Get Mystery Box with random crypto!

ደመ ግቡ ቀይ ሴት የመልኬ ገጽ ፍኩ ሀሴት ይኸው በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ ድንገት ባጋጣሚ ታየ | .

ደመ ግቡ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፍኩ ሀሴት

ይኸው
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ታየኝ ውብ ፈገግታ
(ከዚህ በፊት የማቀው)
የዘላለም ሳቅሽ በድንገት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
እናም ይህ ፈገግታሽ
የድጋሜ እዕድል ነው
ካ'ጥንትሽ ተከፍሎ
ከመልክሽ ተስሎ
በክብር የሚያሰልፍ
ጥልን የሚያሳልፍ
~

አብረሽ ውለሽ መናፈቅ ለምን አስፈለገሽ?