Get Mystery Box with random crypto!

《 ከውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው 》 ድንቅ ምክር ከታላቁ ኢትዮጵያዊ ዓሊም አ | 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

ከውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው

ድንቅ ምክር ከታላቁ ኢትዮጵያዊ
ዓሊም አንደበት

ከሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ

《ሰዎች የአህሉሱና ወልጀመዐን መንገድ ከመከተልና የዚህ ኡማህ ምርጥ ቀደምቶችን (ሰለፎች) አርኣያ ከማድረግ አንፃር ብዙ አይነት ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ በውስጡ አርኣያ አድርጎ የሚከተላቸው አለ። ማለት ከአቂዳህ (ከውስጣዊ እምነት) አንፃር ጤናማ ኢዕቲቃድ (እምነት) ይይዛሉ።ነገር ግን ውጫዊ ገፅታዎችን አስተካክሎ ማቆም ያቅታቸዋል።

ሱናን (የመልዕክተኛውን ፈለግ) በግልፅ አጥብቆ መያዝ ያቅታቸዋል የአህሉሱናንም ተግባር አይተገብሩም።
እንዲያውም በውጫዊ ተግባራቸው አህሉሱናን ከሚፃረሩ አካለት ጋር ይስማማሉ።ለምሳሌ እነርሱ በአቂዳቸው (በአቋማቸው) ሰለፊይ ነን ብለው የሚያምኑ ሆነው ነገር ግን በአደረጃጀት ፣ በተግባርና በእንቅስቃሴ ሌሎች ጀማዓዎችን (አንጃዎችን) ይስማማሉ


ለዚህ እንደምክንያት የሚጠቀሙት ደግም ሰለፊዮችን ቀዝቃዛ ሰዎች ናቸው ፤ ንቅናቄያዊ አይደሉም ፤ ነሻጣ (ተነሳሽነት) የላቸውም በሚል ሙግት ነው። እንዲህም ይላሉ"እነርሱን በአቂዳ መመሳሰል በቂ ነው። ምክንያቱም እነርሱ በእምነታቸው የተረጋጉና የሚያጣጥሙ ናቸው አቂዳቸው ጤናማ ነውና "። ይህቺ በጣም ትልቅ ምስክርነት ናት።ነግር ግን እነርሱ በንቅናቄ ፣ በአደረጃጀትና በተነሳሽነት እንደሌሎች አይደሉም ብለው ያምናሉ። ስለዚህ ራሳቸውን በአቂዳ ሰለፊይ በውጫዊ እንቅስቃሴና አደረጃጀት ደግሞ ንቅናቂያዊ እንደሆኑ ይሞግታሉ። ይህም ግልፅ ስህተት (ጥፋት) ነው።

ሰው ውስጡ ውጩን የሚፃረርና ውጩም ውስጡን የሚፃረር ከሆነ ይህች የኒፋቅ ምልክት ናት። ትክክለኛ የቀደምቶችን መንገድ ለመያዝ ውስጣዊ እምነትህ (አቂዳህ) ብቻ አይበቃም። ከሰለፎች መንገድ አንተ በተግባር እያጎደልክና በአፈፃፀም እየተፃረርካቸው ነው።

የአቂዳህ ጤናማነት ወደ ተግባር ሊጠራህ የግድ ነው። በጥሩ ማዘዝ ፣ ከመጥፎ መከልከል ፣ ለአላህ ባሮች ተማኝነትና ፣ ለእርቅ መትጋት ይህ ነው ኢስላማዊ ተግባር። አንተ ግን ይህን ተግባር ሰዎችን እንደሚያሸሽ አና እንደሚበታትን አስበህ እንደ ሌሎቹ ጀመዓዎች ሰዎችን ለመቀላቀል (ለመደመር) እና ለማጃጃል ትሞክራለህ። ወይም ያለ ምንም ተግባር አመፅን በማደረጀት እንደ አርባዎቹ ትንቀሳቀሳለህ።የሆነ የተደራጀ ጀመዓ ስለሆነ ብቻ ያንን አደረጃጀት አጥብቀህ ትይዛለህ። ስለዚህ በህጋቸውና በእቅዳቸው መሰረት አየሰራህ ሰለፎችህን በተግባር መከተልህን ትተዋለህ። አንተም በአቂዳ እስከተከተልካቸው ድረስ በውጫዊ ተግባርህ ብትፃረራቸው እንደማይጎዳህ ትገምታለህ። ይህ የለየለት ስህተት ነው። የተሳሳት እይታም ነው።

በውስጥም ከውጭም ሰለፍይ ልትሆን ግዴታ ነው። በውስጥ ከአቂዳ አንፃር፤ ከውጭ ደግሞ ከተግባር አንፃር ሰለፊይ ልትሆን የግድ ነው። ተግባርህ ግዴታ ነው።

ከዚህ በላይ ደግሞ ሌሎቹ አንጃዎች እንደሚያምኑት ኢስላማዊ ስራ በመከናወን ውስጥ ለመምከር ፣ ለማቅናት ፣ በጥሩ ለማዘዝ ፣ከመጥፎ ለመከልከል ፣ በቻልከው ልክ ለማስታረቅ መሞከር ለዚህ ዘመን የማይበጅ ነው ብለህ ካመንክ

(ነገሩ የከፋ ነው)። እነርሱ አንደሚያመካኙት ይህ ሰዎችን ያለያያልና ሰዎች በኢስላም ጥላ ስር ፤ በኢስላም ታፔላ (የማስታወቂያ ሰሌዳ) ስር ብቻ ያለተግባር መሰባሰባቸው የግድ ነው ብለህ ካመንክማ ይህች ቢደዓ ናት። የከፋችም ጥመት ናት።

ሰዎችንም ከእውነተኛው የኢስላም ግንዛቤ ማራቅ ነው። ሰዎችንም ማታለል (ማጭበርበር) ነው። ከዚያም ማህበረሰቡ ጃሂል (አላወቂ) እና ለንቅናቄ መሪዎች ጭፍን ተከታይ ሆኖ ይቀራል።

ተጠንቀቅ !! አንተ በጤናማ አቋምና የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመረዳትና በመተግበር ላይ አላህ ያደለ አካል ሆይ : ተጠንቀቅ እራስህን እንዳትበታትን። ግማሽህን ከሰለፊዮች ጋር አድረገህ ሌላው ግመሽህን ደግሞ ከንቅናቄ ቡድኖች ጋር አታድርግ። ለመሆኑ ምንድነው ወደዚህ የሚገፋፋህ!?

ሙስሊም ግልፅ ሊሆን ግድ ነው። መልክን መቀያየር ፣ መተጣጠፍና መከረባበት ደግሞ ከኒፋቅ ምልክቶች ውስጥ ነው። ሙስሊም ውስጡና ውጩ ሁሉ አንድ አይነት ነው። አንደዚሁ ነው።

ነገር ግን ከዚህም ጋር ሸይኹል ኢስላም እንደሚናገረው " እነዚያ አህሉሱና ወልጀማዐህን በውስጣቸው የሚገጥሙና ውጫቸውን ደግሞ ማስተካከልና ማቅናት የማይችሉ እነርሱም ከሱና ተፃራሪዎች አደጋ ሰላም አይሆኑም።" ከእነርሱ ሰላም ለመሆን እየሞከርክ በሙጃመላህ ብትመሳሰላቸውም አንኳ ሰላም የለህም። አቂዳህን (አቋምህን) እስካወቁ ድረስ አንተ ሰላም አትሆንም።

ስለዚህ እራስህን ማከፋፈል ይቅርብህ።
ቀጥተኛው መስመር ላይ ፅና። ምክንያቱም አንተ በየትኛውም መልኩ (ከተንኮለቸው) ሰላም አትሆንምና።》


ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) ሀፊዘሁሏህ

በቀጥታ ከድምፃቸው ለማዳመጥ
https://t.me/AbuImranAselefy/3239

በአረብኛ ፅሁፉን ለማግኘት
https://t.me/AbuImranAselefy/3240

በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በድምፅ [ኦዲዮ] ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠበትን ፋይል ለማግኘት
➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/3246