ሀገር በራሷ ጊዜ ተመስርታ አልተገኘችም:: የጥንት አባቶቻችን "የራሳችን ግዛት ይኑረን" ብለው ተነስተው መሠረቷት እንጅ:: እንዲሁ በሀገርነት ካልነበረችበት ተነስተው ሀገር ያደረጏት አባቶቻችን በጣሉት አሻራ መሠረት ሌሎች ተከታዮቻቸው ግዛት እያሰፉና ተቋም እየገነቡ የአሁኑን ቁመናዋን ሰጥተዋታል:: ይሁንና በመሐሉ ፈተና ነበር:: ሀገርን እስከማፍረስ የሚያደርስ ፈተና:: ለምሳሌ ዘመነ መሳፍንት:: በእንዲህ ያለ የፈተና ወቅትም ግን ሀገር ጀግኖችን አጥታ አታውቅም:: ከወደቀችበት አንስተው ከተበተነችበት ሰብስበው መልሰው ታላቅ ሀገር አድርገዋታል:: በሀገር ላይ ከባድ ፈተናዎች ሲመቱ ታላላቅ ጀግኖችም ይወለዳሉ:: ንጉሣነ ነገሥታቱን ቴዎድሮስና ምንይልክን የመሰሉ ለሰማይም ለምድር የከበዱ መሪዎችን: እነ በላይ ዘለቀን የመሰለ እሳት የላሱ መብረቅ የለበሱ አርበኞችን ያፈራልን በሀገር ሕልውና ላይ የተደቀነ ፈተና ነው:: አሁን ከጥንቱ የቀጠለ ፈተና ላይ ነን:: መላኩ አላምረው 85 views15:25