Get Mystery Box with random crypto!

✝መንፈሳዊ ህይወት✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ linkortodoxe21 — ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ linkortodoxe21 — ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
የሰርጥ አድራሻ: @linkortodoxe21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 784
የሰርጥ መግለጫ

✟✟✟በስመአብ ወወልድ በመንፈስ ቅድስ አሀድ አምላክ አሜን ✞✞✞
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርአት የጠበቁ ለመንፈሳዊ ህይወታችን ይጠቅሙናል ያስተምሩናል የምንላቸውን መንፈሳዊ
ትምህርቶች ብሒሎች ምክሮች እናስተላልፋለን።
ለሌሎች ሼር በማድረግ ቻናሉን ያጋሩ ✟✟✟
መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
✍️✍️ ሀሳብ ወይም አስተያየት ;👇👇
https://t.me/Ortodoxe21 በዚ ይላኩልን

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 13:09:46
መልካም ወጣት ዘተዋሕዶ

" ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3-4)

@Ortodoxe19
119 views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 11:20:22
መንፈስ ቅዱስ ስንቀበል


(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
41፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥

42፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

43፤ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?

44፤ እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።

45፤ ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።

እንደ ኤልሳቤጥ ድንግልን አመስግነን ሰግደን በደስታ ሆነን ተጽናንተን እንጂ የምን ለቅሶ ነው ጉድ እኮ ነው
መንፈስ ቅዱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲሞላባቸው ተደሰቱ እንጂ ጮሁ አለቀሱ ተበሳጩ የሚል የለም

" በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።
"
(የሐዋርያት ሥራ 13:52)

እና የፕሮቴስታንት እምነት ከየት አምጥቶት ነው

#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
108 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:27:37 "ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።"
#ቅዱስ_ሚናስ

@linkortodoxe21
135 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:27:27 ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
126 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 23:11:34
[ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው]

በዓለም መደሰት ወደ እግዚአብሔር ሊመራችሁ አይችልም ከእርሱ ያርቃችኋል እንጂ ። የዓለም ፍቅር ወደ ልባችሁ ከገባም አሳቦቻችሁና አመለካከቶቻችሁ መናጋት ይጀምራሉ ።

በዚህ ጊዜ እናንተ ተስማሚ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን አመለካከት እንዲህ እያላችሁ መጠየቅ ትጀምራላችሁ ፦ ይህንንና ያንን ማድረግ ስሕተቱ ምንድር ነው ? ! እንዲህ ባለው ነገር ብደሰት ኃጢአቱ ወይም ጉዳቱ ምንድር ነው ? ! ከዚህ በኋላ በመመርያዎችና በዋጋቸው የሚደረገው ሰንሰለታማ ክርክር ይጀምራል! ! ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ክርክሮችና ሙግቶች ምክንያት የሚሆነው ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው ።

ስለዚህ ልባችሁን በዓለም ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ውስጥ አታስቀምጡ ደጁ ሰፊ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አትችሉምና [ማቴ 7*13]

[_ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ _]

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
163 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 15:06:42 ጠያቂ:እናንተ ክርስትያኖች ግን ስንት አምላክ ነው ያላቹ

ክርስትያን:አንድም ሶስትም ልዩ አንድ ልዩ ሶስት ነት

ጠያቂ:እንዴት አንድ ነገር ሶስት ይሆናል ሶስት ነገርስ እንዴት አንድ ነገር ይሆናል

ክርስትያን:እኛስ መቼ አንድ ነገር ሶስት ይሆናል አልን አዎ አንድ ነገር ሶስት መሆን አይችልም እግዚአብሔር ግን አንድም ሶስትም መሆን ይችላል ተመልከት አንድ ነገር ሶስት መሆን የማይችለው በእኛ አይምሮ ወይም በአለማዊ ነገር ስለን ስላየነው ነው ይህ ደሞ ለአምላክ አይሆንም እኛ እግዚአብሔርን ልዕል አምላክ የምንለው ስለማይመረመር ስላማይደረስበት ጥልቅ ስለሆነ ነው እና አምላክ በእኛ ጭንቅላት ተሰፍቶ እንዴት ይህ ይሆናል ይህማ አይሆንም ብለን በዝች በጠባብ አዕምሮ ከሰፈነው ምኑን ልዕል ተባለ እንዴትስ አምላክ እንለዋለን በእኛ ጭንቅላት ከለካነው ስለዚ ወዳጄ እግዚአብሔር አንድም ሶስትም ነው አንድ ነገር ሶስት ሶስት ነገር አንድ መሆን አይችልም እግዚአብሔር ግን ይችላል

ጠያቂ:

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
145 viewsedited  12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:21:30 #እንኳን #ለቅድስት #ሥላሴ #ዓመታዊ #በዓል #በሰላም #አደረሳችሁ።
ዓለምን ካለመኖር የፈጠሩ፣ ፈጥረውም የሚያስተዳድሩ ሥላሴ በአካል ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ አንድ ናቸው።

√ በአካላዊ ግብር ሦስት ናቸው። በአካላዊ ግብር ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም ወላዲ አሥራጺ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ መባል ነው።

√ በሥልጣናዊ (በባሕርያዊ) ግብር አንድ ናቸው። በባሕርያዊ ግብር ሥምም አንድ ናቸው። ይህም አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ወዘተ የመሳሰለው ነው።

√ በከዊን ሦስት ናቸው። እኒህም ቃል መሆን፣ ልብ መሆን፣ እስትንፋስ መሆን ናቸው። በዚህም ሥላሴ ነባብያን፣ ሕያዋን፣ ለባውያን መሆናቸውን እናውቃለን

√ በባሕርይ አንድ ናቸው። ይህም ማለት የሦስቱ ኩነታት ተገናዝቦ አንድ ሕይወተ አንድ ባሕርይ ይባላል።

√ በአካል ሦስት ናቸው። በአካል ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ መባል ነው።

@linkortodoxe21
@linoortodoxe21
@linkortodoxe21
517 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:22:43 ውድ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ
#ሐዋርያነት
ሐምሌ ፭ ቀን ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት መታሰቢያ ዕለት ነው። ሐዋርያነት እስከ ሞት ድረስ እውነትን መናገር ነው። ሐዋርያነት ንጉሡ ኔሮንን እንዳይከፋው ተብሎ እውነትን ባለመናገር መተባበር አይደለም። መከራን፣ሞትን ሳይሰቀቁ እውነትን በአደባባይ መናገር ነው። ሐዋርያነት ፍቅርን ትእግስትን፣ ትሕትናን መሠረት አድርጎ እውነትን በአደባባይ መመስከር ነው። እውነትን መናገር ብቻ ሳይሆን ውሸትንም በአደባባይ መቃወም ነው።
።።
ሐዋርያነት ሁሉን ትቶ መከተል ነው። ራሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ኀደግነ ኵሎ ወተሎናከ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምንተ እንከ ንረክብ እንግዲህ ምን እናገኛለን ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጠይቆት ነበረ። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን ትቶ ተከትሎታል ቢሉ አንድ አህያ ነበረችው እርሷን ትቶ ተከትሎታል። ከምንም በላይ ግን "እከብር ባይ ልቡናን" ትቶ ተከትሎታል ብለው መተርጉማን ይናገራሉ። ሐዋርያ የእግዚአብሔርን ቃል በደስታ የሚናገር ነው። እውነትን በአደባባይ የሚመሰክር ነው። ይህን በማድረጉ ሰዎች ሲጠሉት ሲሰድቡት እና መከራን ሲያደርሱበት በደስታ የሚቀበል ነው።
።።
ሐዋርያ ለክብረ ቤተክርስቲያን የሚኖር፣ ፈጣሪውን የሚፈራ፣ በሰው መወደድን እና መከበርን የሚጠላ፣ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ፣ ሁሉን እንደራሱ የሚወድ ፍቅር ያለው፣ ለራሱ ድኅነት እና ለሰዎች መዳን የሚተጋ ነው።

የቅዱሳኑ ሐዋርያት በረከት ይደርብን።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
205 views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:04:31
እንካን አደረሳችሁ በዛሬ ቀን ቤተክርስቲያናችን በደንብ የምታከብራቸው በዓላት መካከል ይህ አንድ ነው።
ዛሬ ጾም የሚፈሰክበት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል በተለየ ሁኔታ የቅዱስ ጳውሎስ ወጴጥሮስ የተሰውበት ቀን ነች እና እንካን አደረሳችሁ አደረሰን

@linkortodoxe21
195 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:43:18
እንካን አደረሳችሁ

እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች
አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤
(ትንቢተ ዳንኤል 10:13)

#join or #share
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
377 views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ