Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ለምን ያረፍዳል? አንድ ሁሌም ወደ ቢሮ አርፍዶ ስለሚገባና አለቃው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለ | 15:53

ሰው ለምን ያረፍዳል?

አንድ ሁሌም ወደ ቢሮ አርፍዶ ስለሚገባና አለቃው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለሰጠው ሰው ምሳሌ ልስጥህ። ይህ አርፋጅ ሰውዬ በተዳጋጋሚ ያረፍዳል ድጋሚ ማርፈድ ግን አይፈልግም፣ይህ ሰውዬም ‘‘ከነገ ጀምሮ በጥዋት እነሳለሁ፤ ከስራ ባልደረቦቼም ቀድሜ ስራ ቦታዬ ላይ እደርሳለሁ’’ ብሎ ይወስናል። በሚቀጥለው ቀን ግን፣ ልክ እንደ ትናንቱ አርፍዶ ይገባል። ከዚያም አለቃው ‘‘ለምንድን ነው ያረፈድከው?’’ ብሎ ሲጠይቀው፣ የተለያዩ ሰበቦቹን ይደረድራል። ሁሌም የሚያረፍድበት ምክንያት ግን ፓራዳይም መሆኑን እሱም ይሁን ምክር፣ ማስጠንቀቅያና ቅጣት የሚሰጠው አለቃው አያውቁም። ግለሰቦች፣ ድርጅቶችም ሆኑ አገር የማይቀየሩበት ምክንያት ፓራዳይም የሚሰራውን ስራ ጠንቅቆ ባለመረዳት ነው።

ብዙ ሰው የማይፈልገውን ነገር በማድረግ የሚፈልገውን ውጤት ባለማግኘቱ ይቆጨዋል። ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን የማይፈልገውን ውጤት የሚያስገኘውን ነገር በድጋሚ ያደርጋል። ወደ ስኬትና ደስታ የሚወስደውን፣ ማድረግ የሚገባውን ነገር እያወቀ ስለማይተገብረው፣ የማይፈልገውን ውጤት እያጨደ፣ የማይፈልገውን ሕይወት ይኖራል፤ ቅሉ ‘‘ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል አይደል!’’ አንተም በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሕይወት ውስጥ ካለህ፣ ‘‘ለምንድን ነው እያወቅክ የምታበላሸው?’’ ፓራዳይምህ መሆኑን ታውቃለህ?


ትልቅ ሕልም አለኝ! አንድ ብር ከ አንድ ዶላር እኩል ነው!

ዳዊት ድሪምስ

@lifein1553