Get Mystery Box with random crypto!

Tiriyachen | ጥሪያችን

የቴሌግራም ቻናል አርማ tiriyachen — Tiriyachen | ጥሪያችን T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tiriyachen — Tiriyachen | ጥሪያችን
የሰርጥ አድራሻ: @tiriyachen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.91K

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-24 20:47:24 "ለጌታ እንደ ምትገዙ ለባሎቻቹህ ተገዙ።" የሰውና የአምላክ ክብር | ኡስታዝ ወሒድ ዑመር





  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
196 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:42:12 የጠፉ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች

“የጠፉ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች” የሚለውን አርዕስት ስትመለከቱ ምናልባት ፀሀፊዎቻቸው ስለማይታወቁ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች አስመልክቶ የቀረበ ፁሁፍ መስሎ ሊታያችሁ ይችላል። በርግጥ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ፀሀፊያቸው የማይታወቅ በርካታ መፅሀፍቶች አሉ። ከሙሴ ኦሪት ጀምሮ አብዛኛው የይዘቱ ክፍል በማን እንደተፃፈ በትክክል አይታወቅም። ነገር ግን ዛሬ የምናወራው ከዛም ስለከፋ ነገር ነው። ይኸውም የመጽሀፉ ህልውና በስያሜ ደረጃ ተነግሮ ነገር ግን ያ የተነገረው መፅሀፍ ከነ አካቴው የት እንዳለ ስለማይታወቅ መጽሀፍ ነው። መሠል ንግግሮች መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ተደጋግመው ተጠቅሰው እናገኛለን። ለአብነት ጥቂቶችን ከታች ለመጥቀስ እሞክራለሁ፦

❶- የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሀፍ

❝ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥❞ ዘኍልቁ ❷❶: ❶❹

❐ እግዚአብሔር የጦርነት መጽሀፍ እንደነበረው መስማት አስደናቂ ቢሆንም እንዳለመታደል ሁኖ ግን ይህ መጽሀፍ አሁን ላይ የውሃ ሽታ ሁኗል። መጽሀፉ እንደነበረ ተገለፀልን እንጅ መጽሀፉ የት እንደገባ አይታወቅም..!

❷- የሰለሞን ታሪክ

❝የቀረውም የሰሎሞን ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ጥበቡም፥ እነሆ፥ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።❞ ❶ኛ ነገሥት ❶❶: ❹❶

❐ ይህ የሰለሞን ታሪክ መፅሀፍ ከወዴት ይገኛል?

❸- የያሻር መጽሀፍ

❝ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።❞
ኢያሱ ❶⓿: ❶❸

በተጨማሪም

❝የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል።❞
❷ኛ ሳሙኤል ❶: ❶❽

❐ የያሻር መጽሀፍ አሁን ታዲያ መገኛው ወዴት ነው?

❹- የጠፉ የሰለሞን ምሳሌዎችና መኃልዬች

❝እርሱም ሦስት ሺህ ምሳሌዎች ተናገረ፤ መኃልዩም ሺህ አምስት ነበረ።❞
❶ኛ ነገሥት ❹: ❸❷

❐ እነዚህ መፅሀፍት ወዴት ይሆን የሚገኙት?

❺- የነብዩ ናታን ታሪክና የባለራእዩ የአዶ ራእይ

❝የቀረውም ፊተኛውና ኋለኛው የሰሎሞን ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በኦሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራእዩ በአዶ ራእይ የተጻፈ አይደለምን?❞ ❷ ዜና ❾: ❷❾

❐ የነብዩ ናታን ታሪክና የባለራእዩ የአዶ ራእይስ ከወዴት ይገኛል?

❻- የነብዩ ሸማያና የአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሀፍ

❝የሮብዓምም የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ ሸማያና በባለ ራእዩ በአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከልም በዘመናቸው ሁሉ ሰልፍ ነበረ።❞ ❷ ዜና ❶❷: ❶❺

የነብዩ ሸማያና የአዶ የትውልድ ታሪክ መጽሀፍ አሁን ከወዴት ይገኛል?

❼- የነብዩ ኢሳያስ ድርሳን

❝የቀረውንም የፊተኛውንና የኋለኛውን የዖዝያንን ነገር ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ጽፎታል።❞ ❷ ዜና ❷❻: ❷❷

❐ ነብዩ ኢሳያስ የቀረውን የዖዝያንን ነገር የጻፈበት ድርሳኑስ ከወዴት ይገኛል?

❽- የሳሙኤል፣የናታንና የጋድ ታሪክ

❝የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።❞
❶ ዜና ❷❾: ❷❾

❐ የሳሙኤል፣የናታንና የጋድ ታሪክ አሁን ላይ ከወዴት ይገኛሉ?

ሲጠቃለል

ይህ ብዙ ትንተና ሳያስፈልገው በግልጽ ቋንቋ የነኝህ ሰዎችና ነብያት ራዕይና ድርሳን ጠፍቷል፡፡ የነብያት ጹሁፍና ራእያቸው አይጠፋም እያሉ የሚከራከሩን ክርስቲያኖች እነዚህ ስያሜያቸው ብቻ ለታሪክ የቀሩ መጽሀፍቶች እንዴት ከምድረ ገፅ ሊጠፉ እንደቻሉ ሊነግሩን ይችላሉ?

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
227 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 19:41:57
214 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 20:49:14
ፈጣሪ አይተኛም አያንቀላፋም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ሰው በፍጡርነቱ ያንቀላፋል ይተኛልም፤ ፈጣሪ ግን ፍጡር ስላልሆነ አይተኛም አያንቀላፋም፦
መዝ.121:4 እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ #አይተኛም #አያንቀላፋምም።

ኢየሱስ ደግሞ በተቃራኒው ፍጡር ስለሆነ ይተኛን ያንቀላፋል፦
ማርቆስ 4:38 እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ #ተኝቶ ነበር፤ #አንቅተውም። መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።

የፈጣሪን ባህርይ ለፍጡር መስጠት አይገባም፤ ይህ ቃል መባል ያለበት ፍጡር ለሆነው ለሚተኛው ለኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስ ሲተኛ ሲጠብቀው ለነበረው ለአላህ ብቻ ነው፤ አላህ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሚባል ባህርይ የለውም፦
2፥255 አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ "#ማንገላጀትም #እንቅልፍም አትይዘውም"፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? ከፍጡሮች በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

አንዱ አምላክ የማይተኛና የማያንቀላፋ ከሆነ፣ ኢየሱስ ደግሞ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ከሆነ ፣ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ኢየሱስ ፣ የማይተኛና የማያንቀላፋውን አንዱን አምላክ በምን አይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል?

ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
338 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:18:35
ዒድ ሙባረክ

Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
531 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 00:55:01 ዘካቱል ፊጥር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

“ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው። “ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏

“ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው። ነዳያን ሲቀሩ ይህ ገንዘብ ወደ ሶላቱል ዒድ ከመሄዳችን በፊት መክፈል በሁሉም ሙሥሊም ላይ የተጣለ ፈርድ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 109
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመሄዳቸው በፊት እንዲከፈል አዘዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم أَمَرَ بِزَكَاةِ الْفِطْرِ قَبْلَ خُرُوجِ النَّاسِ إِلَى الصَّلاَةِ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 104
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ከሙሥሊም በሁሉም ተገልጋይ ሆነ አገልጋይ አሊያም ወንድ ሆነ ሴት ላይ ከተምር አንድ ሷዕ ወይም ከገብስ አንድ ሷዕ ዘካቱል ፊጥር እንዲከፈል ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَرَضَ زَكَاةَ الْفِطْرِ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، عَلَى كُلِّ حُرٍّ أَوْ عَبْدٍ، ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى، مِنَ الْمُسْلِمِينَ‏.‏

በሐዲሱ “ሷዕ” صَاع ማለት እና በቁርኣኑ 12፥72 ላይ “ሡዋዕ” صُوَاع ማለት “የእህል መስፈሪያ” ማለት ነው፥ አንድ ሷዕ በክብደት ከ 2.04 እስከ 2.5 kg የሚመዝን ወይም በመጠን በሁለት እጆች 4 እፍኞች ሲሆን ወደ ዓለም ዓቀፍ የመለኪያ ሥርዓት”metric system” ገንዘብ ሲቀየር 5.5 ፓውንድ ይሆናል። በሸቀጥ ገንዘብ ግብይት ዘካቱል ማል የሚወጣው ከብር፣ ከወርቅ እና ከቤት እንስሳት ሲሆን ዘካቱል ፊጥር ደግሞ ከእህል ዓይነት ነው። ዘካን የማይሰጥ “በመጨረሻይቱ ዓለም ከአሏህ ዘንድ መተሳሰብ የለም” ብሎ የሚክድ ሰው ነው፦
41፥7 ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُم بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ

ዘካን ካለመስጠት ከሚያስቀጣ ቅጣት አሏህ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv

ወሠላሙ ዐለይኩም
232 views21:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 00:54:49
227 views21:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 20:33:57 የድምፅ ትምህርት | 10.6 MB

«የጦም ቱሩፋት»


በኡስታዝ ወሒድ ዑመር

#Tiriyachen
#ንፅፅር_ሐይማኖት

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
350 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 04:37:02 ይህ ቤት ንድፉ ርዝመት፣ ስፋት፣ ቁመት ያለው ባለ ሦስት ቅጥ ስለሆነ “ከዕባህ” ተብሏል፥ “ከዕባህ” كَعْبَة ማለት “አንኳር“The Cube” ማለት ነው። ሁላችንም ቂብላችን ወደዚህ ቤት ነው፥ “ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው። የትም ቦታ ሆነን ለአንድነት ለአላህ የምንሰግደው ወደ ከዕባህ ነው፦
2፥149 *ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር*፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው። ይህ የመጀመሪያው መሥጂድ ነው። እንግዲህ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙሥሊሞች በሕይወት ዘመናቸው አንዴ በመካህ የሚገኘው የአላህን ቤት መጎብኘት ፈርድ ነው። “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት” ማለት ነው። “ሐጅ” حَجّ መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥196 *ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ*፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ *ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው*፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ ۖ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا ۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
2፥158 *ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም*፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ ቤት የሚጎበኝ ተባዕት "ሓጅ" حَاجّ ሲባል፥ የአላህ ቤት የሚምትጎበኝ እንስት ደግሞ "ሓጃህ" حَاجَّة‎ ትባላለች። የሓጅ ወይም የሓጃህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሑጇጅ" حُجَّاج‎ ይባላሉ። አምላካችን አላህ በቅድስት አገር የሚገኘውን ቤቱን ከሚጎበኙት ሑጇጅ ያድርገን! አሚን።

ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

‐‐‐
መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
286 viewsedited  01:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 04:37:01 "ሙሥሊመይኒ" مُسْلِمَيْنِ ሙሰና ሲሆን ለሁለቱ ማለትም ለኢብራሂም እና ለኢሥማዒል የገባ ቃል ነው፥ "ለአንተ ታዛዦችም አድርገን" ማለቱ ይህንን ያሳያል። "ሙሥሊማህ" مُّسْلِمَة ደግሞ "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው አንስታይ መደብ ሲሆን አምላካችን አላህ የኢሥላምን አስኳል የተውሒድን ቃል በዝርዮቹም ውስጥ ቀሪ ቃል አርጓታል፦
43፥28 *”በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት”*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ኢብራሂም፦ "ከዘሮቼ" አለ እንጂ "ዘሮቼ" አላለም። "ዘሮቼ" በሚለው ቃል መነሻ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ሁሉም ዘሮቹ ሁሉ አማንያን እንዳልሆኑ እንደውም ከእነዚህ በተቃራኒው በክደት ጣዖታውያን የሆኑ አሉ፥ ከእነርሱ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን፣ መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን እና ከክህደት የሚያጠራቸውን መልእክተኛ አላህ ልኳል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን *"ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ"*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና *"ከክህደትም የሚያጠራችሁ*፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُون

ይህ መልእክተኛ"ﷺ" ሲመጣ ከክህደትም የሚያጠራችሁ ነው። ይህም ክህደት በአላህ ላይ ጣዖታትን ማጋራት ነው። በኢብራሂም ተገንብቶ የነበረው ቤት ቁረይሾች በማዛባት ገንብተው ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽም? አሏት። እርሷም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን በኢብራሂም በተመሠረተውን ተመልሰው አይገነቧትም? አለች። እርሳቸውም፦ "የአንቺ ሕዝብ በኩፍር ባይከስቱት ኖሮ አደርገው ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا ‏"‏ أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ‏"‌‏.‏ فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَلاَ تَرُدُّهَا عَلَى قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لَوْلاَ حِدْثَانُ قَوْمِكِ بِالْكُفْرِ لَفَعَلْتُ ‏

ቁረይሾች በአላህ ቤት ዙሪያ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ እና በአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ሠርተው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 320
ዐብደላህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በመክፈት ቀን ወደ መካህ በገቡ ጊዜ ሦስት መቶ ስድሳ ኑሱብ በአላህ ቤት ዙሪያ ነበሩ። እርሳቸውም እነርሱን በእጃቸው መምቻ በመምታት ሲጀምሩ፦ "እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ دَخَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مَكَّةَ يَوْمَ الْفَتْحِ وَحَوْلَ الْبَيْتِ سِتُّونَ وَثَلاَثُمِائَةِ نُصُبٍ، فَجَعَلَ يَطْعُنُهَا بِعُودٍ فِي يَدِهِ وَيَقُولُ ‏ "‏ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ، جَاءَ الْحَقُّ، وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ ‏"‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል”ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም፦ “አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም” አሉ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ “‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ

"ኑስብ" نُصْب ማለት "ሐውልት" ማለት ሲሆን የኑስብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኑሱብ" نُصُب ወይም "አንሷብ" أَنْصَاب ነው፥ “አዝላም” أَزْلاَم ማለት ደግሞ “የጥንቆላ ቀስት” ማለት ነው። አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም *"አንሷብም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው"*፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
ነቢያችን"ﷺ" ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው አንሷብን እና አዝላምን ካስወገዱ በኃላ ከዕባን አድሰዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 68
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ" ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ *"ከዕባህ በሚገነባ ጊዜ ነቢዩ"ﷺ" እና ዐባሥ ለግንባታ ድንጋዮች ለማምጣት ሔዱ። ዐባሥ ለነቢዩ"ﷺ"፦ "የወገቦትን መታጠቂያ አንገቶት ላይ ያድርጉ" አለ"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ لَمَّا بُنِيَتِ الْكَعْبَةُ ذَهَبَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَعَبَّاسٌ يَنْقُلاَنِ الْحِجَارَةَ فَقَالَ الْعَبَّاسُ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم اجْعَلْ إِزَارَكَ عَلَى رَقَبَتِك
261 views01:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ