Get Mystery Box with random crypto!

ውድ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ #ሐዋርያነት ሐምሌ ፭ ቀን ቅዱስ | ✝መንፈሳዊ ህይወት✝

ውድ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ
#ሐዋርያነት
ሐምሌ ፭ ቀን ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት መታሰቢያ ዕለት ነው። ሐዋርያነት እስከ ሞት ድረስ እውነትን መናገር ነው። ሐዋርያነት ንጉሡ ኔሮንን እንዳይከፋው ተብሎ እውነትን ባለመናገር መተባበር አይደለም። መከራን፣ሞትን ሳይሰቀቁ እውነትን በአደባባይ መናገር ነው። ሐዋርያነት ፍቅርን ትእግስትን፣ ትሕትናን መሠረት አድርጎ እውነትን በአደባባይ መመስከር ነው። እውነትን መናገር ብቻ ሳይሆን ውሸትንም በአደባባይ መቃወም ነው።
።።
ሐዋርያነት ሁሉን ትቶ መከተል ነው። ራሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ኀደግነ ኵሎ ወተሎናከ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምንተ እንከ ንረክብ እንግዲህ ምን እናገኛለን ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጠይቆት ነበረ። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን ትቶ ተከትሎታል ቢሉ አንድ አህያ ነበረችው እርሷን ትቶ ተከትሎታል። ከምንም በላይ ግን "እከብር ባይ ልቡናን" ትቶ ተከትሎታል ብለው መተርጉማን ይናገራሉ። ሐዋርያ የእግዚአብሔርን ቃል በደስታ የሚናገር ነው። እውነትን በአደባባይ የሚመሰክር ነው። ይህን በማድረጉ ሰዎች ሲጠሉት ሲሰድቡት እና መከራን ሲያደርሱበት በደስታ የሚቀበል ነው።
።።
ሐዋርያ ለክብረ ቤተክርስቲያን የሚኖር፣ ፈጣሪውን የሚፈራ፣ በሰው መወደድን እና መከበርን የሚጠላ፣ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ፣ ሁሉን እንደራሱ የሚወድ ፍቅር ያለው፣ ለራሱ ድኅነት እና ለሰዎች መዳን የሚተጋ ነው።

የቅዱሳኑ ሐዋርያት በረከት ይደርብን።

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21