Get Mystery Box with random crypto!

[ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው] በዓለም መደሰት ወደ እግዚአብሔር ሊመራችሁ አይችልም | ✝መንፈሳዊ ህይወት✝

[ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው]

በዓለም መደሰት ወደ እግዚአብሔር ሊመራችሁ አይችልም ከእርሱ ያርቃችኋል እንጂ ። የዓለም ፍቅር ወደ ልባችሁ ከገባም አሳቦቻችሁና አመለካከቶቻችሁ መናጋት ይጀምራሉ ።

በዚህ ጊዜ እናንተ ተስማሚ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን አመለካከት እንዲህ እያላችሁ መጠየቅ ትጀምራላችሁ ፦ ይህንንና ያንን ማድረግ ስሕተቱ ምንድር ነው ? ! እንዲህ ባለው ነገር ብደሰት ኃጢአቱ ወይም ጉዳቱ ምንድር ነው ? ! ከዚህ በኋላ በመመርያዎችና በዋጋቸው የሚደረገው ሰንሰለታማ ክርክር ይጀምራል! ! ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ክርክሮችና ሙግቶች ምክንያት የሚሆነው ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው ።

ስለዚህ ልባችሁን በዓለም ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ውስጥ አታስቀምጡ ደጁ ሰፊ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አትችሉምና [ማቴ 7*13]

[_ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ _]

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21