Get Mystery Box with random crypto!

የሱንና ዓሊሞቻችንን ምክር አጥብቀን እንያዝ!! ——— ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ቢን ፈውዛን | 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የሱንና ዓሊሞቻችንን ምክር አጥብቀን እንያዝ!!
———
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ብለዋል:-
«ነፍሲያችን እና ወንድሞቻችንን የምንመክርበት ነገር፣ አላህን በመፍራት ላይና በደጋግ ቀደምቶች መንገድ በመጣበቅ!፣ እንዲሁም ከቢድዓና ከሙብተዲዓዎች መጠንቀቅን፣ ትክክለኛውን ዓቂዳንና የሚቃረነውን በማስተማር ላይ ትኩረት መስጠትን፣ እንዲሁም በዓቂዳቸውና በእውቀታቸው ታማኝ ከሆኑ ዓሊሞች (እውቀት) መያዝን ነው።

ከነዚያ እውነትን በባጢል ከሚያደባልቁና እውነትን የሚያውቁት ከመሆናቸውም ጋር የሚደብቁ ከሆኑ መጥፎ ሰባኪ (ዳዒዎች) መጠንቀቅን!፣ አልያም ከነዚያ እውነትን እነሱ የማያውቁት ሆነው ሳለ ከሚሞግቱ መሀይማን መጠንቀቅን ነው የምንመክረው!!። ምክንያቱም እነሱ ከሚያሳምሩት የበለጠ አበላሾች ናቸው!።» [አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ ዐን አስኢለት አልመናሂጅ አልጀዲዳ 257-258]
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join በማድርግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa