Get Mystery Box with random crypto!

Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ talkethiopia — Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ talkethiopia — Talk Ethiopia | ቶክ ኢትዮጵያ
የሰርጥ አድራሻ: @talkethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.01K
የሰርጥ መግለጫ

በዋነኝነት በፌስቡክ የማጋራቸውን ጽሑፎች እና ላይቭ ቪዲዮዎች ባልተቋረጠና ሌሎች ፖስቶችን በማይቀላቅል መልኩ ለማድረስ የተቋቋመ ነው።
ድረገጽ [ https://www.talkethiopia.com ]
ፌስቡክ ገጽ [ fb.me/isuchisu ]
ዩቲውብ ቻነል [ bit.ly/SubscribeToIsaac ]
ትዊተር [ twitter.com/isuchisu ]

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-15 18:30:20

866 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 12:54:51
971 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 12:54:47 ለወሎ ተወላጅ ኤሊቶች እና አክቲቪስቶች አንዳንድ ጥቆማዎች
══════
.
ጠባቂ አልባ የወሎ ተወላጆችን ለይቶ እና አሥልቶ መጨፍጨፍ የፖለቲካችን አስቀያሚነት ጥግጋት ሆኗል። የወሎ ተወላጆች ሕይወት ከፖለቲካ መቆመሪያነት ያለፈ ዋጋ ሊሰጠው አልቻለም። ወለጋን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ወሎዬው ብቻ ተመርጦ እና ተሠልቶ ጭዳ እየተደረገ ነው። ጥቃቶቹ መስጊድ ውስጥም ጭምር ዘልቀው የገቡ እና እጅግ አውሬያዊ ገጽታ በተላበሰ መልኩ ሴቶችና ሕፃናትን ዒላማ ያደረጉ ናቸው። ለማን አቤት እንደሚባል ግራ የሚገባ ነው!
.
የወሎ ተወላጅ ምሁራን እና አክቲቪስቶች ከምንጊዜውም በላይ ኃላፊነታቸው የከበደበት ጊዜ ነው። የሚከተሉትን ነጥቦች መጻፍ ምንም እንኳን እጅግ ምቾት የሚነሣኝ እና የሚቆረቁረኝ ቢሆንም ወደመፍትሄ በሚደረገው ጉዞ ጥቂትም ቢሆን ካገዙ የራሴን ጠጠር ለመወርወር የወሎ ምሁራን እና አክቲቪስቶች እንዲያጤኗቸው በከበደ ልብ አደራ እላለሁ፦
.
——————
➽ ❶ አሁን ባለው ፖለቲካ በፈሰሰ ደማቸው ከመቆመር ባለፈ የወሎ ተወላጆች ስቃይና ሞት ግድ የሚለው ፖለቲካም ሆነ ፖለቲከኛ እንደሌለ እቅጩን መረዳት፤
.
➽ ❷ የወሎ ተወላጆች ሞት ቢያንስ በቀጣይ አደጋ ውስጥ ያሉ ወለዬዎች ሕይወት ሊተርፍ ወደሚችልበትና አጀንዳቸውም በስማቸው ሊያዝ ወደሚችልበት የአክቲቪዝም አቅጣጫ መዞር እንዳለበት መገንዘብ፤
.
➽ ❸ ማንነትን እና ሃይማኖትን ጭምር መሠረት ባደረገ የግድያ ወንጀልና የፖለቲካ ቁማር በወሎ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል በሌሎች ትርክቶች ውስጥ ተጥፋፍቶና ሳይጎላ ተሸፋፍኖ የሚያልፍበት ሁኔታ እጅግ አክሳሪ መሆኑን ተረድቶ ለተበዳዮች እየተበደሉበት ባለው ማንነታቸው እንዲጮህ ማድረግ፤
.
➽ ❹ የወሎ ተወላጆች ተለይተው እየተጨፈጨፉ ያሉት የፖለቲካ ውክልናም ሆነ ከልብ የሚቆረቆርላቸው ደጀን ስለሌላቸው መሆኑን ተረድቶ ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ያለን ግንኙነት መፈተሽ፣ ማጤን፣ ክሪቲካሊ ማየት፣ ማሻሻል፣ ማሸጋሸግ፣ ከተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር የውስጥ ውይይትና ድርድር ማድረግን ጨምሮ ሌሎችም ደጀን የማፍሪያ ወይም የመፍጠሪያ መንገዶችን ማሰስ፤
.
➽ ❺ ❝ወሎዬው እየተገደለ ያለው አማራ ስለሆነ ነው❞ የሚለውና ወሎዬው በማይጠቀምበት መልኩ ለተለያዩ አካላት የፖለቲካ አጀንዳ ማስያዣ የሆነው ድምዳሜ የወሎ ጉዳት በስሙ ተጠርቶ እንዳይወሳ፣ እንዳይጮህለትና በራሱ የሚገባውን ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎ የወሎን አጀንዳ በሰፊ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲሟሟ የሚያደርግ መሆኑን ተረድቶ የወሎው ጉዳት በስሙ ተጠርቶ እንዲጮህለት ማድረግ፤
.
➽ ❻ እንዲህ ዓይነት አውሬያዊ ጥቃቶች ሲደርሱ የወሎ አክቲቪስቶች ከባድ ኃላፊነት በትከሻቸው ላይ የሚወድቅ እንደመሆኑ መጠን አንዳንድ አክቲቪስቶች ስሜት እያሸነፋቸው የውግዘት አቴንዳንስ መያዝን በመሳሰሉ አላስፈላጊ ተግባራት ውስጥ ሲዘፈቁ ይታያል፤ ይህን መሰል ተግባራት የወሎን ሕዝብ ህመም በማንፀባረቁ በኩል ምንም ፋይዳ የሌላቸውና እንደውም የጎንዮሽ ቁርቁስን የሚፈጥሩ፣ አጀንዳውም የወሎ ጥቃት ለማይገዳቸው የፖለቲካ ቁማርተኞች ጥቅም ከማስገኘት ውጭ የወሎን ስቃይ የማይቀንስ መሆኑን ተረድቶ ይህንን የሚያደርጉ ልጆች እርምት እንዲወስዱ ማድረግ፤
.
➽ ❼ የትኛውም ትግል አቅጣጫው የሚወሰነው በትርክቱ በመሆኑ የወሎ ምሁራን እና አክቲቪስቶች በራሳቸው ተገናኝተው፣ ተወያይተው እና ተሟግተው በወሎ ተወላጆች ጥቅም እና ከስቃይ መትረፍ ላይ ያተኮረ የትግል ትርክት እና ዕቅድ ነድፈው መንቀሳቀስ አለባቸው፤ ለዚህም በራስ መድረክ መገናኘት እና ማውራት፣ የራስን ተወካይ መፍጠር፣ የራሳቸውን አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተደራዳሪ የኤሊት ቡድን ማዋቀር፤
———
.
ሌሎችም በርካታ መፍትሄዎች ይኖራሉ። እኔ ለጊዜው እነዚህ ታይተውኛል። ከምንም በላይ የወሎ ሕዝብ መሬት ላይ ያረፈ የፖለቲካ ውክልና፣ ድምጹን የሚያሰማ ተምሳሌታዊ ተወካይ ቡድን ይሻል! የወሎ ኤሊቶች ተነሡ! ተገናኙ! አውሩ! ተደራደሩ! ተለምዷዊ ሳይሆን ሣይንሳዊ በሆነ ሥሌት አጋርና ተቀናቃኛችሁን ለዩ! የፖለቲካ መቆመሪያ ለሆነው ምስኪን ሕዝባችሁ የሐዘኔታ ልብ ያላችሁ እናንተ ብቻ ናችሁና ❝ብቸኛ ወኪል❞ ሆናችሁ ውጡ! ፍትህ የሚያስጨንቀው፣ የንጹሃን ሞት የሚገደው ሁሉ ከጎናችሁ ይሠለፋል!
.
#የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎጠልነት #ወለጋ #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #ኢትዮጵያ
1.0K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:56:20
የሰው ነፍስ ዋጋ የሌለባት፣ የግድያ ዜና የሚከታተልባት መከረኛ አገር! ወለጋ ዛሬም የንፁሃን ደም በግፍ ፈሰሰባት! ከ2 ሣምንት በፊት የተጨፈጨፉት አንዳችም ፍትህ ሳያገኙ ሌላ ጭፍጨፋ!
.
ዛሬም ጠባቂም ሆነ የፖለቲካ ውክልና የሌላቸው ምስኪን የወሎ ተወላጆች በሰው በላ ታጣቂዎች መጨፍጨፋቸው አላቆመም! እንደአገር ኪሳራ ውስጥ ነን!
.
#የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎጠልነት #ወለጋ #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #ኢትዮጵያ
879 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 16:26:35
1.1K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 16:26:31 ❝የበታችነት ስሜት አለብህ❞ ይለኛል። የቃሉን ትርጉም ያውቀው አይመስልም። የማንነት ጭፍለቃን መሠረት ያደረጉ ጽዩፍ ሥርዓቶች አገሪቷ ላይ የደፈደፉትን ኋላቀርነት መፈቅፈቅ ስትጀምር በተራ ማብሸቂያ ሊያደናቅፍህ ይሞክራል!
.
ወዳጄ… አንተ ማኅበረ‐ፖለቲካዊ የበላይነትን ቻሌንጅ ማድረግን ❝የበታችነት ስሜት❞ ስትለው አላፈርክም። ሊትራሊ ተቃራኒ ነውኮ!
.
የበታችነት ስሜት ለማንነትህ መታገል አይደለም ‐ ምርኮኛ ላደረጉህ ደፍጣጭ ሥርዓቶች ቀን ተሌት ውዳሴ ማውረድ ነው! ግዴለህም ዘወርወር አድርገህ አስበው!
.
#የአሐዳውያንማምታቻ #አሐዳዊነት #የማንነትትግል #ኢትዮጵያ
1.1K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:34:05
ቴዲ አፍሮን በብዙ ነገር ልታማው ትችል ይሆናል… በንግድ ችሎታው ግን መቼም ቢሆን አታማውም! ብላቴናው ከምር ንግድ ይችላል!
.
#ቴዲአፍሮ
1.5K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 12:31:19
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዎች እንደቀልድ ይገደላሉ! እንደቀልድ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ ይቀራል! ንፁሃን ሕይወታቸው ይመሰቃቀላል! በዚያውም ተረስተው ይቀራሉ!
.
በወሎ ተወላጆች ላይ በወለጋና በሌሎችም ቦታዎች የተፈጸመው ግፍ የፖለቲካ ቁማር መበላያ ከመሆን ባለፈ ጠያቂ ኖሮትም፣ ፍትህ አግኝቶም አያውቅም! ያሳፍራል!
.
#ወሎጠልነት #ወለጋ #የወሎዬውሰቆቃእስከመቼ? #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #ኢትዮጵያ
1.3K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:56:59 በወለጋ ያለማቋረጥ በታጣቂዎች ደማቸው የሚፈሰው የወሎ ተወላጆች ጉዳይ አሁንም መቋጫ አልተገኘለትም። በጽንፍ ፖለቲካ ወዲያና ወዲህ ጫፎች የፖለቲካ መቆመሪያ የተደረገው ወሎዬ የሚጠብቀው ትግል ምን ይሆን?! ዕይታዬን እነሆ!
.
Enjoy! | Like | Share | Subscribe
.
[

]
.
#ወሎጠልነት #ወለጋ #ወለጋየደምምድር #የወሎሰቆቃእስከመቼ? #ወሎዬንመግደልይብቃ #ሸኔ #OLA #ብልፅግና #ኦሮሚያክልል #ወሎ #የወሎኦሮሞ #ኢትዮጵያ
2.1K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 13:53:08
1.7K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ