Get Mystery Box with random crypto!

ሃናማርያም ጸዓዳማው ግቢያችንን መዋያ አጥ መንገደኛ ሁሉ የላይ ላዩን ከውጭ ቆሞ ካስተዋለው ካም | .

ሃናማርያም


ጸዓዳማው ግቢያችንን መዋያ አጥ መንገደኛ ሁሉ የላይ ላዩን ከውጭ ቆሞ ካስተዋለው ካምፕ ነበር የሚመስለው። ማደሪያ ካምፕ። የየራሱን ልፋት ተኮር ኑሮ ምሽጉ ባደረገ ነዋሪ ላይ ስር ሰዶ፤ የተፈጥሮን ዙሪት ፅልመት ይሉትን ዑደት በእንቅልፍ ቢጤ ሽልብታ ሸውዶ፤ ነገ ላይ ለመገኘት መከተቻ ያደረጉት ካምፕ መሳይ ቅያስ እንጂ ከልጅ እስከ አዋቂ ከአዋቂም በእድሜ እስከጃጁ እንቢ አላረጅም ባይ ባልቴቶች ጉርብትና ላይ ከሰርክ እስከ መንፈቅ በማይረግብ ሆይሆይታ የተዋቀረ ግቢ አይመስልም ነበር። የጊዜ ንብብሮሽ ለነበር ትዝታ ሰጥቶኛል። ለዚህ ግቢ ልዩ ትዝታ አለኝ። በጣም ልዩ።


#ሃናማርያም