Get Mystery Box with random crypto!

.

የቴሌግራም ቻናል አርማ merbebtt — . M
የቴሌግራም ቻናል አርማ merbebtt — .
የሰርጥ አድራሻ: @merbebtt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 343
የሰርጥ መግለጫ

እ ን ደ ው የላይ ላዩን . . .
@hmf27

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-07 21:08:16 ሃናማርያም


ጸዓዳማው ግቢያችንን መዋያ አጥ መንገደኛ ሁሉ የላይ ላዩን ከውጭ ቆሞ ካስተዋለው ካምፕ ነበር የሚመስለው። ማደሪያ ካምፕ። የየራሱን ልፋት ተኮር ኑሮ ምሽጉ ባደረገ ነዋሪ ላይ ስር ሰዶ፤ የተፈጥሮን ዙሪት ፅልመት ይሉትን ዑደት በእንቅልፍ ቢጤ ሽልብታ ሸውዶ፤ ነገ ላይ ለመገኘት መከተቻ ያደረጉት ካምፕ መሳይ ቅያስ እንጂ ከልጅ እስከ አዋቂ ከአዋቂም በእድሜ እስከጃጁ እንቢ አላረጅም ባይ ባልቴቶች ጉርብትና ላይ ከሰርክ እስከ መንፈቅ በማይረግብ ሆይሆይታ የተዋቀረ ግቢ አይመስልም ነበር። የጊዜ ንብብሮሽ ለነበር ትዝታ ሰጥቶኛል። ለዚህ ግቢ ልዩ ትዝታ አለኝ። በጣም ልዩ።


#ሃናማርያም
73 viewsH.M.F, edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:53:54 ሃናማርያም


ሀቀኛ ነው። የውሳኔ ሰው። ከአላማ ጋር ተፈራርሞ ከትጋት ጋር የቆረበ። ሁልጊዜ ግዱ ለእኔ ነው። ይመክረኛል። የመስማትም የመተግበርም ፍላጎት እንደሌለኝ ቢያውቅም ተስፋ ሳይቆርጥ ይመክረኛል፤ ጆሮዬ እስኪፋቅ እሰማዋለሁ። አፍታም ሳልቆይ ግን ልበደነዝ መሆኔና የሚነግሩኝን ከቁብ አለመቁጠሬ የራሴ ወቀሳ ቢሆኑልኝ ብዬ እመኛለሁ። ግን ምንም። ሁሉን ልክ ለመሆን መጣጣር ሰልችቶኛል። የተገኘውን ለመብላት በተገኘው የመደሰት ካጡም ለመተኛት የሚሆን አቋም ጎኔ ለምዷል። የአቋም ጉልበት ምንኛ የበረታ ነው?!

ክብር ለኔ !

#ሃናማርያም
72 viewsH.M.F, edited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:16:23 ቧልትን ከፈገግታ
ሳቅን ከፌዝ ጋራ
ባንድ ላይ ቀይጠን
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን ባህር ላይ ብናንቆረቁርም
ባህሩ ሰፊ ነው መልኩን አይቀይርም።

#በእውቀቱ_ስዩም
85 viewsAb, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:16:10
ደመ ግቡ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፍኩ ሀሴት

ይኸው
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ታየኝ ውብ ፈገግታ
(ከዚህ በፊት የማቀው)
የዘላለም ሳቅሽ በድንገት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
እናም ይህ ፈገግታሽ
የድጋሜ እዕድል ነው
ካ'ጥንትሽ ተከፍሎ
ከመልክሽ ተስሎ
በክብር የሚያሰልፍ
ጥልን የሚያሳልፍ
~

አብረሽ ውለሽ መናፈቅ ለምን አስፈለገሽ?
85 viewsAb, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:49:25
ዐይንህ ነገ ይበራል ቢሉት . . . የዛሬን እንዴት አድሬ? . . . kind situation over here . . . Can't wait !

78 viewsH.M.F, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:38:07 አንድ ብለን መሻታችንን ማሳደድ ከጀመርንበት ዕለት አንስቶ መሰልቸትን መጋፈጥ ምን ማለት እንደነበረ አናውቅም።

#ሃናማርያም
88 viewsH.M.F, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:13:02 ሃናማርያም

ቀኔን መንትፎ ሊሮጥ ያኮበኮበ ቀን ከጅምሩ ይታየኛል።

ሴት የመሆን አጋጣሚዬን ሊያከችቸው ነጋው ነጋው የሚል ቀን።

ሴትነቴን ሊያስደብተው ቆርጦ የቀረበ ቀን።

ከመንጋቱ ይወራል።

ከጅምሩ ይቀፋል።

ከሁለት የሆነች የሌት ጉንጉኔን መፍቻ ጉልበት ይነጥቀኛል።

ወረት ከማያውቃት ጣፋጯ ውሎዬ ያናትበኛል።

ከፊልም አለሜ የሚያናጋኝ፤

ከመፅሀፍቶቼ መንፈስ አላቆ ሸርተት የሚያደርገኝ ቀን አለኝ።

ሲንክ ሞልቶ የፈሰሰ ያልታጠበ ዕቃ የሚያቀርብልኝ፤

አፅዱኝ የሚል ቤት፤ አንጥፉኝ የሚል አልጋ፤ እዚህም እዚያም ጣዱኝ የሚል ድስት በረድፍ በረድፍ የሚያዘጋጅልኝ፤

አካልና መንፈስ አድክሞ ካልተጠበቀ እንግዳ በባዶ ቤት የሚያላትም አንዳንድ ክፉ ቀን አለኝ።

H.M.F 27
@Merbebtt
83 viewsH.M.F, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 12:06:54 "እምነት እና ተግባርን አጨባብጦ አብረው እንዲሄዱ የሚያደርጋቸው ነገር ከባድ ጭካኔ ነው።"

ሌሊሳ ግርማ
85 viewsH.M.F, 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:40:50 "I can't imagine life without reading , thinking and doing art."

John baladeessari
82 viewsH.M.F, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:53:47 ተዐምር የሚያስከትል ታምዕር ከሆነብኝ ሰነባብቶታል። አንድ እሱነቱ የስንቱን ሰው ተፅዕኖ መርታት ውጤት እንደሆነም ከጎኔ ሳሰልፈው አውቄአለሁ። መልካም ባህሪውን ጥለው የማይፈታ ኮስታራ ፊቱን እያዩ ሸሹት። ለኔ ግን ስሙ ያለ ጨዋ አይገለጥም። የሳቅን ተፈጥሮ ባፍጢሙ የደፋ ምን ተፈጥሮ ቢኖረው እንባዬ እስኪዝረከረክ በሳቅ የምንሳፈፍ እኔን ለማጀብ አዳጋች አልሆንኩትም። ባልጎደለ ዘዴ ተሞላልተን አለን።



#ሃናማርያም
89 viewsH.M.F, edited  19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ