#እንኳን #ለቅድስት #ሥላሴ #ዓመታዊ #በዓል #በሰላም #አደረሳችሁ። ዓለምን ካለመኖር የፈጠሩ፣ ፈጥረውም የሚያስተዳድሩ ሥላሴ በአካል ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ አንድ ናቸው። ። √ በአካላዊ ግብር ሦስት ናቸው። በአካላዊ ግብር ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም ወላዲ አሥራጺ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ መባል ነው። ። √ በሥልጣናዊ (በባሕርያዊ) ግብር አንድ ናቸው። በባሕርያዊ ግብር ሥምም አንድ ናቸው። ይህም አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ወዘተ የመሳሰለው ነው። ። √ በከዊን ሦስት ናቸው። እኒህም ቃል መሆን፣ ልብ መሆን፣ እስትንፋስ መሆን ናቸው። በዚህም ሥላሴ ነባብያን፣ ሕያዋን፣ ለባውያን መሆናቸውን እናውቃለን ። √ በባሕርይ አንድ ናቸው። ይህም ማለት የሦስቱ ኩነታት ተገናዝቦ አንድ ሕይወተ አንድ ባሕርይ ይባላል። ። √ በአካል ሦስት ናቸው። በአካል ሥምም ሦስት ናቸው። ይህም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ መባል ነው። @linkortodoxe21 @linoortodoxe21 @linkortodoxe21 517 views16:21