Get Mystery Box with random crypto!

Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ talkethiopia — Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ talkethiopia — Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ
የሰርጥ አድራሻ: @talkethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.01K
የሰርጥ መግለጫ

በዋነኝነት በፌስቡክ የማጋራቸውን ጽሑፎች እና ላይቭ ቪዲዮዎች ባልተቋረጠና ሌሎች ፖስቶችን በማይቀላቅል መልኩ ለማድረስ የተቋቋመ ነው።
ድረገጽ [ https://www.talkethiopia.com ]
ፌስቡክ ገጽ [ fb.me/isuchisu ]
ዩቲውብ ቻነል [ bit.ly/SubscribeToIsaac ]
ትዊተር [ twitter.com/isuchisu ]

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-20 13:53:02 ንፁሃንን የሚቀጥፍ ፖለቲካ ሥር አልባ ዛፍ ነው! አያፈራም!
.
———
❝በቶሌ በአንድ መስጊድ ውስጥ ብቻ 40 ሰው ነው የተገደለው። እኔ ቤት ውስጥ 12 ሰው ሞተ። ሌላው ቆስሎ ወጣ። ያው በረሐ ላይ በእግር እየሄድን ነው መድረሻ አጥተን። ሁለት ልጆች ተርፈውልኝ ነበር በውሃ ጥም ተቸግረናል።❞
.
ከጥቃቱ የተረፉ አንድ አዛውንት ለዶቼቬሌ
———
.
#ወሎጠልነት #ወለጋ #ወለጋየደምምድር #የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #የወሎኦሮሞ #ኢትዮጵያ
1.6K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 13:50:57
1.6K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 13:50:48 ወለጋ የምስኪኑ ወሎዬ መታረጃ ሆና እስከመቼ?
══════
.
በቅርብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደወሎ ሕዝብ ተሳዳጅና ሰለባ የሆነ የለም። በተለይ ደግሞ የደም ምድር ሆና በቀረችው ወለጋ የወሎ ጥላቻ ባናወዛቸውና የደም ጥማት ባሰከራቸው ታጣቂዎች እንደቅጠል የሚረግፈው ወለዬው ከሆነ እጅግ ሰንብቷል። ይኸው እንደተለመደው አንዳችም ጠባቂ የሌላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ከ250 በላይ የወሎ ተወላጆች (የወሎ ኦሮሞዎችን ጨምሮ) በወለጋ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተዘግቧል። በአንድ መስጊድ ውስጥ ብቻ ከ40 በላይ ሙስሊም ወለዬዎች በጭካኔ እንደተገደሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
.
እንደተለመደው ሁሉ መንግሥት "ገዳዩ ሸኔ ነው" ሲል OLA ደግሞ ውንጀላውን አስተባብሎ ድርጊቱን በመንግሥት ታጣቂዎች ማሳበቡን ዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። እስከዛሬም የተለመደው ይኸው ነው - ወሎዬው ይጨፈጨፋል። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም "እኔ የለሁበትም" ይላሉ። መንግሥትም በታጣቂዎቹ እያሳበበ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል። ክስተቱም የልሙጥ ፖለቲካ አጀንዳ አራማጆችና የአስከሬን ነጋዴዎች የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆኖ አንዳችም መፍትሄ ሳያገኝ እንደቀልድ ያልፋል።
.
እጅግ ያሳዝናል! ንጹሃንን በመጨፍጨፍ የፖለቲካ ግባቸውን እንደሚያሳኩ የሚያምኑ ታጣቂ ቡድኖች መቼ ይሆን ወሎዬውን መቆመሪያ ማድረጋቸውን የሚያቆሙት?! መቼ ነው የወለዬ ሕይወት በወለጋ ከጓሮ እንስሳት የተሻለ ዋጋ የሚኖረው?! መቼ ነው ደም አፍሳሾቹ ገዳዮች በፍትህ እልፍኝ የእጃቸውን የሚያገኙት?! እስከመቼ ነው ይህን የአጀንዳ ቆማሪ እንጂ ከልብ ተቆርቋሪ ባለቤት ያጣ ምስኪን ወሎዬ እየጨፈጨፉ "እኔ አይደለሁም እገሌ ነው" በሚል ተራ መካካድና እርስ በእርስ ማሳበብ ደሙን ደመ ከልብ አድርገው የሚያስቀሩት?!
.
ወደድንም ጠላንም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በወለጋ በወሎ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ሰብዓዊ ወንጀልና ጭፍጨፋ ለማስቆም ተከታታይ ዘመቻዎችን ማድረግ፣ ለምስኪኑ ሕዝብ ፍትህ ቢቀር ቢያንስ የመኖር ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ድምጹን ለዓለም ማሰማት፣ ጽንፈኛ ታጣቂዎችና የፖለቲካ ቁማርተኞች "ተቆርቋሪ የለውም" በሚል የሚጫወቱበትን ሕዝብ "አለሁልህ" የማለት ግዴታ አለብን።
.
የወሎ ተወላጅ አክቲቪስቶች እና ሚዲያዎች ተሰባስበው ጉዳዩን በዋና ባለቤትነት ማስኬድ፣ አጀንዳ ቀርፆና አስተዋይ አካሄድ መርጦ የተደራጀ ድምጽ የማሰማት እንቅስቃሴ ማድረግና ለክፉ የአስከሬን ነጋዴዎችና የፖለቲካ ቁማርተኞች መጠቀሚያ የማይሆን ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በበኩሌ እንደአንድ ግለሰብ እና የሚዲያ ባለሙያ በዚህ በኩል የቻልኩትን ለማድረግና የወሎን ሕዝብ ሰቆቃ ለማሰማት በቻልኩት የማግዝ ይሆናል። (ዛሬ ምሽት በዚሁ ጉዳይ ዕይታዬን ለማጋራት እሞክራለሁ!)
.
ንጹሃንን መያዣ እና መቆመሪያ የሚያደርግ ፖለቲካ ሁሉ ወዳቂ ነው!
.
#ወሎጠልነት #ወለጋ #ወለጋየደምምድር #የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #የወሎኦሮሞ #ኢትዮጵያ
1.8K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 13:26:46 በአማራ ብሄርተኞች ስፖንሰርነትና ድጋፍ ብሄር ብሄረሰቦችን ሲያንቋሽሹ የኖሩት አቶ ታዲዮስ ታንቱ ነውረኛ አቋሞች የዛሬው "ካየሁት በኋላ" ትኩረቴ ነው። የተመልካች አስተያየትም ተካትቷል።
.
Enjoy! | Like | Share | Subscribe
.
[

]
.
ቶክ ኢትዮጵያን ያግዙ!
[ https://gofund.me/909f39f3 ]
የኢትዮጵያ የባንክ ሒሳብ… ⇩
AHMED ADEM GETU (CBE)
Acc NO: 1000436333483
.
#ታዲዮስታንቱ #የአማራብሄርተኝነት #ፋኖ #አሐዳዊነት #ልሙጣዊነት #ትምክህት #የብሄርፖለቲካ #ኢትዮጵያ #ካየሁትበኋላ
1.3K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 14:18:25
1.5K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 14:18:19 የአማራ ብሄርተኞች ተከፋይ ተሳዳቢ አቶ ታዲዮስ ታንቱ
══════
.
በአማራ ብሄርተኞች ❝እውነተኛ የታሪክ ምሁር❞ ተብለው የሚወደሱትና ኢትዮጵያውያንን እንዲሳደቡ ገንዘብ ተዋጥቶላቸው በየመድረኩ የሚጋበዙት ነውረኛው አቶ ታዲዮስ ታንቱ በምኒልክ ቲቪ ባቀረቡት አንድ ፕሮግራም ለጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ ኢትዮጵያን ከሀ እስለ ፐ የሠራት አማራ እንደሆነ ካስረዱት በኋላ ሌሎችን ሲያጥላሉ እንዲህ አሉት…
.
———
❝በዓመት አንድ ጊዜ ገላቸውን የማይታጠቡ አያት ቅድም አያቶቻቸው ተስማምተው የኖሩባት ኢትዮጵያ እነሱ ዛሬ በቀን ሁለት ጊዜ ሻወር ስለወሰዱ መበታተን አለባት?❞
———
.
አስቡት እንግዲህ ከአማራ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ❝በዓመት አንድ ጊዜ ገላቸውን የማይታጠቡ❞ ሲሉ መውረፍ ምን ያክል አሳፋሪ እንደሆነ?
.
እርግጥ ሰውየው በሚዲያ ቅሌት የሚታወቁ በመሆናቸው ከዚህም የባሰ ሲናገሩ ኖረዋል። የሚገርሙኝ ይህ አቅጣጫ የሚጠቅም ይመስል ፀያፍ ስድብ እና ብሽሽቅ ስፖንሰር በማድረግ የፖለቲካ ዋልጌነታቸውን የሚያስመሠክሩት የአማራ ብሄርተኞች ናቸው።
.
ምከሯቸው… ❝እኛ ለመናገር ያልደፈርነውን ይናገሩልናል ይሳደቡልናል❞ በሚል አጉል አራዳነት የእኒህን ዕኩይ አዛውንት ያልተገራ አንደበት ማግዘፍ፣ እንደምሁር ቆጥሮ ማሸለምና በየሚዲያው እያቀረቡ መርዛቸውን እንዲረጩ ማድረግ ለማንም አይጠቅምም!
.
በቴሌግራም ➤ t.me/TalkEthiopia
.
#ታዲዮስታንቱ #የአማራብሄርተኝነት #ፋኖ #አሐዳዊነት #ልሙጣዊነት #ትምክህት #የብሄርፖለቲካ #ኢትዮጵያ
1.4K viewsedited  11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 09:30:35 ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የነበራቸው የፓርላማ ቆይታ ምን ይመስል ነበር? ከቀረቡላቸው ጥያቄዎችና ከሰጧቸው መልሶች መካከል ትኩረት ይሻሉ የምላቸውን አስመልክቶ ዕይታዬን እነሆ!
.
Enjoy! | Like | Share | Subscribe
.
[

]
.
ቶክ ኢትዮጵያን ያግዙ!
[ https://gofund.me/909f39f3 ]
የኢትዮጵያ የባንክ ሒሳብ… ⇩
AHMED ADEM GETU (CBE)
Acc NO: 1000436333483
.
#ዐቢይአሕመድ #ኢትዮጵያ #ፓርላማ #የሕዝብተወካዮች #ምክርቤት #ኢትዮጵያ
1.6K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 16:32:50
ዶ/ር ዐቢይ የፋኖ ስምን መጠቀሚያ በማድረግ የሚሠሩ በሚል የጠቀሷቸው ወንጀሎች
═══
.
➽ ከተማ ውስጥ ተኩስ መክፈት
➽ የነጋዴን ንብረት መዝረፍ
➽ ሴቶችን አስገድዶ መድፈር
➽ ሕፃናትና ሴቶችን መጥለፍ
➽ ሲባጎ ለጥፎ ግብር መሰብሰብ
➽ ፎርጅድ ብር ማምረት
.
#የአማራብሄርተኝነት #ፋኖ #አሐዳዊነት #ልሙጣዊነት #ትምክህት #የብሄርፖለቲካ #ኢትዮጵያ
1.7K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 16:25:56
ወዳጄ ❝የዘር ፖለቲካን እንቃወማለን❞ የሚል ሰምተህ እንዳትሸወድ! አውጋዦቹ ራሳቸው እልም ያሉ ብሄርተኞች ናቸው። ❝የኢትዮጵያ ዠግና❞ እያሉ የሚያንቆላጵሷቸው ዐፄዎችም ለልሙጥ ማንነት እንጂ ለኢትዮጵያዊነት እንዳልታገሉ ራሳቸውም ይመሠክራሉ።
.
አሁን በ❝ጎጃም-ጎንደር❞ ግብግብ መካከል የተጠመደውን የአብኑን አቶ ክርስትያን ታደለ ንግግር ስማው። ዐፄዎቹ የቆሙት አሁን እሱ ❝የአማራ ብሄርተኝነት❞ ብሎ ለሠየመው እንቅስቃሴ መሆኑን አፍ አውጥቶ ይነግርሃል። ስለብሄርተኝነት አንቆለጳጵሶ ያወራሃል።
.
ችግሩ እሱ አይደለም! ችግሩ በሌላ መድረክ ደግሞ ❝የጎሣ ፖለቲካ ኢትዮጵያን አቆረቆዘ❞ እያለ ሙድ ሲይዝብህ ማግኘትህ ነው! ❝የአማራ ብሄርተኝነት ችግር ገና ከመቆሚያ ፍልስፍናዎቹ ይጀምራል❞ ስልህ የኖርኩት ለዚሁ ነው!
.
#የአማራብሄርተኝነት #ፋኖ #አሐዳዊነት #ልሙጣዊነት #ትምክህት #የብሄርፖለቲካ #ኢትዮጵያ
1.6K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:58:02 "ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት" መባል መቆሙ ያንገበገባቸው ቀሲስ ፋሲል (አባ ሞቃዲሾ) በሥልጠና ስም የበተኑት የጥላቻ ሰበካ የዛሬ "ካየሁት በኋላ" ፕሮግራሜ ትኩረት ይሆናል። የተመልካች አስተያየትም ተካትቷል።
.
Enjoy! | Like | Share | Subscribe
.
[

]
.
ቶክ ኢትዮጵያን ያግዙ!
[ https://gofund.me/909f39f3 ]
የኢትዮጵያ የባንክ ሒሳብ… ⇩
AHMED ADEM GETU (CBE)
Acc NO: 1000436333483
.
#አባሞቃዲሾ #ደሴታዊነት #ሙስሊምጠልነት #IslamophobiaInEthiopia #አሐዳዊነት #ልሙጣዊነት #የሃይማኖትእኩልነት #እኩልነት #ኢትዮጵያ #ማኅበረቅዱሳን #ቀሲስፋሲል
1.6K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ