Get Mystery Box with random crypto!

፦) ሁልጊዜም እንደ ዛሬው ነው.....አዲስ ነገር የለም ....አሮጌው በአዲስ ቀን ይተካል | የ ቃል ደብዳቤዎች💌



፦)
ሁልጊዜም እንደ ዛሬው ነው.....አዲስ ነገር የለም ....አሮጌው በአዲስ ቀን ይተካል ...የመሸው ፅልመት በፀሀይ ብርሀን ይበራል ...ትላንት ዛሬን ይተካል እንጂ.....ምንም ለውጥ የለም......ምንም አዲስም የለም ...ምንም ....ግን ምናልባት የኔ አዲስ ነገር አንተ ስለሆንክ ይሆን?....እንጃ አላውቅም

አንዳንዴ ግን ልክ ያልሆኑ ነገሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው አይደል.......በስህተቴ ውስጥ ያገኘሁህ ልክነቴ አንተ ነበርክ...በልክነቴም ያጣሁህ ስህተቴም አንተው ነህ ......

ታውቃለህ ...ረሳሁህ ብዬ ካመንኩ ከብዙ ጊዜያት ቦኋላ ነው ያስታወስኩህ .....ጠላሁህ ብዬ ከነገርኩህ ከብዙ ሂደቶች ቦኋላ ነው ፍቅርህ የበረታብኝ ......የእውነት ህይወቴ ናፍቀኸኛል ...ልክ እንዳልሆነ አውቃለሁ ግን አልቻልኩም የምር ከታገስኩት በላይ ነበር ባንተ ተስፋ የቆረጥኩት ግን አልሆነም .......አዲስ ነገር የለውም ባልኩት ማንነቴ ውስጥ ዳግም አሰብኩህ...

አሁን ላይ ግን ምን እንደሚቆጨኝ ታውቃለህ .....ተሸናፊዋም.... ጥፋተኛዋም እኔ መሆኔ ብቻ ....ለማሸነፍ ሳይሆን ላለመሸነፍ ስኳትን ነበር የተሸነፍኩት......ሀቀኛ ሳይሆን ከሃዲ ላለመሆን ስጥር ነበር ጥፋቴን ያገኘሁት......
ምናልባት ህይወቴ .....ማንነቴ አስቀይሞህ ...እኔነቴ አስጠልቶህ..እውነታዬ አስከፍቶህ እና ልቤ ጎድቶህ ይሆናል .........የእውነት ለዛም ደግሞ በጣም ይቅርታ ....

ህይወቴ ይቅርታ ስልህ ግን ጥፋተኝነቴ ተሰምቶኝ አልያም ከልቤ አዝኜ እንዳይመስልህ ....ታውቃለህ አይደል?.. ላለፈባቸው እና እኛነታችንን ላስረሱን ነገሮች አዝኜ እንደማላውቅ ....ለትላንት ተግባሬ እና ላለፈው ህይወቴ እንደማልቆጭ........አዎ ህይወቴ አንተ ትላንትናዬ ነህ.....ግን ይቅርታ እሺ .....ላለፈው ሳይሆን ለሁልጊዜው ...ለትላንቱ ሳይሆን ለዛሬው ጥፋቴ ....ይቅርታ.....

* በስህተቴ ውስጥ ያገኘሁህ ልክነቴ አንተ ነበርክ*

ፊያሜታ

@yekaldebdabewoch