Get Mystery Box with random crypto!

የሆነ ቦታ ላለኸው ፍቅሬ _______________________ መሽቷል..... ግን አልገፋበትም.. | የ ቃል ደብዳቤዎች💌

የሆነ ቦታ ላለኸው ፍቅሬ
_______________________
መሽቷል..... ግን አልገፋበትም..... ነፋሱ ስልት እየቀያየረ ዛፎችን ያሽኮረምማል.... ውቧ ጨረቃ የምድርን እርቃን ገላ ትስማለች..... እዛ ማዶ ጥሻው ስር ሁለት ድመቶች ፍቅር ሊሰሩ ይዘጋጃሉ.....ከፊቴ ሁለት ጥንዶች በነፍስም በስጋም ተሳስረው ጎዳናው ላይ ያብሮነት ዳናቸውን ያሳርፋሉ...... ምሽቱ አንዳች ፍቅር ፍቅር የሚሸት ድባብ ሰፍፎበታል..... በዛ መሀል..... እኔ.....ነጭ ልብስ ላይ ጠብ እንዳለች ጥቁር ቀለም እዚህ ድባብ ላይ ይሆንኩ መሰለኝ.. አለ አይደል ቆንጆ ፊት ላይ እንደወጣች ትንሽ ብጉር! .... ሁሉም ሞልቶ እኔ ብቻ ጎድያለው ... ያንገት ሹራቤ አቻውን ፍለጋ ይመስል ካንገቴ ወደኊላ ይሸሻል..... እጆቼ ሌላ እጆች መሀል መገኘት ሲኖባቸው ኪሴ ውስጥ ተደብቀዋል....... አይኔ የማናቸው ማዕድ ላይ ማረፍ እንዳለበት ግራ እንደገባው በቅናትና ምኞት ተኩሎ የበይ ተመልካች ሆኗል.... እግሬ በጎዳናው ላይ የሚያጋጥመውን እንቀፋት ለብቻው እየተጋፈጠ ያዘግማል................ ብቸኛ ነኝ.... ሰዎች የሚዘረጓቸው የዝምድና ገመዶች የተበጠሱብኝ... ከትልቁ ገመድ 'ቤተሰብ' አንስቶ እስከ ጥቃቅኖቹ ክሮች 'አጭብጫቢ' ድረስ!.... የዛሬው እለት ደግሞ ዙሪያ ገባው ፈራጅ እና ምስክር ሆኖ ብቸኝነቴን ይባስ ያጎላበት እለት ነው ሚመስለው...
ጓደኞች ስቀርብ 'ሙድሽ ደስ አይልም አንዳች የሚከብድ ነገር አለሽ' ይሉኛል.... ስቆ ማሳቁን፣ተጫውቶ መጫወቱን፣ ማማለሉንና መሽኮርመሙን ከየት ተምሬ ልቻልበት?( ቻልኩበት! አለች ኩኩ ሰብስቤ) ከናቴ እንዳልል? ... የት ያሳደገቺኝን? ካባቴ? እሱስ መች ነበረ? እድገቴ የማሳደግያ ድርጅት ውስጥ ሆኖ!
ብዙ ግዜ በብቸኝነት ተወግቻለው... የዛሬው ግን ተለየብኝ... ሆድ አስባሰኝ.... የእንባዬን አገልግል በቀላሉ አስፈታኝ,,,,,,, በመሀል ካንድ ባጃጅ አፈትልኮ የወጣው ድምፅ ይባስ ሁኔታዬን አባባሰው....
.
.
"እስኪያገናኘን እንጅ ግዜና ቦታ
ለኔ የምትሆን የሄዋን ዘር ከቶ መች ጠፍታ
አለች አለች አንድ ቦታ
የኔ ስጦታ"
..
..
የወንድሙ ጅራ ዘፈን! ዘፈኑን ከነፍሴ ሰማውት... ከዚ በፊት ሺ ግዜ ሰምቼዋለው እንደዛሬ ግን አላዳመጥኩትም
....

"ለግዜው እንጅ ብሆን ከርታታ
አገኛታለው የማታ ማታ"
፨፨
፨፨
'ለምን የኔ "ለግዜው" ዘልአለም ሆነ? ለምን የኔ "የማታ ማታ" እንደምፅአት ቀን መምጫው ራቀ?' ይጠይቃል አንጎሌ... መልስ ግን .......
፨፨
፨፨
"አታጣድፉኝ ጥድፊያ አሎድም
ለኔ ያሰባት የትም አቴድም"
...
......
ዘፈኑኮ ርቋል..ግን ውስጤ የቀረው ድምፅ በ10እጥፍ ተባዝቶ ይሰማኛል.

"እኔ ቸኩዬ ነው? ወይስ እሱ ዘግይቶ? ማነው ተጠያቂው?? እኔ?.... ስላልታገስኩ?... እሱ?... ስለዘገየ?? ወይስ ፈጣሪ? እንዲ ስሆን እያየ ዝም ስላለ?....." ይጠይቃል ዳግም አንጎሌ..........
"ተረጋጊ! የእግዜር Timing ፍፁም ልክ ነው.. ያባይሆን ኖሮማ ሁሉም ያለግዜው እየሆነ አስቀያሚ ይሆን ነበር!" ይመልሳል ልቤ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ እውነቱን ይሆን??????

... የት ነህ ግን? ምን እየሰራህ ነው? መቼ ነው ምትመጣው?...... መልስ የሌላቸው የዘወትር ጥያቄዎቼ.... እርግጠኝነት የጎደላቸው የሁሌ ሀሳቦቼ.....
ይሄኔኮ አንዲት እንስት አቅፈህ "ዘላለም አብረን ነን" እያልካት ይሆናል.... ምናልባትም የድመቶቹን ድርጊት እየደገምክ ይሆናል.... ህምም! ....................

.... መቼ ነው ግን ውዴ.... ጨረቃን ምስክር አድርገህ እንደማትለየኝ የምትምልልኝ፣ አርፍደህ መጥተህ ይቅርታ የምትጠይቀኝ፣ ናፍቀኸኝ የምታስለቅሰኝ፣ እጄን ከኪሴ አውጥተህ በጆችህ የምታሞቀኝ፣ በጨረቃና ምድር የቀናውትን መልሰህ እነሱኑ የምታስቀናልኝ? .... መቼ ነው ፍቅሬ ሆይ.............................

ተፃፈ By aggie

@yekaldebdabewoch