Get Mystery Box with random crypto!

15:53

የቴሌግራም ቻናል አርማ lifein1553 — 15:53 1
የቴሌግራም ቻናል አርማ lifein1553 — 15:53
የሰርጥ አድራሻ: @lifein1553
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 260
የሰርጥ መግለጫ

✔ፊልም
✔ዘፈን
✔ግጥም
✔መፅሀፍ
✔ሳይኮሎጂ
✔የህይወት ተሞክሮ
✔አባባሎች
✔ታሪኮች
✔አነቃቂ ንግግሮች
✔አሰገራሚ እውነታዎች
✔ፎቶዎች
✔ፍልስፍና
✔ቪድዮዎች
Created by: ካህሊልአብዲ
TIK TOK: @1553_
INSTAGRAM: @lifein1553_

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-10 16:04:01 እግዚአብሔር ሲቀጣን

"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡

"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
54 views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 21:22:13 ሰው ለምን ያረፍዳል?

አንድ ሁሌም ወደ ቢሮ አርፍዶ ስለሚገባና አለቃው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለሰጠው ሰው ምሳሌ ልስጥህ። ይህ አርፋጅ ሰውዬ በተዳጋጋሚ ያረፍዳል ድጋሚ ማርፈድ ግን አይፈልግም፣ይህ ሰውዬም ‘‘ከነገ ጀምሮ በጥዋት እነሳለሁ፤ ከስራ ባልደረቦቼም ቀድሜ ስራ ቦታዬ ላይ እደርሳለሁ’’ ብሎ ይወስናል። በሚቀጥለው ቀን ግን፣ ልክ እንደ ትናንቱ አርፍዶ ይገባል። ከዚያም አለቃው ‘‘ለምንድን ነው ያረፈድከው?’’ ብሎ ሲጠይቀው፣ የተለያዩ ሰበቦቹን ይደረድራል። ሁሌም የሚያረፍድበት ምክንያት ግን ፓራዳይም መሆኑን እሱም ይሁን ምክር፣ ማስጠንቀቅያና ቅጣት የሚሰጠው አለቃው አያውቁም። ግለሰቦች፣ ድርጅቶችም ሆኑ አገር የማይቀየሩበት ምክንያት ፓራዳይም የሚሰራውን ስራ ጠንቅቆ ባለመረዳት ነው።

ብዙ ሰው የማይፈልገውን ነገር በማድረግ የሚፈልገውን ውጤት ባለማግኘቱ ይቆጨዋል። ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን የማይፈልገውን ውጤት የሚያስገኘውን ነገር በድጋሚ ያደርጋል። ወደ ስኬትና ደስታ የሚወስደውን፣ ማድረግ የሚገባውን ነገር እያወቀ ስለማይተገብረው፣ የማይፈልገውን ውጤት እያጨደ፣ የማይፈልገውን ሕይወት ይኖራል፤ ቅሉ ‘‘ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል አይደል!’’ አንተም በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሕይወት ውስጥ ካለህ፣ ‘‘ለምንድን ነው እያወቅክ የምታበላሸው?’’ ፓራዳይምህ መሆኑን ታውቃለህ?


ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ

@lifein1553
80 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 18:25:42 ሀገር በራሷ ጊዜ ተመስርታ አልተገኘችም:: የጥንት አባቶቻችን "የራሳችን ግዛት ይኑረን" ብለው ተነስተው መሠረቷት እንጅ:: እንዲሁ በሀገርነት ካልነበረችበት ተነስተው ሀገር ያደረጏት አባቶቻችን በጣሉት አሻራ መሠረት ሌሎች ተከታዮቻቸው ግዛት እያሰፉና ተቋም እየገነቡ የአሁኑን ቁመናዋን ሰጥተዋታል:: ይሁንና በመሐሉ ፈተና ነበር:: ሀገርን እስከማፍረስ የሚያደርስ ፈተና:: ለምሳሌ ዘመነ መሳፍንት::

በእንዲህ ያለ የፈተና ወቅትም ግን ሀገር ጀግኖችን አጥታ አታውቅም:: ከወደቀችበት አንስተው ከተበተነችበት ሰብስበው መልሰው ታላቅ ሀገር አድርገዋታል:: በሀገር ላይ ከባድ ፈተናዎች ሲመቱ ታላላቅ ጀግኖችም ይወለዳሉ:: ንጉሣነ ነገሥታቱን ቴዎድሮስና ምንይልክን የመሰሉ ለሰማይም ለምድር የከበዱ መሪዎችን: እነ በላይ ዘለቀን የመሰለ እሳት የላሱ መብረቅ የለበሱ አርበኞችን ያፈራልን በሀገር ሕልውና ላይ የተደቀነ ፈተና ነው::

አሁን ከጥንቱ የቀጠለ ፈተና ላይ ነን::

መላኩ አላምረው
85 views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 19:36:11
88 viewsedited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 17:25:45 የጣሊያን ቀራፂያን ናቸው፡፡ የበረዶ ኤግዚቢሽን እንዲህ በሚል ርዕስ አዘጋጁ...
"ህይወት አጭር ናት ከመቅለጧ በፊት አጠጥማት"
"life is short, enjoy it before it melts"
ማጣጣም ተብላ የተገለፀችው ቃል በግርድፉ ስጋዊ ደስታን ማሳደድ ብቻ ተብላ እንዳትወሰድ፡፡ የነፍስ ጥያቄዎችን መመለሻ የሚል ተዛማች ትርጓሜን ብንሰጣቸው የተሻለ ነው፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ የነፍስ ጥያቄን የሚመልስበት አግባብ እንደየመልኩ የተለያየ ነው፡፡
@UoG_Psych
85 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 15:16:13
[ በእውቀቱ_ሥዩም ]

ያንን ገለባ ልብ ፣ ከ'ደጅ የወደቀው
አድራሻህ ወዴት ነው ፣ ብለህ አትጠይቀው
የነገው ነፋስ ነው ፣ መንገዱን የሚያውቀው ።
96 views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 16:40:09 "...የኢትዮጵያ አባወራ ከሚስቱ ጋር ውይይት ይጀምራል፡፡ እንወያይ ብለው ይቀመጣሉ፡፡ ከዚያም ይናገር፣ ይናገር፣ ይናገርና...በቃ ጨርሻለሁ ደህና ዋዪ ይላል..."
ከመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
@lifein1553
95 viewsedited  13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 07:03:02
"ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል:: ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም:: ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!"

- ዊሊያም ሼክስፒር

@lifein1553
279 viewsedited  04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 22:42:15 ከነገሩ ውጪ መኖር ካልቻልክ ከነገሩ ጋር መኖር አትችልም
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)
ሰዎች አንድን ነገር በእጃቸው ለማስገባት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱት፣ ማስገባት ካቃታቸው ከሰው በታች እንደሆኑ የሚያስቡትና ተሳክቶላቸው ካስገቡ በኋለ ደግሞ ያንን ነገር ላለማጣት እንደገና ምንም አይነት የጭካኔም ስራ ቢሆን ከመስራት የማይመለሱት ከዚያ ነገር ውጪ ሙሉ ሕይወት ሊኖራቸው እንደማይችል ሲያስቡ ነው፡፡
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ከስልጣን ውጪ መኖር እንደማይችል ካሰበ ስልጣንን በእጁ ለማስገባትም ሆነ አንዴ በእጁ የገባውን ስልጣን ላለመልቀቅ ሌላውን በጭካኔ እስከማጥፋት ድረስ ይደርሳል፡፡ ይህ እውነታ ከዝና፣ ከሃብትና ከመሳሰሉት “ውጫዊ” ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ ተግባራዊነቱ ያው ነው፡፡
አየህ፣ ከስልጣን፣ ከዝና፣ ከሃብትና ከመሳሰሉት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ሊሰጣቸው ከሚገባቸውን ነገሮች ውጪ መኖር እንደምንችል ራሳችንን ስናሳምነው ብቻ እነዚህ ነገሮች በእጃችን ሲገቡ በተረጋጋና ከእኛና ከቤተሰባችን አልፈን ለሕብረተሰቡ የሚጠቅም ነገር እናደርግባቸዋለን፡፡ ምናልባት ጊዜው ተለውጦ ደግሞ ቀድሞ የነበረን ነገር በእጃችን እንደማይቆይ ስናስብ አሁንም ቀድሞ ከሁኔታው ውጪ በነበርንበት ጊዜ የነበረንን የተረጋጋ ማንነት ይዘን መቀጠል አያስቸግረንም፡፡
እቅጩን ልንገርህ፡- ከመወደድና ከተቀባይነት ውጪ አርፈህ መኖር ካልቻልክ በመወደድና በተቀባይነት ውስጥ አርፈህ መኖር አትችልም፡፡ ከሃብት ውጪ ተረጋግተህ መኖር ካልቻልክ ሃብትን ሰብስበህ ተረጋግተህ መኖር አትችልም፡፡ ከስልጣን ውጪ ሰከን ብልህ መኖር ካልቻልክ ስልጣን ብታገኝም ሰክነህ አትኖርም፡፡ ከዝና ውጪ ዘና ብለህ መኖር ካልቻልክ ዝነኛ ስትሆን ዘና ብለህ መኖር አትችልም፡፡
ቀድሞውኑ ያላረፈ ሰው ይህንና ያንን ባገኝ አርፍ ነበር የሚለውን ነገር በእጁ ለማስገባት ሲግለበለብ ኖሮ፣ እጁ ካስገባው በኋላ ደግሞ ያንን ነገር ከእጁ ላለማጣት ሲግለበለብ ለራሱና ለሌላው የረብሻ ምክንያት ይሆናል።

@lifein1553
134 viewsedited  19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 17:54:21
#መልካም_የትንሳኤ_በዓል

•┉┉•>> <<•̶┉┉•
•┉┉•>> <<•̶┉┉•

join: @lifein1553
123 viewsedited  14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ