2023-03-29 23:50:40
የእስራኤል ነቢይ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ
አምላካችን አሏህ ዒሣን መልእክተኛ አድርጎ የላከው ወደ እስራኤል ልጆች ስለሆነ እርሱ፦ "የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የተላኩኝ የአላህ መልእክተኛ ነኝ" በማለት ተናግሯል፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልእክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላኩኝ የአላህ መልእክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ
ይህ ሐቅ በባይብል ላይ በቅሪት ደረጃ ኢየሱስ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" ብሏል፦
ማቴዎስ 15፥24 እርሱም መልሶ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" አለ።
"በቀር" የሚለው ግድባዊ ተውሳከ ግሥ ከእስራኤል ቤት ውጪ ለሌላ አለመላኩን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። በተጨማሪ ጴጥሮስ፦ "የእስራኤል ሰዎች ሆይ! የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ "ለ"-እናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ" በማለት የናዝሬቱ ኢየሱስ ለእስራኤል ሰዎች እንደተላከ ይናገራል፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 "የእስራኤል ሰዎች" ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ "ለ"-እናንተ" የተገለጠ ሰው ነበረ።
ጳውሎስ ምንም እንኳን በኃላ ላይ አሳቡን ቢቀይርም በጅምሩ ላይ፦ "እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል "ለ"-እስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ" በማለት እግዚአብሔር ኢየሱስን ለእስራኤል እንዳመጣው ተናግራል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23፤ ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል "ለ"-እስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።
ልጅነት፣ ኪዳን፣ የተስፋው ቃል ወዘተ ለእስራኤል ቤት ብቻ የተሰጠ ሲሆን መሢሕም "ይመጣላችኃል ይላክላችኃል" ተብሎ ቃል የተገባላቸውም ለእስራኤል ቤት ብቻ ነው፥ ይህንን የልጆችን የእስራኤል ቤት እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም፦
ማቴዎስ 15፥26 እርሱ ግን መልሶ፦ "የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም" አለ።
ማቴዎስ 15፥27 እርስዋም፦ "አዎን ጌታ ሆይ! ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ" አለች።
"ቡችሎች" የተባሉት ከእስራኤል ቤት ውጪ ያሉት ሰዎች ናቸው፥ ከእስራኤል ቤት ውጪ ያሉት ሰዎች ከእስራኤል ቤት ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ እንጂ ዋናው የኢየሱስ መልእክት ለእስራኤል ቤት ብቻ እና ብቻ ነው። ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣ ነቢይ ነው፦
ዮሐንስ 6፥14 ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ "ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው" አሉ።
የእስራኤል ቤት እኮ ዓለም ነው፥ "ዓለም" የሚለው የእስራኤልን ቤት ያመለክታል፦
ዮሐንስ 15፥18 ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።
ኢየሱስን የጠሉት እነማን ናቸው? የእስራኤል ቤት ወይስ መላው የሰው ልጆች? ፈሪሳውያን፦ "ዓለሙ በኋላው ተከትሎት ሄዶአል" ሲሉ ተከትለው የሄዱት ሰዎች አንድ ሺህም አይሞሉም ነበር፦
ዮሐንስ 12፥19 ሰለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፦ አንድ ስንኳ ልታደርጉ እንዳይቻላችሁ ታያላችሁን? እነሆ፥ ዓለሙ በኋላው ተከትሎት ሄዶአል" ተባባሉ።
ስለዚህ "ዓለም" ሲባል መላው የሰው ዘር ሳይሆን የእስራኤል ቤትን በጉልኅ የሚያሳይ ነው፦
ቆላስይስ 2፥20 ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ።
ገላትያ 4፥3 እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን።
"ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት" የሚለው የፊተኛውን ኪዳን እንደሆነ ገላትያ 4፥9 ቆላስይስ 2፥8 ላይ ያሉትን ጥቅስ ተመልከት! የሙሴ ሕጉም ሁሉ እና የነቢያት ትንቢት "ተሰቅለዋል" ሲባል ጳውሎስ "ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት" ሲል በሕግ በኩል ለሕግ መሰቀሉን ለማመልከት "እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት" በማለት ዓለም የሚለው የእስራኤልን ቤት እንደሆነ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 22፥40 በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።
ገላትያ 2፥19 በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና፥ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ።
ገላትያ 6፥14 ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
"በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ" የሚለው ይሰመርበት! የሙሴ ሕግ የያዘው የእስራኤል ቤት ሲሆን ኢየሱስ ከአብ የሰማውን መልእክት "ለዓለም እናገራለሁ" ሲል "ለእስራኤላውያን እናገራለን" ማለቱ እንጂ ለሰው ዘር ሁሉ ማለቱ አይደለም፦
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን "ይህን ለዓለም እናገራለሁ"።
ኢየሱስ፦ "ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ" ሲል የእስራኤል ቤት የሆኑትን የጠፉ በጎች ነው፥ እርሱ የተላከው ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 10፥6 ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።
ማቴዎስ 15፥24 እርሱም መልሶ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" አለ።
ዮሐንስ 10፥16 ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
ክርስቲያኖች ሆይ! በኢየሱስ በማመናችሁ ትሩፋት በመካዳችሁ ቅጣት አታገኙም፥ ምክንያቱም ኢየሱስ ለእስራኤል ቤት የተላከ የእስራኤል ነቢይ ነው። ብትከተሉት ከልጆች እንጀራ የተረፈ ፍርፋሪ እንጂ ቡችሎች ናችሁ፥ ለእናንተ ፍርፋሪ ከመብላት መፍትሔው ነቢያችንን"ﷺ" መከተል ነው። ምክንያቱም ነቢያችን"ﷺ" ለሰዎች ሁሉ የተላኩ የአሏህ መልእክተኛ ናቸው፦
4፥79 "ለሰዎችም ሁሉ" መልእክተኛ ኾነህ ላክንህ፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا
7፥158 በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ "ወደ ሁላችሁም" የአላህ መልእክተኛ ነኝ»፡፡ قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُمْ جَمِيعًا
34፥28 አንተንም "ለሰዎች ሁሉ በሙሉ" አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا كَافَّةً لِّلنَّاسِ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
148 views20:50