Get Mystery Box with random crypto!

University of Ethiopian ( UOE)

የቴሌግራም ቻናል አርማ university0fethio — University of Ethiopian ( UOE) U
የቴሌግራም ቻናል አርማ university0fethio — University of Ethiopian ( UOE)
የሰርጥ አድራሻ: @university0fethio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 562
የሰርጥ መግለጫ

1⃣ የድፖርትመንት መረጃዎች
2⃣ የአምና MID EXAME
3⃣ የአምና FINAL EXAM
4⃣ freshman Pdf
5⃣ freshman short note
6⃣ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃዎች
ማየት ማመን ነው ሁሉንም በአንድ የሚያገኙበት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-07 10:31:18 #ArbaMinchUniversity

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት የተመደቡ የ'Applied Chemistry' እና 'Medical Radiology' ተማሪዎች ከኅዳር 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

https://t.me/university0fethio
538 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-06 13:02:53 #WolayitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ትምህርት ዘመን ሙሉ ካላንደሩን ይፋ አድርጓል።

በዚህም የሁሉም የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ ኅዳር 27 እና 28/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ያሳያል።

https://t.me/university0fethio
486 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-05 13:25:27 Technology


programming ችሎታ ያላቸው ወይንም ትንሽ hint ያላቸው ተማሪዎች አንዳንዶቹ Computer Science, አንዳንዶቹ ደግሞ Software Engineering መግባት እፈልጋለው ሲሉ እሰማለው,የ programming ችሎታ or ፍቅር ስላላቸው ብቻ

programming እንደ major Course ሚሰጡ የተለያዩ Departmentoch አሉ።

Computer Science
Computer Engineering
Software Engineering
Information System
Information Technology

፨ከእነዚህ 5 departments ፈለጣ ሚበዛበት

Computer Engineering ነው ፤ ሌሎቹ 1st Year Lay እንጂ this Much ፈለጣ የላቸውም።ግን ቀላል ናቸው ማለት አይደለም።
Maths ጎበዝ ሆነው programmer/coder መሆን ለሚፈልጉ i Suggest Computer Science.
ምክንያቱም CS Is All About mainly
Programming
Data Structure & Algorithm
Software Engineering
Networking.
maths ጎበዝ የሆኑ ተማሪዎች CS ቢገቡ የተሻለ ነው።
Computer Science ስራ የለውም ሚባለው ነገር...Conditional ነው።
ማለት Computer Science Degree ጨርሰው ምንም Code ማድረግ ማይችሉ አሉ(am Sorry to say this).
አብዛኛው አይችሉም።programming/coding perfect ከሆናችሁ እንደውም ግዜው አሁን ነው።ሀገር ውስጥ ቀርቶ ውጪ የመሄድ እድል ሰፊ ነው።

Computer Engineering/electrical and computer engineering.
ይሄ department ፈለጣ ይበዛዋል።
physics,maths ena programming ችሎታ ያላቸው ቢገቡበት ውጤታማ ይሆኑበታል።
Computer Engineering ከ software በተጨማሪ ስለ hardware Course አለው
Computer Engineering ማለት
የ Electerical Engineering እና የ Computer Science ድብልቅ ነው።
እዚ department ላይ physics እኮ its All About Analysis Of Circuit Design Nw Grade 12 ላይ የተወሰነ ተምረውታል።

Software Engineering ደግሞ programming ብቻ ሚወዱ ቢገቡበት አሪፍ ነው።
Software Engineering የ Computer Science Subdicipline ነው።
Computer Science ላይ Programming Language(java,C++,python)የመሳሰሉትን አይነት የ computer ቛንቛዎች develope እስከማድረግ ነው። which require a lot of math.
Software Engineering ግን , Computer Scientist በፈጠረው የ computer Programming Language(java,C++) በመጠቀም Application Ena Software Develope Maderg ነው።
ስለዚ Computer Science ከ software Engineering 1 Step ከፍ ያለ ነው ማለት ያስችላል(from Knowledge Aspect)
Computer Science በጣም ሰፊ ነው።

Computer Science የጨረሱ ተማሪዎች scientifically Programmer ነው ሚባሉት
Software Engineering የጨረሱ scientifically Software Developer ነው ሚባሉት።
Computer Engineering የጨረሱ Both Hardware&Software Engineer ይባላሉ።

Computer Science is all about how the Computing/Computer System Work.

Software Engineering Is All About How Software System Work.
information System ሚባለው ደሞ ከ Software ዝቅ ብሎ information ወይንም data እንዴት process እንደሚደረግ የሚዳሰስ ነው።
Information System Is All About How Data Is Processed. programming Major Course Nw.
Gn Computer Science ላይ የሚሰጡ programming Language እዚ ላይሰጡ ይችላሉ።ለምሳሌ
ወልቂጤ ዩንቨርሲቲ
information System Or Information Science ላይ
C#(C Sharp) ሚባል programming Language ይማራሉ። Computer Science ተማሪዎች ግን አይወስዱትም።
Information Technology ያው be Computer technology የመጨረሻው ቀላል department nw.

#atc

Join and share
https://t.me/university0fethio
https://t.me/university0fethio
3.7K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-04 19:43:00 #MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም ከወልዲያ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 11 እና 12/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ከወልዲያ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ለምዝገባ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ የተማሪነት መታወቂያ ካርድ የምዝገባ ስሊፕ እና ግሬድ ሪፖርት
• የ8ኛ፣ 10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕቶች
• የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰርቴፊኬት (3 ኮፒ)
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
871 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-03 19:33:29 #BongaUniversity

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ከአክሱም እና ከወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ተቋሙ የተመደቡ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 29 እና 30/2014 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።

ተማሪዎች ለምዝገባ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ የተማሪነት መታወቂያ ካርድ
• የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ የምዝገባ ስሊፕ
• የነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ግሬድ ሪፖርት
• የ8ኛ፣ 10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕቶች
• የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰርቴፊኬት (3 ኮፒ)
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)

ምንጭ፡የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
@university0fethio
@university0fethio
@university0fethio
@university0fethio
485 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 22:12:48 #NewsAlert

የትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመወያየት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሀሳቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ የሁሉንም ዜጋ ኀላፊነት እና ትብበር የምትፈልግበት በመሆኑ ከሕዳር 27 እስከ ታህሳስ 3/2014 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በጦርነቱ የዘማች አርሶ አደሮችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦችን በመርዳት ትብብር እንዲያደርጉ ወስኗል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ " ለዘመቱ አካላት የሚሆን የስንቅና የደም ልገሳ በማድረግም የዜግነት ግዴታን የምንወጣበት ጊዜ ነው " ያሉ ሲሆን " ተማሪዎች ትምህርት በሚቋረጥበት ጊዜ ከትምህርታቸው ሳይዘናጉ የወገን ጦርን የሚረዱበትና የሀገር ፍቅራቸውን የሚያሳዩበት ይሆናል " ሲሉ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
509 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 22:12:47 ዛሬ ረፋዱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የዋዜማ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል። ሰልፈኞቹ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት፣ በኢምባሲው ዋና በር ላይ ለ40 ደቂቃ ያህል ድምጽ ሳያሰሙ በጸጥታ በመቀመጥ እና የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት እና አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ብዙኀን መገናኛዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያሠራጯቸውን የተዛቡ መረጃዎች እና ለአማጺው ሕወሃት የሚያሳዩትን ወገንተኝነት የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ነው። #ዋዜማ
479 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 10:45:12 #MaddaWalabuUniversity

የመደ ወላቡ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ ትክክለኛ አለመሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

@university0fethio
485 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ