Get Mystery Box with random crypto!

ወንድሜ.... ሴት ልጅን  መውደድ አለብህ.... ሴት ልጅ ክብር ይገባታል!!...  ሴት ልጅ ማለት | የ ቃል ደብዳቤዎች💌

ወንድሜ.... ሴት ልጅን  መውደድ አለብህ.... ሴት ልጅ ክብር ይገባታል!!...  ሴት ልጅ ማለት.... 9 ወር ሙሉ በማህፀኗ... ምናምን እያልኩ ላዝግህ አልፈልግም።   ግን ሴት ልጅ የውነት የምር ክብር ይገባታል።
አስበኸዋል....    ማንነቷን  ነው አሳልፋ የምትሰጥህ... ላንተ ስትል ትምርቷን ልታቆም ሁላ ትችላለች.... ክብሯን አሳልፋ ልትሰጥህ ሁላ ትችላለች....  ታገባታለህ....   በሚሰቀጥጥህ ህመም ውስጥ አሳልፋ ልጅ ትሰጥሃለች።  ሚገርመው ነገር እንዲህም ሆና የሚወለደው ልጅ ባንተ ስም ነው ሚጠራው። አንተን ብላ ቤተሰቦቿን ትታ ነው አንተ ቤት የምትመጣው።

ስለዚ ፕሊስ ክብር ይኑርህ... ደግሞ ኮ ስኬታማ ወንድ ታደርግሃለች። አስታውስ ደግሞ ከያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ ጀርባ ስኬታማ ሴት ደግሞ አትጠፋም።   ከዚ አንፃር  በቅርቡ የሆነ ፅሁፍ አንብቤ ነበር እና  እሱን ላንሳ።

አዞዎች በብዛት የሚገኙበት  ሃይቅ ለይ አንድ   የቱሪስት  ቡድን   በጀልባ    እየቀዘፈ አዞዎቹን ይሾፉዋቸዋል።      ልክ አዞዎቹ የሚበዙበት  ቦታ ሲደርሱ  ከቱሪስቶቹ መሃከል ሃብታም የሚባለው እንዲ አለ ።   "ከናንተ መሃከል  እዚ ሃይቅ ውስጥ ዘሎ ገብቶ   እየዋኘ ዳርቻው ጋር የሚደርስ ካለ አንድ ሚሊዮን ብር እሰጠዋለው።"
ሶዬው  ይሄን ቻሌንጅ  ዲክሌር ቢያደርግም  አዞዎቹ እንደዛ ቱሪስቶቹን እያዩ ምራቃቸውን እየዋጡ እየታየ  ሃይቁ ውስጥ ገብቶ የሚዋኝ ሰው ጠፋ። ቡሃላ ግን አንዱ   ዘሎ ገባ።   ....  አዞዎቹም ተከተሉት።     ኪዳነ ምህረት በለተ ቀኗ  ረዳችውና አዞዎቹ ሳይደርሱበት  እየዋኘ  ወጣ።
ሚሊዮኗንም አፈፍ አደረጋት።   ባንዴ ወደ ስኬታማ ወንድ ተቀየረ ማለት ነው።

ቡሃላ ለይ ከባለቤቱ ጋር  አልጋ ወደ ያዙበት ሆቴል የሄዳሉ።   ሚስቱም ትጠይቀዋለች። 
" እና ፍቅር  ምን ተሰማህ... ሚሊዬነር ስለሆንክ..?"
"  እንዴ... ደስታ 'ንጂ..... ግን ማን እንደ ገፈተረኝ ማወቅ ፈልጋለው። "
" ውይ  ፍቅር አላወክም እንዴ...  እኔ ኮ ነኝ "
እና ወንድሜ ከዚ ታሪክ ልንረዳ የምንችለው  ከያንዳንዱ ስኬታማ  ወንድ ጀርባ ስኬታማ ሴት አለች።

ምትኩ

@yekaldebdabewoch