2023-02-18 20:22:43
አስገራሚ የመፅሀፍ "ቅዱስ" አንቀፆች
አስፀያፊ አንቀፆች
እነኝህ ቃላት አይደለም አምላክ ሊናገራቸውና የሰው ልጅ እንኳን ሊጠራቸው የሚያሳቅቁ ናቸው፡፡
❖ የሴት ልጅ ጡት
ወሲባዊ በሆነ መልኩ የሴት ልጅ ጡት ባይብል ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ለአብነት ጥቂቶችን እንግለፅ
➊ (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕ. 1)
----------
13፤ ውዴ ለእኔ #በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።
14፤ ውዴ ለእኔ በዓይንጋዲ ወይን ቦታ እንዳለ እንደ አበባ እቅፍ ነው።
15፤ ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዓይኖችሽም እንደ ርግቦች ናቸው።
16፤ ውዴ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መልካምም ነህ፤ አልጋችንም ለምለም ነው።
➋
(መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕ. 4)
----------
5፤ ሁለቱ #ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩእንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
6፤ ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪያልፍ ድረስ፥ወደ ከርቤው ተራራ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።
7፤ ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም።
8፤ ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፤ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፤ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
9፤ እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፤አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽ ድሪ በአንዱልቤን በደስታ #አሳበድሽው።
➌ " በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አበዛሁሽ፥ አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ፤ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆንሽ፥ ተራቍተሽም ነበርሽ። "
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 16:7)
ስለዚህ የሚያወሩ አንቀፆች ብዙ ስለሆኑ ሁሉንም መዘርዘሩ ይከብዳል አንቀፁን ብቻ ሰጥቸ ልለፍ፡፡
መኃልየ መኃልየ ዘሰለሞን 7:4 ; 7:8; 8:10
❖ የእግዚአብሄር "ሚስቶች"
በህዝቅኤል ትንቢት እንደተገለፀው እግዚአብሄር ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ እስኪ ሙሉ ታሪኩን ህዝቅኤል እራሱ ይንገረን፡፡
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 23)
----------
1፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።
3፤ በግብጽም አመነዘሩ፥ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ #ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ።
4፤ ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
5፤ ኦሖላም ገለሞተችብኝ፥ ውሽሞችዋንም ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው።
6፤ እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ።
7፤ ግልሙትናዋንም ከተመረጡ ከአሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደረገች፥ በፍቅር በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።
8፤ በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም፤ በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም #ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር።
❖ የወንድ ልጅ ብልት
ይሄኛው ደግሞ እጅግ አሳፋሪ ከመሆኑ የተነሳ ለመንፈሳዊ ሰው ይፅፈው ዘንድ እራሱ ይከብዳል፤ እንዲህ ይነበባል
" #ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። "
(ኦሪት ዘዳግም 23:1)
❖ ማጠቃለያ
እንግዲህ እነኝህ አንቀፆች አይደለም ከአምላክ ይቅርና ከቅዱሳን ሰዎች እንኳን ቢሠማ ያሰቅቃል፡፡ አምላክ ደግሞ ከማንም በላይ ቅዱስ ነውና ከሱ እንዲህ አይነት ወሲብ ቀስቃሽ ፁሁፎችን አንጠብቅም እናም እመኑኝ መፅሀፍ "ቅዱስ" የግለሰብ ድርሰት የተቀላቀለበት ፁሁፍ እንጅ ንጹህ የአምላክ ቃል አይደለም፡፡
አሏሁ አዕለም!!!
የሕያ ኢብኑ ኑህ
መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
406 views17:22