Get Mystery Box with random crypto!

ሃናማርያም ትላንት ሌላ ዛሬ ሌላ ! ከጥንተ ጥንተ ዘመን እየተሳቡ መጥተው 'አደገች እኮ ቁርጥ | .

ሃናማርያም

ትላንት ሌላ ዛሬ ሌላ !

ከጥንተ ጥንተ ዘመን እየተሳቡ መጥተው "አደገች እኮ ቁርጥ ቅላቷ ያባቷ " ምናምን እያሉ መዳፋቸው ጉያ ጉንጬን ሰክተው ከሚመጠምጡ የአዋቂ ውሪዎች መሀል ከእያንዳንዷ ሴት ጀርባ ቢቻላቸው የራሳቸው ሊያደርጉት የሚፈልጉትን አይነት ታታሪ፣ ጎበዝ፣ ልጆቿን ሲበዛ የሚወድላት ጥሩ አባት እና ጥሩ ባል ያላትን እናቴን በሆዳቸው መንፈሳዊ ቅናታቸውን አዝለው በጥርሳቸው ግን የወዳጅነታቸውን የሚፈግጉላት ነበሩ። መቀማጠልን የሚፈቅድ ባል። ወለድሽ አገባሁሽ ሳይል ጎንበስ ብሎ የሚታዘዛት ባል። ለሷ ሲሉት ካለው ላይም ከሌለው ላይም የማይሰስት ባል። ለማንምና ለምንም ቀርቶ "አላውቃችሁም"ብላ አንጀታቸውን ለቆረጠችላቸው ቤተሰቦቿ እንኳን አሳልፎ የማያስነካ ባል። እንዴት አያስቀናቸው?!
እኔ በማውቀው አባቴ ሲያኖረን እራሱን ሰውቶ ነው። ፍላጎቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ። ጭንቀቱን አምቆ። ተሳስቶ ቢያስከፋን የሚጨብጠው ኤሌትሪክ ሙሊት ገመድ ይጠፋዋል። ድሎትን ከሞላ ጎደል ገርምማ ያደገች ሚስት ናትና ያለችው ችግር ብሎ ነገር አታውቅለትም። ጠባብ ቤት ምን ሊመስል እንደሚችል ከአባቴ ጋር ከመኖሯ አስቀድሞ ከግምቷም አልነበር።

H.M.F 27
@Merbebtt