Get Mystery Box with random crypto!

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የሰርጥ አድራሻ: @rodas9
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 37.96K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-01-11 19:53:57

13.5K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 02:36:01 [የአምላክ ድንቅ ልደት በቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ [የክርስቶስ ልደት ምስጢር በያዕቆብ ዘሥሩግ ከሚለው መጽሐፉ የተወሰደ]
ርሱ እሳትን ለብሷል፤ በመጠቅለያ ጨርቅም ተጠቅልሏል፤ ግን ደግሞ ከመታወቅ በላይ ነው፤ በዙፋን ላይ ተቀምጧል እንዲኹም በግርግም ተኝቷል፤ ግን ደግሞ አይመረመርም፤ በኪሩቤል ዠርባ ላይ ተቀምጧል እንዲኹም ጉልበቶች ተሸክመውታል፤ እናም በዚያ ምክንያት ርሱ ታላቅ ነው፨

ርሱ የተፈጠሩ ፍጥረታትን ያላውሳቸዋል እንዲኹም ርሱ አካለ ሥጋን ተውሕዷል እናም እነርሱ ድንቁን ይናገራሉ፤ ርሱ ወገኖችን ያኖራቸዋል ርሱ እንዲኹም ወተት ይጠባል፤ ርሱን ይረዳው ያውቀው ዘንድ ማን ይችላል? ርሱ ዝናብን ያዘንባል፤ ርሱ ደግሞ ጡት ይጠባል፤ እናም ድንቁን ተመልከቱ፤ ርሱ ልዑል እና አስፈሪ ነው፤ ርሱም የሚቀኝለት ነው፤ እነሆ ድንቁ፨

ሰማይ ለእርሱ እጅግ ያንሰዋል እናም ርሱ መኖሪያን ፈለገ፤ እነሆ እንዴት ያለ ጸጋ ነው! ሱራፌል ራሳቸውን ይሸፍናሉ (ይጋርዳሉ)፤ ዮሴፍ ይሰግዳል አንዳች ድንቅ በዚኽ አለና፤ ሥልጣናት ተዘርግተዋል ሰዎችም ደካሞች ናቸው፤ ያስተውል ዘንድ ግን ማን ይችላል?፨

ክብር በአርያም፤ ሰላም በምድር፤ ለአዳም ተስፋና ውዳሴ በኹሉም ስፍራ፤ መላእክት ተደነቁ ጉባኤዎችም በደስታ አሰምተው ተናገሩ ሥልጣናትም እንዲኹ፤ ክፍላተ ሰራዊት አመሰገኑ ሰልፈኞችም ተንቀጠቀጡ፤ እናም ወደ ምድር ወረዱ፤ ሕያዋን እሳታሞች በድምቀት አበሩ፤ ረቂቃን ሕያዋንም እስትንፋስን አወጡ፤ መዘምራንም ተሰበሰቡ፤ ሺዎች ከአእላፍ ጋር በታላቅ ድምፅ አመሰገኑ በረሓማው ምድር ከሰማያውያን ሰራዊት ጋር አስተጋባ፡፡

የመላእክት ውበትም በግርማው በሌሊት ወጣ፤ የእሳት ብልጭታዎች እየተጠማዘዙ ምድርን ከበቡ፤ የብርሃን ፍንጣቂዎችም ተቀጣጠሉ እና ጨለማው ተገፈፈ፤ የእሳት ክንፎች ተዘረጉ ምሽቶችም ጠፉ የሰማይ ሕያዋን ወደታች ወረዱ በምድርም ላይ ተመላለሱና ሰማይ አደረጉት፨

ዳርቻዎች ለገናንነት ንጉሥ የምስጋናን ዘውድ አዘጋጁ፤ አንዱ ከሰማይ ሌላኛውም ከምድር ለርሱ ተበረከቱ፤ የሰማይ እና የምድር ሕያዋን አንዱ ከሌላው ጋር ተቀላቀሉ እና ብቻውን የኹሉ ጌታ ለኾነው የምስጋናን ዘውድ አበጁ (ጠለፉ)፡፡ ለሰዎች ያበሥሩ ዘንድ መላእክት ወረዱ፨

እንዲኽ ባበራው በወልድ አማካይነት ከምድር ወደ ሰማይ ይሸጋገራሉና፤ አንዱ ወገን ከሌላኛው ጋር ተያያዘ እና ምስጋና አስተጋባ፤ መላእክት እና ሰዎች በተለያየ ድምፅ በዚያ አመሰገኑ፤ ከገብርኤል ቤት የኾኑት ከአዳም ቤት ለኾኑት ድምፅን ሰደዱ፤ በሰማያውያን ሕያዋን ምስጋና (ውዳሴ) ይቀሰቀሱ ዘንድ፡፡

የነገደ ሚካኤል መዘምራን በጣፋጭ ዜማ ተጣሩ፤ የሰው ዘርም ይሰማ እና የእነርሱን ዝማሬ ይማር ዘንድ፤ የኪሩቤል ድምፅ በታላቅ መናወጥ አስተጋባ፨
የተዘጉ አንደበቶችን ለምስጋና ያነሣሣ ዘንድ፤ እንደ መለከትም ያንን የሱራፌልን “ቅዱስ፤ ቅዱስ፤ ቅዱስ” አሰማ፤ ያመሰግኑ ዘንድ ሰዎችን ለመቀስቀስ፤ ከፈጣኖቹ ሠረገላዎች ነጐድጓድ ወጣ እና ምድሪቱን ነቀነቃት ተናውጣ እንድትነሣ፤ ጌታዋ መጥቷልና በምስጋና እንድትዘምርም ሰማያውያን ሕያዋን በበገኖቻቸው የዝማሬያቸውን ዜማ አሰሙ፨

ክብር በአርያም፤ ለምድር ሰላም፤ ተስፋም ለአዳም፡፡ በላይ በሰማይ የክብር ዘውድ ለሰማያት ጌታ እና በታች በምድር ላይ ለሰዎች በጎ ፈቃድ፡፡ እረኞቹ እና መንጎቻቸው በሰሙት መልካም ዜና ደስ አላቸው፤ አጥብቀው አመኑ፣ ክብርንም ሰጡ፣ እንዲኹም ስጦታዎችን ተሸክመው አመጡ፨

ልበ ንጹሓን፣ ታናናሾች፣ እውነተኞች፣ ንጹሓን እና ታማኞች የኾኑት፤ እነርሱ ተለይተው መጥተው ዐሥራቱን በኩራቱን በመውሰድ አምጥተው ሰጥተዋል፤ እንዲኹም መርጠው ሠውተዋልና፤ ለካህንንነቱ በግ፣ ለሕፃንነቱ ወተት፣ ለንጉሥነቱ ምስጋናን ልባሞቹ ሰዎች አመጡ፤ የመላእክት ሰራዊት ተመሙ፤ ወደዋሻውም ቀረቡ፡፡

ገቡ እና አዩት፤ እጅ መንሻ ይዘውም በፊቱ ሰገዱ፤ እረኞቹ የመዠመሪያውን ዘውድ አበጅተው አቀረቡለት የመንጎቹ ጠቦቶች ለመጣው አማናዊ ጠቦት (በግዕ) ተሰጡት፤ ርሱ በመሠዋት ግልገሎቹን ከመሥዋዕትነት ያተርፋቸዋልና፤ መላእክት እና ሰዎች በሕፃኑ ፊት ተሰበሰቡ፨

መላእክት እና እረኞች አንድ ላይ ተቀላቀሉና ምስጋና ሰጡ፡፡ በልደቱ ተአምር የሰማይና የምድር መታረቅ ድንቁ ታላቅ ነው ምክንያቱም ዜማዎች ከዜማዎች ጋር ተዋሕደዋልና፤ የሰማይ ልጆች ከምድር ልጆች በአንዲት ዝማሬ፤ መንፈሳውያን ዜማዎች ከአካላውያን ዜማዎች ጋር ተዋሐዱ፤ የተዋሐዱ ዝማሬዎች ከኹሉም ዳርቻዎች ወደ ወልድ ዐረጉ፡፡

መንፈሳውያን አንደበቶች በሆሳዕናቸው በዚያ ተናገሩ፤ የሥጋ አንደበቶችም በቋንቋዎቻቸው በዚያ ጮኹ፤ የሰማያውያኑ የጠራ ድምፅ በምስጋና ከፍ ከፍ ብሎ ጮኸ፤ የእረኞቹም የተመረጡ ዜማዎች (ዝማሬዎች) ምስጋናን ዕጥፍ አደረጉ፤ ከእሳት ፍም የወጣውም የነበልባሉ ረጋ ያሉ ድምፆች ደምቀው አበሩ፨

ከሰው ዘር የሚመጣውም የመደነቅ ውዳሴ በረከተ (በዛ)፤ የንጹሕ እሳት ወላፈኖች ዝማሬያቸውን አሰሙ፤ የሰው አንደበቶችም በደስታ ጩኸት አስተጋቡ፤ መላእክት በማስተዋላቸው በጥበብ ድምፆችን ሰጡ፤ የተናቁ ሰዎችም በንግግራቸው ትሑት ምስጋናን ሰጡ፡፡

የሰማይ ሥልጣናት በልዩ ልዩ መልካቸው ትንሹን ግርግም ከበቡት፤ የመላእክት እና የሰዎች ሰልፎችም (ስብስቦችም) በአክብሮት ተዋሐዱ፤ ዋሻው በመንፈሳውያን መላእክት እና በሰዎች ጉባኤ ተመላ የሰማይና የምድር ልጆች አንደበቶች አስተጋቡ፤ ሰማይ እና ምድር፤ ለምስጋና ተያያዙ፨

በልደቱ ሰላም ያደረገውን ብቸኛውን የሰላም ባለባት ያመሰግኑ ዘንድ፡፡ ሕፃኑ ዝም ብሏል፤ ጉባኤው ሰፍቷል፤ ዜማዎች ከፍ ብለዋል መላእክት በተዋሐደ ሕብረ ዜማ ይዘምራሉ፤ ሰዎችም ያመሰግናሉ፤ ዋሻው ጠባብ ነው፤ ግርግሙም የተዋረደ፤ እናቲቱም ድንግል ናት
ዮሴፍ ይንቀጠቀጣል፤ ምስጋና በለኆሳስ ይወጣል፨
[እንኳን አደረሳችሁ]
[አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የልደትኽን በረከት በኔ ላይ አሳድር፤ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
12.7K views23:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-31 18:01:15

14.2K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 20:13:52
15.8K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 20:13:42
13.2K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 17:15:25 ዛሬ ታኅሣሥ 17 የመፀው ወቅት የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 12:52 ጀምሮ በገውዛ (ጀሚናይ) መናዝል መውጣት ትጀምራለችና የጨረቃ አፍቃሪዎች ፎቷችሁን በዘህ ቴሌግራም ቻናል ላይ የምታነሡትን ፎቶ መልቀቅ ትችላላችሁ።
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
13.7K viewsedited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 22:57:24
13.7K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 17:52:26
12.8K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 17:48:40 Emailing [Ethiopien 214] - ባሕረ ሐሳብ.pdf
15.5K views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-23 21:26:42 Emailing ግዕዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት.pdf
13.2K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ