Get Mystery Box with random crypto!

የሀገራችን ሙመይዓዎች ልብ ብሎ ላስተዋለ ሁሉ ከሚታዩ የሙመይዓዎች ጥመቶች ውስጥ: 5 ጥንድ ጥፋቶ | 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የሀገራችን ሙመይዓዎች
ልብ ብሎ ላስተዋለ ሁሉ ከሚታዩ የሙመይዓዎች ጥመቶች ውስጥ:
5 ጥንድ ጥፋቶች ለምሳሌ

ያፈረሱት እና የገነቡት
ለዚህ ዘመን አይበጅም በሚል አዳዲስ በፈበረኳቸው መርሆዎች መንሃጅ አሰለፍን ንደው ህንፃ ገንብተዋል።ከሙብተዲዖች ጋር ለመኗኗር ሲሉ ሀቅን ደብቀው ቀብረዋል።

ያንቋሸሹት እና ያወደሱት
ለተውሂድና ሱነህ የሚተጉ ሰለፊዎችን አንቋሸው ሙብተዲዖችን አወድሰዋል። ዑለማዎችን ጭምር "ወሰን አላፊ ፣ አቡጀህል ፣ የረድ ጉረኛ ፣ የእንጨት ሽበት ፣ እብድ ወዘተ " እያሉ በተቃራኒው ደግሞ ግልፅ የወጡ አጥማሚዎችን አወድሰዋል ፤ ጥብቅና ቆመውላቸዋል ።
ሰለፊዮችን ንቀው አንቋሸው ሙብተዲዖችን ክበው አወድሰዋል።

የበተኑት እና የሰበሰቡት
እንደ አንድ ልብ የሚዋደዱ የነበሩ የሀቅ ጀመዓዎችን አነታርከው በትነዋል።በዚህም ከጠማሞች ድጋፍና ውዳሴን አግኝተዋል። የሱነህ መድረሳዎችን በትነው የሂዝቢየህ ስብስቦችን አፍርተዋል።

የተጣሉት እና የተወዳጁት
ከሙሽሪኮች ጋር ሳይቀር ተደራድረው ፣ ከሙብተዲዖችም ጋር ተቀራርበው ልዩነታቸውን አጥብበው ሊተባበሩ ተስማምተዋል። ሰለፊዮችን ግን ለማናገር በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ምክንያት እየደረደሩ ሰንበተው፣ በንቀት አልፈው ጠላትነታቸውን አሳውቀዋል።

የከሰሩት እና ያተረፉት
ብዙ ከልባቸው ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ሰለፊዮችን ፣ አስተማሪ የነበሩ ኡስታዞችና ትልልቅ ዑለማወችን በየቦታው ከስረዋል ያተረፉትን ግን አላውቅም። የሂዝቢይ ቲፎዞ ማብዛት ፣ ጭፍን ሙሪዶችን መኮትኮት እና በጥቅማጥቅም የተለጎሙ ሙለቢሶችን መያዝ እንደሆነ በራሱ ኪሳራ ነው።

እንደዚህ ነገሩ ተገላባብጦባቸዋል።

{ رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا }.
ጌታችን ሆይ: ቅንኑን ከመራሀን በኋላ ልቦቻችንን አታጣምብን።

 " اللَّهُمَّ مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ "
ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው አላህ ሆይ: ልቤን በዲንህ ላይ አፅናት።

ሸምሱ ጉልታ
https://t.me/Abuhemewiya