀሙት ደግም ሰለፊዮችን ቀዝቃዛ ሰዎች ናቸው ፤ ንቅናቄያዊ አይደሉም ፤ ነሻጣ (ተነሳሽነት) የላቸውም በሚል ሙግት ነው። እንዲህም ይላሉ"እነርሱን በአቂዳ መመሳሰል በቂ ነው። ምክንያቱም እነርሱ በእምነታቸው የተረጋጉና የሚያጣጥሙ ናቸው አቂዳቸው ጤናማ ነውና "። ይህቺ በጣም ትልቅ ምስክርነት ናት።ነግር ግን እነርሱ በንቅናቄ ፣ በአደረጃጀትና በተነሳሽነት እንደሌሎች አይደሉም ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ራሳቸውን በአቂዳ ሰለፊይ በውጫዊ እንቅስቃሴና አደረጃጀት ደግሞ ንቅናቂያዊ እንደሆኑ ይሞግታሉ። ይህም ግልፅ ስህተት (ጥፋት) ነው።

ሰው ውስጡ ውጩን የሚፃረርና ውጩም ውስጡን የሚፃረር ከሆነ ይህች የኒፋቅ ምልክት ናት። ትክክለኛ የቀደምቶችን መንገድ ለመያዝ ውስጣዊ እምነትህ (አቂዳህ) ብቻ አይበቃም። ከሰለፎች መንገድ አንተ በተግባር እያጎደልክና በአፈፃፀም እየተፃረርካቸው ነው።

የአቂዳህ ጤናማነት ወደ ተግባር ሊጠራህ የግድ ነው። በጥሩ ማዘዝ ፣ ከመጥፎ መከልከል ፣ ለአላህ ባሮች ተማኝነትና ፣ ለእርቅ መትጋት ይህ ነው ኢስላማዊ ተግባር። አንተ ግን ይህን ተግባር ሰዎችን እንደሚያሸሽ አና እንደሚበታትን አስበህ እንደ ሌሎቹ ጀመዓዎች ሰዎችን ለመቀላቀል (ለመደመር) እና ለማጃጃል ትሞክራለህ። ወይም ያለ ምንም ተግባር አመፅን በማደረጀት እንደ አርባዎቹ ትንቀሳቀሳለህ።የሆነ የተደራጀ ጀመዓ ስለሆነ ብቻ ያንን አደረጃጀት አጥብቀህ ትይዛለህ። ስለዚህ በህጋቸውና በእቅዳቸው መሰረት አየሰራህ ሰለፎችህን በተግባር መከተልህን ትተዋለህ። አንተም በአቂዳ እስከተከተልካቸው ድረስ በውጫዊ ተግባርህ ብትፃረራቸው እንደማይጎዳህ ትገምታለህ። ይህ የለየለት ስህተት ነው። የተሳሳት እይታም ነው።

በውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው። በውስጥ ከአቂዳ አንፃር፤ ከውጭ ደግሞ ከተግባር አንፃር ሰለፊይ ልትሆን የግድ ነው። ተግባርህ ግዴታ ነው።

ከዚህ በላይ ደግሞ ሌሎቹ አንጃዎች እንደሚያምኑት ኢስላማዊ ስራ በመከናወን ውስጥ ለመምከር ፣ ለማቅናት ፣ በጥሩ ለማዘዝ ፣ከመጥፎ ለመከልከል ፣ በቻልከው ልክ ለማስታረቅ መሞከር ለዚህ ዘመን የማይበጅ ነው ብለህ ካመንክ

(ነገሩ የከፋ ነው)። እነርሱ አንደሚያመካኙት ይህ ሰዎችን ያለያያልና ሰዎች በኢስላም ጥላ ስር ፤ በኢስላም ታፔላ (የማስታወቂያ ሰሌዳ) ስር ብቻ ያለተግባር መሰባሰባቸው የግድ ነው ብለህ ካመንክማ ይህች ቢደዓ ናት። የከፋችም ጥመት ናት።

ሰዎችንም ከእውነተኛው የኢስላም ግንዛቤ ማራቅ ነው። ሰዎችንም ማታለል (ማጭበርበር) ነው። ከዚያም ማህበረሰቡ ጃሂል (አላወቂ) እና ለንቅናቄ መሪዎች ጭፍን ተከታይ ሆኖ ይቀራል።

ተጠንቀቅ !! አንተ በጤናማ አቋምና የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመረዳትና በመተግበር ላይ አላህ ያደለ አካል ሆይ : ተጠንቀቅ እራስህን እንዳትበታትን። ግማሽህን ከሰለፊዮች ጋር አድረገህ ሌላው ግመሽህን ደግሞ ከንቅናቄ ቡድኖች ጋር አታድርግ። ለመሆኑ ምንድነው ወደዚህ የሚገፋፋህ!?

ሙስሊም ግልፅ ሊሆን ግድ ነው። መልክን መቀያየር ፣ መተጣጠፍና መከረባበት ደግሞ ከኒፋቅ ምልክቶች ውስጥ ነው። ሙስሊም ውስጡና ውጩ ሁሉ አንድ አይነት ነው። አንደዚሁ ነው።

ነገር ግን ከዚህም ጋር ሸይኹል ኢስላም እንደሚናገረው " እነዚያ አህሉሱና ወልጀማዐህን በውስጣቸው የሚገጥሙና ውጫቸውን ደግሞ ማስተካከልና ማቅናት የማይችሉ እነርሱም ከሱና ተፃራሪዎች አደጋ ሰላም አይሆኑም።" ከእነርሱ ሰላም ለመሆን እየሞከርክ በሙጃመላህ ብትመሳሰላቸውም አንኳ ሰላም የለህም። አቂዳህን (አቋምህን) እስካወቁ ድረስ አንተ ሰላም አትሆንም።

ስለዚህ እራስህን ማከፋፈል ይቅርብህ።
ቀጥተኛው መስመር ላይ ፅና። ምክንያቱም አንተ በየትኛውም መልኩ (ከተንኮለቸው) ሰላም አትሆንምና።》


ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) ሀፊዘሁሏህ

በቀጥታ ከድምፃቸው ለማዳመጥ
https://t.me/AbuImranAselefy/3239

በአረብኛ ፅሁፉን ለማግኘት
https://t.me/AbuImranAselefy/3240

በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በድምፅ [ኦዲዮ] ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበትን ፋይል ለማግኘት
➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/3246
578 viewsأبو حموية, 09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:44:36 ማስታወሻ

በቅርብ ተለቆ የነበረውን ማስታወቂያ እኔ አይደለሁም ሌላ ሰው ሳያስበው በስህተት እንደለቀቀው ነግሮኛል።

ከሙመይዓዎች ጋር ካልተላቀቀ ሰው ጋር በፍፁም አልተባበርምና አጥፍቼዋለሁ።


በውስጥ መስመር ላስታወሳችሁኝ ሁሉ አላህ መልካም ጀዛችሁን ይክፈላችሁ።

ሸምሱ ጉልታ ዐብዱረህማን (አቡ ሀመዊየህ)
877 viewsأبو حموية, edited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ