Get Mystery Box with random crypto!

ወለጋ የምስኪኑ ወሎዬ መታረጃ ሆና እስከመቼ? ══════ . በቅርብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደወሎ ሕ | Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ

ወለጋ የምስኪኑ ወሎዬ መታረጃ ሆና እስከመቼ?
══════
.
በቅርብ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደወሎ ሕዝብ ተሳዳጅና ሰለባ የሆነ የለም። በተለይ ደግሞ የደም ምድር ሆና በቀረችው ወለጋ የወሎ ጥላቻ ባናወዛቸውና የደም ጥማት ባሰከራቸው ታጣቂዎች እንደቅጠል የሚረግፈው ወለዬው ከሆነ እጅግ ሰንብቷል። ይኸው እንደተለመደው አንዳችም ጠባቂ የሌላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ከ250 በላይ የወሎ ተወላጆች (የወሎ ኦሮሞዎችን ጨምሮ) በወለጋ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተዘግቧል። በአንድ መስጊድ ውስጥ ብቻ ከ40 በላይ ሙስሊም ወለዬዎች በጭካኔ እንደተገደሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
.
እንደተለመደው ሁሉ መንግሥት "ገዳዩ ሸኔ ነው" ሲል OLA ደግሞ ውንጀላውን አስተባብሎ ድርጊቱን በመንግሥት ታጣቂዎች ማሳበቡን ዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። እስከዛሬም የተለመደው ይኸው ነው - ወሎዬው ይጨፈጨፋል። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችም "እኔ የለሁበትም" ይላሉ። መንግሥትም በታጣቂዎቹ እያሳበበ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል። ክስተቱም የልሙጥ ፖለቲካ አጀንዳ አራማጆችና የአስከሬን ነጋዴዎች የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆኖ አንዳችም መፍትሄ ሳያገኝ እንደቀልድ ያልፋል።
.
እጅግ ያሳዝናል! ንጹሃንን በመጨፍጨፍ የፖለቲካ ግባቸውን እንደሚያሳኩ የሚያምኑ ታጣቂ ቡድኖች መቼ ይሆን ወሎዬውን መቆመሪያ ማድረጋቸውን የሚያቆሙት?! መቼ ነው የወለዬ ሕይወት በወለጋ ከጓሮ እንስሳት የተሻለ ዋጋ የሚኖረው?! መቼ ነው ደም አፍሳሾቹ ገዳዮች በፍትህ እልፍኝ የእጃቸውን የሚያገኙት?! እስከመቼ ነው ይህን የአጀንዳ ቆማሪ እንጂ ከልብ ተቆርቋሪ ባለቤት ያጣ ምስኪን ወሎዬ እየጨፈጨፉ "እኔ አይደለሁም እገሌ ነው" በሚል ተራ መካካድና እርስ በእርስ ማሳበብ ደሙን ደመ ከልብ አድርገው የሚያስቀሩት?!
.
ወደድንም ጠላንም በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በወለጋ በወሎ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ሰብዓዊ ወንጀልና ጭፍጨፋ ለማስቆም ተከታታይ ዘመቻዎችን ማድረግ፣ ለምስኪኑ ሕዝብ ፍትህ ቢቀር ቢያንስ የመኖር ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ድምጹን ለዓለም ማሰማት፣ ጽንፈኛ ታጣቂዎችና የፖለቲካ ቁማርተኞች "ተቆርቋሪ የለውም" በሚል የሚጫወቱበትን ሕዝብ "አለሁልህ" የማለት ግዴታ አለብን።
.
የወሎ ተወላጅ አክቲቪስቶች እና ሚዲያዎች ተሰባስበው ጉዳዩን በዋና ባለቤትነት ማስኬድ፣ አጀንዳ ቀርፆና አስተዋይ አካሄድ መርጦ የተደራጀ ድምጽ የማሰማት እንቅስቃሴ ማድረግና ለክፉ የአስከሬን ነጋዴዎችና የፖለቲካ ቁማርተኞች መጠቀሚያ የማይሆን ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በበኩሌ እንደአንድ ግለሰብ እና የሚዲያ ባለሙያ በዚህ በኩል የቻልኩትን ለማድረግና የወሎን ሕዝብ ሰቆቃ ለማሰማት በቻልኩት የማግዝ ይሆናል። (ዛሬ ምሽት በዚሁ ጉዳይ ዕይታዬን ለማጋራት እሞክራለሁ!)
.
ንጹሃንን መያዣ እና መቆመሪያ የሚያደርግ ፖለቲካ ሁሉ ወዳቂ ነው!
.
#ወሎጠልነት #ወለጋ #ወለጋየደምምድር #የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #የወሎኦሮሞ #ኢትዮጵያ