Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ረፋዱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ | University of Ethiopian ( UOE)

ዛሬ ረፋዱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የዋዜማ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል። ሰልፈኞቹ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት፣ በኢምባሲው ዋና በር ላይ ለ40 ደቂቃ ያህል ድምጽ ሳያሰሙ በጸጥታ በመቀመጥ እና የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት እና አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ብዙኀን መገናኛዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚያሠራጯቸውን የተዛቡ መረጃዎች እና ለአማጺው ሕወሃት የሚያሳዩትን ወገንተኝነት የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ነው። #ዋዜማ