Get Mystery Box with random crypto!

የ ቃል ደብዳቤዎች💌

የቴሌግራም ቻናል አርማ yekaldebdabewoch — የ ቃል ደብዳቤዎች💌
የቴሌግራም ቻናል አርማ yekaldebdabewoch — የ ቃል ደብዳቤዎች💌
የሰርጥ አድራሻ: @yekaldebdabewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 530
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ 👇
ደብዳቤዎችን💌
ወጎችን📃
ግጥሞችን📝
የተለያዩ መፅሐቶችን📚 ያገኛሉ፡፡
ሀሳብ, አስተያየት እንዲሁውም እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት ደብዳቤ ካለ
@Hebestina ይላኩልን፡፡ ቻናሉ ላይ እንለቃለን...

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-07 09:05:12 የሆነ ቦታ ላለኸው ፍቅሬ
_______________________
መሽቷል..... ግን አልገፋበትም..... ነፋሱ ስልት እየቀያየረ ዛፎችን ያሽኮረምማል.... ውቧ ጨረቃ የምድርን እርቃን ገላ ትስማለች..... እዛ ማዶ ጥሻው ስር ሁለት ድመቶች ፍቅር ሊሰሩ ይዘጋጃሉ.....ከፊቴ ሁለት ጥንዶች በነፍስም በስጋም ተሳስረው ጎዳናው ላይ ያብሮነት ዳናቸውን ያሳርፋሉ...... ምሽቱ አንዳች ፍቅር ፍቅር የሚሸት ድባብ ሰፍፎበታል..... በዛ መሀል..... እኔ.....ነጭ ልብስ ላይ ጠብ እንዳለች ጥቁር ቀለም እዚህ ድባብ ላይ ይሆንኩ መሰለኝ.. አለ አይደል ቆንጆ ፊት ላይ እንደወጣች ትንሽ ብጉር! .... ሁሉም ሞልቶ እኔ ብቻ ጎድያለው ... ያንገት ሹራቤ አቻውን ፍለጋ ይመስል ካንገቴ ወደኊላ ይሸሻል..... እጆቼ ሌላ እጆች መሀል መገኘት ሲኖባቸው ኪሴ ውስጥ ተደብቀዋል....... አይኔ የማናቸው ማዕድ ላይ ማረፍ እንዳለበት ግራ እንደገባው በቅናትና ምኞት ተኩሎ የበይ ተመልካች ሆኗል.... እግሬ በጎዳናው ላይ የሚያጋጥመውን እንቀፋት ለብቻው እየተጋፈጠ ያዘግማል................ ብቸኛ ነኝ.... ሰዎች የሚዘረጓቸው የዝምድና ገመዶች የተበጠሱብኝ... ከትልቁ ገመድ 'ቤተሰብ' አንስቶ እስከ ጥቃቅኖቹ ክሮች 'አጭብጫቢ' ድረስ!.... የዛሬው እለት ደግሞ ዙሪያ ገባው ፈራጅ እና ምስክር ሆኖ ብቸኝነቴን ይባስ ያጎላበት እለት ነው ሚመስለው...
ጓደኞች ስቀርብ 'ሙድሽ ደስ አይልም አንዳች የሚከብድ ነገር አለሽ' ይሉኛል.... ስቆ ማሳቁን፣ተጫውቶ መጫወቱን፣ ማማለሉንና መሽኮርመሙን ከየት ተምሬ ልቻልበት?( ቻልኩበት! አለች ኩኩ ሰብስቤ) ከናቴ እንዳልል? ... የት ያሳደገቺኝን? ካባቴ? እሱስ መች ነበረ? እድገቴ የማሳደግያ ድርጅት ውስጥ ሆኖ!
ብዙ ግዜ በብቸኝነት ተወግቻለው... የዛሬው ግን ተለየብኝ... ሆድ አስባሰኝ.... የእንባዬን አገልግል በቀላሉ አስፈታኝ,,,,,,, በመሀል ካንድ ባጃጅ አፈትልኮ የወጣው ድምፅ ይባስ ሁኔታዬን አባባሰው....
.
.
"እስኪያገናኘን እንጅ ግዜና ቦታ
ለኔ የምትሆን የሄዋን ዘር ከቶ መች ጠፍታ
አለች አለች አንድ ቦታ
የኔ ስጦታ"
..
..
የወንድሙ ጅራ ዘፈን! ዘፈኑን ከነፍሴ ሰማውት... ከዚ በፊት ሺ ግዜ ሰምቼዋለው እንደዛሬ ግን አላዳመጥኩትም
....

"ለግዜው እንጅ ብሆን ከርታታ
አገኛታለው የማታ ማታ"
፨፨
፨፨
'ለምን የኔ "ለግዜው" ዘልአለም ሆነ? ለምን የኔ "የማታ ማታ" እንደምፅአት ቀን መምጫው ራቀ?' ይጠይቃል አንጎሌ... መልስ ግን .......
፨፨
፨፨
"አታጣድፉኝ ጥድፊያ አሎድም
ለኔ ያሰባት የትም አቴድም"
...
......
ዘፈኑኮ ርቋል..ግን ውስጤ የቀረው ድምፅ በ10እጥፍ ተባዝቶ ይሰማኛል.

"እኔ ቸኩዬ ነው? ወይስ እሱ ዘግይቶ? ማነው ተጠያቂው?? እኔ?.... ስላልታገስኩ?... እሱ?... ስለዘገየ?? ወይስ ፈጣሪ? እንዲ ስሆን እያየ ዝም ስላለ?....." ይጠይቃል ዳግም አንጎሌ..........
"ተረጋጊ! የእግዜር Timing ፍፁም ልክ ነው.. ያባይሆን ኖሮማ ሁሉም ያለግዜው እየሆነ አስቀያሚ ይሆን ነበር!" ይመልሳል ልቤ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ እውነቱን ይሆን??????

... የት ነህ ግን? ምን እየሰራህ ነው? መቼ ነው ምትመጣው?...... መልስ የሌላቸው የዘወትር ጥያቄዎቼ.... እርግጠኝነት የጎደላቸው የሁሌ ሀሳቦቼ.....
ይሄኔኮ አንዲት እንስት አቅፈህ "ዘላለም አብረን ነን" እያልካት ይሆናል.... ምናልባትም የድመቶቹን ድርጊት እየደገምክ ይሆናል.... ህምም! ....................

.... መቼ ነው ግን ውዴ.... ጨረቃን ምስክር አድርገህ እንደማትለየኝ የምትምልልኝ፣ አርፍደህ መጥተህ ይቅርታ የምትጠይቀኝ፣ ናፍቀኸኝ የምታስለቅሰኝ፣ እጄን ከኪሴ አውጥተህ በጆችህ የምታሞቀኝ፣ በጨረቃና ምድር የቀናውትን መልሰህ እነሱኑ የምታስቀናልኝ? .... መቼ ነው ፍቅሬ ሆይ.............................

ተፃፈ By aggie

@yekaldebdabewoch
511 viewsKal--kidan, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:05:12 ወንድሜ.... ሴት ልጅን  መውደድ አለብህ.... ሴት ልጅ ክብር ይገባታል!!...  ሴት ልጅ ማለት.... 9 ወር ሙሉ በማህፀኗ... ምናምን እያልኩ ላዝግህ አልፈልግም።   ግን ሴት ልጅ የውነት የምር ክብር ይገባታል።
አስበኸዋል....    ማንነቷን  ነው አሳልፋ የምትሰጥህ... ላንተ ስትል ትምርቷን ልታቆም ሁላ ትችላለች.... ክብሯን አሳልፋ ልትሰጥህ ሁላ ትችላለች....  ታገባታለህ....   በሚሰቀጥጥህ ህመም ውስጥ አሳልፋ ልጅ ትሰጥሃለች።  ሚገርመው ነገር እንዲህም ሆና የሚወለደው ልጅ ባንተ ስም ነው ሚጠራው። አንተን ብላ ቤተሰቦቿን ትታ ነው አንተ ቤት የምትመጣው።

ስለዚ ፕሊስ ክብር ይኑርህ... ደግሞ ኮ ስኬታማ ወንድ ታደርግሃለች። አስታውስ ደግሞ ከያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ ጀርባ ስኬታማ ሴት ደግሞ አትጠፋም።   ከዚ አንፃር  በቅርቡ የሆነ ፅሁፍ አንብቤ ነበር እና  እሱን ላንሳ።

አዞዎች በብዛት የሚገኙበት  ሃይቅ ለይ አንድ   የቱሪስት  ቡድን   በጀልባ    እየቀዘፈ አዞዎቹን ይሾፉዋቸዋል።      ልክ አዞዎቹ የሚበዙበት  ቦታ ሲደርሱ  ከቱሪስቶቹ መሃከል ሃብታም የሚባለው እንዲ አለ ።   "ከናንተ መሃከል  እዚ ሃይቅ ውስጥ ዘሎ ገብቶ   እየዋኘ ዳርቻው ጋር የሚደርስ ካለ አንድ ሚሊዮን ብር እሰጠዋለው።"
ሶዬው  ይሄን ቻሌንጅ  ዲክሌር ቢያደርግም  አዞዎቹ እንደዛ ቱሪስቶቹን እያዩ ምራቃቸውን እየዋጡ እየታየ  ሃይቁ ውስጥ ገብቶ የሚዋኝ ሰው ጠፋ። ቡሃላ ግን አንዱ   ዘሎ ገባ።   ....  አዞዎቹም ተከተሉት።     ኪዳነ ምህረት በለተ ቀኗ  ረዳችውና አዞዎቹ ሳይደርሱበት  እየዋኘ  ወጣ።
ሚሊዮኗንም አፈፍ አደረጋት።   ባንዴ ወደ ስኬታማ ወንድ ተቀየረ ማለት ነው።

ቡሃላ ለይ ከባለቤቱ ጋር  አልጋ ወደ ያዙበት ሆቴል የሄዳሉ።   ሚስቱም ትጠይቀዋለች። 
" እና ፍቅር  ምን ተሰማህ... ሚሊዬነር ስለሆንክ..?"
"  እንዴ... ደስታ 'ንጂ..... ግን ማን እንደ ገፈተረኝ ማወቅ ፈልጋለው። "
" ውይ  ፍቅር አላወክም እንዴ...  እኔ ኮ ነኝ "
እና ወንድሜ ከዚ ታሪክ ልንረዳ የምንችለው  ከያንዳንዱ ስኬታማ  ወንድ ጀርባ ስኬታማ ሴት አለች።

ምትኩ

@yekaldebdabewoch
367 viewsKal--kidan, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:05:12

፦)
ሁልጊዜም እንደ ዛሬው ነው.....አዲስ ነገር የለም ....አሮጌው በአዲስ ቀን ይተካል ...የመሸው ፅልመት በፀሀይ ብርሀን ይበራል ...ትላንት ዛሬን ይተካል እንጂ.....ምንም ለውጥ የለም......ምንም አዲስም የለም ...ምንም ....ግን ምናልባት የኔ አዲስ ነገር አንተ ስለሆንክ ይሆን?....እንጃ አላውቅም

አንዳንዴ ግን ልክ ያልሆኑ ነገሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው አይደል.......በስህተቴ ውስጥ ያገኘሁህ ልክነቴ አንተ ነበርክ...በልክነቴም ያጣሁህ ስህተቴም አንተው ነህ ......

ታውቃለህ ...ረሳሁህ ብዬ ካመንኩ ከብዙ ጊዜያት ቦኋላ ነው ያስታወስኩህ .....ጠላሁህ ብዬ ከነገርኩህ ከብዙ ሂደቶች ቦኋላ ነው ፍቅርህ የበረታብኝ ......የእውነት ህይወቴ ናፍቀኸኛል ...ልክ እንዳልሆነ አውቃለሁ ግን አልቻልኩም የምር ከታገስኩት በላይ ነበር ባንተ ተስፋ የቆረጥኩት ግን አልሆነም .......አዲስ ነገር የለውም ባልኩት ማንነቴ ውስጥ ዳግም አሰብኩህ...

አሁን ላይ ግን ምን እንደሚቆጨኝ ታውቃለህ .....ተሸናፊዋም.... ጥፋተኛዋም እኔ መሆኔ ብቻ ....ለማሸነፍ ሳይሆን ላለመሸነፍ ስኳትን ነበር የተሸነፍኩት......ሀቀኛ ሳይሆን ከሃዲ ላለመሆን ስጥር ነበር ጥፋቴን ያገኘሁት......
ምናልባት ህይወቴ .....ማንነቴ አስቀይሞህ ...እኔነቴ አስጠልቶህ..እውነታዬ አስከፍቶህ እና ልቤ ጎድቶህ ይሆናል .........የእውነት ለዛም ደግሞ በጣም ይቅርታ ....

ህይወቴ ይቅርታ ስልህ ግን ጥፋተኝነቴ ተሰምቶኝ አልያም ከልቤ አዝኜ እንዳይመስልህ ....ታውቃለህ አይደል?.. ላለፈባቸው እና እኛነታችንን ላስረሱን ነገሮች አዝኜ እንደማላውቅ ....ለትላንት ተግባሬ እና ላለፈው ህይወቴ እንደማልቆጭ........አዎ ህይወቴ አንተ ትላንትናዬ ነህ.....ግን ይቅርታ እሺ .....ላለፈው ሳይሆን ለሁልጊዜው ...ለትላንቱ ሳይሆን ለዛሬው ጥፋቴ ....ይቅርታ.....

* በስህተቴ ውስጥ ያገኘሁህ ልክነቴ አንተ ነበርክ*

ፊያሜታ

@yekaldebdabewoch
345 viewsKal--kidan, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:05:12 ቆምያለዉ

ከተለያየን ግን ምን ያህል ጊዜ አለፈ....ቀናት ወራት ወይንስ ደግሞ አመታት አካልህ ከራቀኝ ምን ያህል ጊዜያት ነጉደው ይሆን? አምሮዬ ማሰብ ተስኖት የሰራ አከላቴ በድን ከሆነኮ ሰነባብቶል....አንተ ከተለየሀኝ አንስቶ አደለም ቀናት እድሜዬን መቁጠር ተስኖኛል ብልህ ማጋነን አይሆንብኝም ለነገሩ አንተን ካጣሁ በሆላ እድሜዬ ቢቆጠር ምንስ ፋይዳ አለው ለኔኮ ሂወቴ ነበርክ በልቤ ወስጥ የነበረን ፅልመት ድል አርገህ የብርሃንን ጮራ ያሳየሀኝ ፋኖሴ

ዳሩ ምን ያረጋል ....ጨክነህ ስትለየኝ በልቤ ያበራሀውን ፋኖስ ሳትራራ ብታጠፋብኝ መራመድ ፈራውኝ ልራመድ ብልስ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ወዴት እጎዛለው መድረሻዬን ሳላቅ ለነገ ተስፋ ሳልሰንቅስ ከወዴት እደርሳለው?
አዎ ቆምያው! ጀርባህን ሰጥተህ ከተለየሀኝ ቦታ አለው! ግና አለሜ ብቻዬን እንዳልመስልህ አብረን ያሳለፍናቸው እነዛ ወርቃማ ቀናቶች ተለይተውኝ አያቁም ደግሜ ልነገርህ አዎ ቆምያለሁኝ! በነዛ ጣፋጭ ትዝታዎቻችን ውስጥ ያለ አንተ ከትሚያለው የዚህ አለም ውጥንቅጡ ሆነ ግርግሩን ከመጤፍ ቆጥሬው አላቅም ምክንያቱም የቆምኩበት ቦታ ሰላም አለ ያለውበት ቦታ አንተ አለህ።

ተፃፈ በelu jaz @Elujaz

@yekaldebdabewoch
310 viewsKal--kidan, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 09:05:12 ​ "ልሂድ ያልከኝ ለታ"

እንዴት ነሽ ስትለኝ ያኔ የመለስኩልህ
ከሌለህ የለሁም ብዬ የነገርኩህ
እንዳትረሳው ብዬ ዛሬም ልድገምልህ

እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለህ የለሁም
አንተ ስላለህልኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
ግን ውዴ ካጣሁክ በህይወት እያለሁ
አልቅሰህ ሳትቀብረኝ በቁሜ ሞታለሁ

እስኪ አስበው ውዴ በቁም ከሞትኩብህ
አላቅፍህ አልስምህ ግጥም አልፅፍልህ
በአካል አላገኝህ ወይ አልደውልልህ
ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልህ

እናቴ አልቅሳ በቁሜ አትቀብረኝ
ወይ ድጋሚ አርግዛ እኔኑ አትወልደኝ
ሞትና ቀብሬ ተራርቀውብኝ
እውነት ያበደ ሰው ሆኜ እቀራለሁ

አንተ የሄድክ እለት ጨለማን እዚሁ አያለሁ
ብርሃንን በትዝታህ ጨለማን በእብደት ውስጥ እመለከታለሁ

ልሂድ ያልከኝ ጊዜ ቀኑ ይጨልማል
ጨረቃ ጠዋት ላይ ፀሀይ ማታ ይወጣል
ተፈጥሮ በኔ ላይ ይገለባበጣል

ውዴ ልሂድ ያልከኝ ለታ
ቀን ላይ እየሞትኩ እኖራለሁ ማታ
አንተኑ እያሰብኩ ሁሌ በትዝታ

ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረህ ጊዜ ምንም እንዳትለኝ
3 ሶስት ፊደል ተናግረህ "ል ሂ ድ" ብቻ በለኝ


@yekaldebdabewoch
325 viewsKal--kidan, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 11:23:35 #Elsita

አንዳንዴ የወደድናቸው መልሰው አይወዱንም…ህይወታችንን የሰጠናቸው ጊዚያቸውን እንኳን አይሰጡንም…ቢሆንም ግን የሆነ ቀን ሌሎች የወደድናቸው መልሰው ይወዱናል…ፈጣሪም ያለ ቀን ጊዚያቸውን ብቻ ሳይሆን እራሳቸውንም እሚሰጡን ይመጣሉ

@yekaldebdabewoch
@yekaldebdabewoch
361 viewsHáŷmî, 08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 07:25:47 Měķåěłįňâ
Ďųďű ýě ĥåñū
..... ţīķ țőķ
..... pĭĉ
.....ćåpűľě
..... műšīĉ
..... vįďěő
......ťěķėŝ
..... vőĩċė
Ĉŕøøś...@Yumdudu
......ŵěłł ĉőmė ďųďű ýė ĥåňű ćĥåňňľě
https://t.me/Mekaelina
358 viewsKal--kidan, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 10:49:58 https://t.me/simeten
398 viewsKal--kidan, 07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 22:16:47 ኦርቶዶክሳዊነት

እምነት ፍቅር ከሆነ ኦርቶዶክስ #ትሰብካለች
እምነት ትዕግሰት ከሆነ እሱን
#ተግብራለች
እምነት በክርስቶስ ፍቅር በማርያም #ትህትና
እንደሆነ የጳውሎስ ሰብከቱ
በእምነት #እንጽና
418 viewsዳዊት, edited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 20:23:33 1 , ኦርቶዶክስ ነኝ የሚልና ማዕተብ ያሰረ በሙሉ ቢያንስ ለ20 ሰው የግዴታ ሼር ያድርግ በሁሉም social media ለተዋህዶ ልጆች ሁሉ መድረስ አለበት። ሀላፊነታችሁን የማትወጡ የተዋህዶ ፀር እናንተ ናችሁ።
2, ልቦና ማስተዋል ያላቹና እንደ አብዛኛው የተዋህዶ ልጆች ቸልተኛ ያሎናችሁ የተዋህዶ ልጆች ደሞ ጦማሩን በአግባቡ አንብቡና አስተዋይ እና ለሀይማኖቱ የሚቀና ሰው የሚደርገውን አድርጉ።
?ማስጠንቀቂያና ማሳሰብያ በምንም ተአምር የተዋህዶ ልጅ ሆኖ ሼር የማያደርግ እንዳይኖር የእውነት ቸልተኞች ሆይ አደራ የኅልውና ጉዳይ ነው በእግዚአብሔር ስም ተይዛችኋል ይህን ባታደርጉ የቤተክርስቲያን ጠላቶቿ ናችሁ !!!
779 views....., 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ