Get Mystery Box with random crypto!

​ 'ልሂድ ያልከኝ ለታ' እንዴት ነሽ ስትለኝ ያኔ የመለስኩልህ ከሌለህ የለሁም ብዬ የነገርኩህ | የ ቃል ደብዳቤዎች💌

​ "ልሂድ ያልከኝ ለታ"

እንዴት ነሽ ስትለኝ ያኔ የመለስኩልህ
ከሌለህ የለሁም ብዬ የነገርኩህ
እንዳትረሳው ብዬ ዛሬም ልድገምልህ

እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለህ የለሁም
አንተ ስላለህልኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
ግን ውዴ ካጣሁክ በህይወት እያለሁ
አልቅሰህ ሳትቀብረኝ በቁሜ ሞታለሁ

እስኪ አስበው ውዴ በቁም ከሞትኩብህ
አላቅፍህ አልስምህ ግጥም አልፅፍልህ
በአካል አላገኝህ ወይ አልደውልልህ
ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልህ

እናቴ አልቅሳ በቁሜ አትቀብረኝ
ወይ ድጋሚ አርግዛ እኔኑ አትወልደኝ
ሞትና ቀብሬ ተራርቀውብኝ
እውነት ያበደ ሰው ሆኜ እቀራለሁ

አንተ የሄድክ እለት ጨለማን እዚሁ አያለሁ
ብርሃንን በትዝታህ ጨለማን በእብደት ውስጥ እመለከታለሁ

ልሂድ ያልከኝ ጊዜ ቀኑ ይጨልማል
ጨረቃ ጠዋት ላይ ፀሀይ ማታ ይወጣል
ተፈጥሮ በኔ ላይ ይገለባበጣል

ውዴ ልሂድ ያልከኝ ለታ
ቀን ላይ እየሞትኩ እኖራለሁ ማታ
አንተኑ እያሰብኩ ሁሌ በትዝታ

ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረህ ጊዜ ምንም እንዳትለኝ
3 ሶስት ፊደል ተናግረህ "ል ሂ ድ" ብቻ በለኝ


@yekaldebdabewoch