Get Mystery Box with random crypto!

#NewsAlert የትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ | University of Ethiopian ( UOE)

#NewsAlert

የትምህርት ሚኒስቴር ለተወሰነ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ የዘማቾች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመወያየት ውሳኔ በተሰጠባቸው ሀሳቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ የሁሉንም ዜጋ ኀላፊነት እና ትብበር የምትፈልግበት በመሆኑ ከሕዳር 27 እስከ ታህሳስ 3/2014 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ተግባር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በጦርነቱ የዘማች አርሶ አደሮችን የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ቤተሰቦችን በመርዳት ትብብር እንዲያደርጉ ወስኗል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ " ለዘመቱ አካላት የሚሆን የስንቅና የደም ልገሳ በማድረግም የዜግነት ግዴታን የምንወጣበት ጊዜ ነው " ያሉ ሲሆን " ተማሪዎች ትምህርት በሚቋረጥበት ጊዜ ከትምህርታቸው ሳይዘናጉ የወገን ጦርን የሚረዱበትና የሀገር ፍቅራቸውን የሚያሳዩበት ይሆናል " ሲሉ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።