Get Mystery Box with random crypto!

ሃናማርያም ቀኔን መንትፎ ሊሮጥ ያኮበኮበ ቀን ከጅምሩ ይታየኛል። ሴት የመሆን አጋጣሚዬን ሊያከ | .

ሃናማርያም

ቀኔን መንትፎ ሊሮጥ ያኮበኮበ ቀን ከጅምሩ ይታየኛል።

ሴት የመሆን አጋጣሚዬን ሊያከችቸው ነጋው ነጋው የሚል ቀን።

ሴትነቴን ሊያስደብተው ቆርጦ የቀረበ ቀን።

ከመንጋቱ ይወራል።

ከጅምሩ ይቀፋል።

ከሁለት የሆነች የሌት ጉንጉኔን መፍቻ ጉልበት ይነጥቀኛል።

ወረት ከማያውቃት ጣፋጯ ውሎዬ ያናትበኛል።

ከፊልም አለሜ የሚያናጋኝ፤

ከመፅሀፍቶቼ መንፈስ አላቆ ሸርተት የሚያደርገኝ ቀን አለኝ።

ሲንክ ሞልቶ የፈሰሰ ያልታጠበ ዕቃ የሚያቀርብልኝ፤

አፅዱኝ የሚል ቤት፤ አንጥፉኝ የሚል አልጋ፤ እዚህም እዚያም ጣዱኝ የሚል ድስት በረድፍ በረድፍ የሚያዘጋጅልኝ፤

አካልና መንፈስ አድክሞ ካልተጠበቀ እንግዳ በባዶ ቤት የሚያላትም አንዳንድ ክፉ ቀን አለኝ።

H.M.F 27
@Merbebtt