Get Mystery Box with random crypto!

ሃናማርያም ሀቀኛ ነው። የውሳኔ ሰው። ከአላማ ጋር ተፈራርሞ ከትጋት ጋር የቆረበ። ሁልጊዜ ግዱ | .

ሃናማርያም


ሀቀኛ ነው። የውሳኔ ሰው። ከአላማ ጋር ተፈራርሞ ከትጋት ጋር የቆረበ። ሁልጊዜ ግዱ ለእኔ ነው። ይመክረኛል። የመስማትም የመተግበርም ፍላጎት እንደሌለኝ ቢያውቅም ተስፋ ሳይቆርጥ ይመክረኛል፤ ጆሮዬ እስኪፋቅ እሰማዋለሁ። አፍታም ሳልቆይ ግን ልበደነዝ መሆኔና የሚነግሩኝን ከቁብ አለመቁጠሬ የራሴ ወቀሳ ቢሆኑልኝ ብዬ እመኛለሁ። ግን ምንም። ሁሉን ልክ ለመሆን መጣጣር ሰልችቶኛል። የተገኘውን ለመብላት በተገኘው የመደሰት ካጡም ለመተኛት የሚሆን አቋም ጎኔ ለምዷል። የአቋም ጉልበት ምንኛ የበረታ ነው?!

ክብር ለኔ !

#ሃናማርያም